Get Mystery Box with random crypto!

ኢብኑ ሲሪን ይሰኛል። ከአሊምነት ባሻገር እጅግ የናጠጠ ሀብታም ነው። በማር ንግድ ኃብቱ ይታወቃል። | Reyan Records

ኢብኑ ሲሪን ይሰኛል። ከአሊምነት ባሻገር እጅግ የናጠጠ ሀብታም ነው። በማር ንግድ ኃብቱ ይታወቃል። 600 በርሜል የሚጠጋ ማር በየጊዜው ለገበያ ያቀርባል። በወቅቱ የኛ ዘመን ሚሊየነር ማለት ነው።

ታዲያ ከእለታት በአንዱ ቀን ከማር በርሜሎቹ መካከል በአንዱ ውስጥ አይጥን አገኙ። እንደ ዘይት፣ ማር ወይም ወተት ባሉ ፈሳሽ ነገሮች ውስጥ ከወደቀ በሸሪአ ሁክሙ ሙሉ በርሜሉን መድፋት ነበርና አይጡን ከበርሜሉ ውስጥ አውጥተው ወረወሩት። በኋላ እንደፋዋለን ብለው የተውት በርሜል አላህ ለፈለገው ታላቅ ጥበብ የትኛው በርሜል እንደሆነ ረሱት።

ሙሐመድ ቢን ሲሪን ሁሉም በርሜሎች እንዲደፉ አዘዘ። ሙሉ ንብረቱን ለማጣት ወሰነ። በወቅቱ በዓለም ላይ ካሉ ባለፀጎች አንዱ የነበረ ቢሆንም ጥርጣሬ ባለው ነገር አላህን መገናኘትን ተጠነቀቀ። ሰዎችም እንዲህ አሉት፡- “ኢማም ሆይ! ይህኮ ከፍተኛ ኪሳራ ነው"
እርሱም መለሰላቸው ስለክስተቱ አብራራላቸው
"በአላህ እምላለሁ ይህ አርባ አመት ሙሉ ስጠብቀው የነበረ የወንጀሌ ውጤት ነው። ከአርባ ዓመት በፊት አንድ ሰው ብድር ጠይቆኝ ስሰጠው አንተ ደሀ ብዬው ነበር። በዚህ ቃል ምክንያት አላህ ቀጣኝ። አሁን አጠራጣሪ ነገር ተፈጥሯልና ለአላህ ስል ሙሉ ንብረቴ ላይ ወስኛለሁ"

ምንጭ
تاريخ بغداد / الخطيب البغدادي
Mahi Mahisho

@yesheh_kalidrashid_daewawoch
@yesheh_kalidrashid_daewawoch