Get Mystery Box with random crypto!

ወደ እውቀት ምክር ቤት ብቃረብ ኖሮ ፣ እና እኔ ብደርስባቸውና የነሱ ትውስታ አንድ አካል ብሆን ኖ | Reyan Records

ወደ እውቀት ምክር ቤት ብቃረብ ኖሮ ፣ እና እኔ ብደርስባቸውና የነሱ ትውስታ አንድ አካል ብሆን ኖሮ ፣ ያንን የፍቅር መንገድ ብከተል ኖሮ፣ እነሱም መንገድ ላይ አይተውኝም ነበር።  እኔም ትቼ አልሄድም ነበር። ሁሌም ቢሆን ምላሳቸው የነሱ ከዚክር የዘለለ ሌላ ነገር አይልም ነበር። ትክክለኛው መንገድ ላይ ነበሩ እነሱ። አላህን አምላኪዎች ብቻ ነበሩ። ትክክለኛውን መንገድ እስኪያገኙ ድረስ ይሄዳሉ። ከዛም አንተን ይወስዱሀል። እነሱ ሁሌም ቢሆን ልቦቻቸውን አላህን ከማስገዛት ወደጎን አይሉም ነበር። ሲታዩ አለም ከነሱ በፊት ምንም ነበር የሚመስለው። ይህንን መንገድ ከወደድከው እነሱ ይወስዱሀል።
.
.
ረያን አቡዲ

@Mejnun_Leyla_poem