Get Mystery Box with random crypto!

አይ ጊዜ፥ አወይ ጊዜ፥ ባለ ጊዜ.....፥ ውጣ ከፍ በል ከፍ አትስማው ይሄን እንከፍ ይለሀል በጠዋ | Reyan Records

አይ ጊዜ፥
አወይ ጊዜ፥
ባለ ጊዜ.....፥
ውጣ ከፍ በል ከፍ
አትስማው ይሄን እንከፍ
ይለሀል በጠዋት ሊለክፍ
ከሹመት ሰገነት ብረር ክነፍ
ከፊትህ የመጣ ተቀድሞ አይለፍ
ከንዳ አውርድ አንደገና አሳርፍ
ተጠንቀቅ ሰንደቅ ሰቃዩን አሳልፍ፥

አይ ጊዜ፥
አወይ ጊዜ፥
ባለ ጊዜ...፥
ሰፋ ሰፋ አርጉለት ያው መጣ መሰል
ትናንት የሌለውን ዛሬ ሰንደቅ ሊሰቅል
አሽሽሽሽ ዝም ብለህ ተቀበል
አይተህ እንዳላየ ሁንና አስመስል
ጊዜ ያወጣውን ጊዜ እንደሚሽረው
  የማናውቅ ይመስል፥
አይ ጊዜ፥
አወይ ጊዜ፥
ባለ ጊዜ...፥
ቀናብሎ ሊያየን ያፍር እንዳልነበር
ዛሬ ጊዜ ደርሶት ያዘምረን ጀመር።

ረያን አቡዲ
━━━━✦✗✦━━━━━━━
   ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን

አዘጋጅ፦ ግጥም እና ቅኔ

➳➳ ከወደዱት ለሌሎች ሼር ያድርጉ
@Mejnun_Leyla_poem