2023-02-24 07:51:51
በዩኬ 12 ሺህ ጥገኝነት ጠያቂዎች ቃለ መጠይቅ አያስፈልጋቸውም ተባለበዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) ወደ 12 ሺህ የሚጠጉ ጥገኝነት ጠያቂዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ፊት ለፊት ቃለ መጠይቅ ሳይደረግላቸው ጥያቄያቸው ተቀባይነት ሊያገኝ እንደሚችል ተነገረ።
ወደ አገሪቱ ለመግባት ቃለ መጠይቅ ሳያስፈልጋቸው የጥገኝነት ጥያቄያቸው ተቀባይነት ሊያገኝ ይችላል የተባሉት የአምስት አገራት ዜጎች ናቸው።
እነዚህም ኤርትራ፣ አፍጋኒስታን፣ ሊቢያ፣ ሶሪያ እና የመን ሲሆኑ ባለፈው ዓመት ሐምሌ ለጥገኝነት ጥያቄ ያቀረቡ መሆን አለባቸውም ተብሏል።
የስደተኝነት ጥያቄያቸውም የሚወሰነው ይህንን በቀጥታ የሚመለከተው የዩኬ የአገር ውስጥ ጉዳይ መሥሪያ ቤት (ሆም ኦፊስ) ባወጣው 10 ገጽ መጠይቅ ነው።
ይህ እርምጃ ከፍተኛ የጥገኝነት ጠያቂዎችን ቁጥር ለማቃለል ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ ቃል መግባታቸውን ተከትሎ ተግባራዊ የሚደረግ ነው።
የአገር ውስጥ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ይህ ውሳኔ ጥገኝነት ጠያቂዎችን በቀላሉ የማሳለፍ ጉዳይ አይደለም፣ ነገር ግን ሥርዓቱ የአምስት ሃገር ዜጎችን ጉዳይ ብቻ የሚመለከት ነው ብለዋል።
ከእነዚህ አምስት አገሮች የመጡ አመልካቾች ቀደም ሲልም 95 በመቶ የጥገኝነት ጥያቄያቸው ተቀባይነት ያገኝ እንደነበር ሆም ኦፊስ አስታውቋል።
ሆኖም የተለመደው የደህንነት እና የወንጀል ታሪካቸው ይጣራል እንዲሁም ሌሎች መረጃዎች የሚሰበሰቡ ሲሆን ነገር ግን ለመጀመሪያ ጊዜ ፊት ለፊት የሚደረግ ቃለመጠይቆች አይኖሩም ሲሉ ባለስልጣናት ተናግረዋል ።
በምትኩ ጥገኝነት ጠያቂዎች ፎርም መሙላት እና እስከ 40 የሚሆኑ ጥያቄዎችን መመለስ አለባቸው።
መጠይቁ በእንግሊዝኛ ተሞልቶ በ20 የስራ ቀናት ውስጥ ማስረከብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ካለበለዚያ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር የጥገኝነት ማመልከቻውን እንደተተወ ሊገምት ይችላል ተብሏል።
ሆኖም ባልስልጣናቱ ምላሽ ካላገኙ ክትትሎች እንደሚያደርጉና እያንዳንዱ ማመልከቻዎች በየራሳቸው እንደሚታዩ አስረድተዋል።
103 views04:51