Get Mystery Box with random crypto!

ውዴታ እስከ ጀነት

የቴሌግራም ቻናል አርማ remye2 — ውዴታ እስከ ጀነት
የቴሌግራም ቻናል አርማ remye2 — ውዴታ እስከ ጀነት
የሰርጥ አድራሻ: @remye2
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 328
የሰርጥ መግለጫ

ምንኛ መታደል ነው የረሱል ሰ.ዓ.ወ ኡመት መሆን እርሳቸውን መከተልስ እንዴት ደስስ ይላል
ይህንን ላደለኝ አሏህ ምስጋና ይድረሰው አልሀምዱሊላህ ።
ይህ ግሩፕ የረመዳን ነስሩ ዋናው ቻናል ነው
ወደ ዋናው ግሩፕ ለመግባት @remye3
ይህ ግሩፕ ላይ አስየያት ያለው ካለ በ @remye ማሳወቅ ትችላላችሁ።
በተረፈ ወደ ግሩፑ ሰው በመጋበዝ ተደራሽነቱን እናብዛ ባረከሏህ ፊኩም።

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-06 07:15:02 ጉድ በሉ እናንተ....!

የታጠቁ ዘራፊዎች ወደ ባንክ ገብተው “አንድም ሰው እንዳይንቀሳቀስ! ገንዘቡ የመንግሥት ነው፤ ህይወታችሁ ግን የእናንተ ነው” ሲሉ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ተናገሩ። ሁሉም ሰው ወለሉ ላይ በደረቱ ተኛ። ይኼ “Mind Changing Concept ይባላል፤ ከተለመደው ወጣ ባለ መልኩ የሰዎችን አስተሳሰብ መቀየር ነውና። ጠረጴዛ ላይ ተደፍታ የነበረች አንዲት ሴት የማጉረምረም ድምጽ ስታሰማ፣ ከዘራፊዎች አንዱ ቆጣ ብሎ፣ “እመቤት እንደሰለጠነ ሰው አስቢ እንጂ። ይህ እኮ ዘረፋ እንጂ አስገድዶ መድፈር አይደለም” አላት ፀጥ አለች ይኼ “Being Professional” ነው፤ በሰለጠንክበት ጉዳይ ላይ ብቻ ትኩረት ታደርጋለህና።

ዘራፊዎቹ ያለምንም ችግር ቤታቸው ገቡ። ከዘራፊዎቹ መካከል ልጅ እግሩ እና የMaster of Business Administration ተመራቂው የተዘረፈው ገንዘቡ እንዲቆጠር ሃሳብ አቀረበ። ነገር ግን በዕድሜ ታላቅ የሆነውና እስከስድስተኛ ክፍል ብቻ የተማረው ዘራፊ፣ በቁጣ “አንተ የማትረባ ደደብ! ይህን ሁሉ ገንዘብ ማን ይቆጥራል? ዛሬ ማታ በቴሌቪዥን ዜና ላይ ስንት እንደዘረፍን ይነግሩናል፡” ይኼ “Experience” ይባላል። ዛሬ ዛሬ በትምህርት ከሚገኝ ዕውቀት ይልቅ 'ልምድ የበለጠ ዋጋ አለው"።

ዘረፋው ከተፈፀመ በኋላ፣ የባንኩ ማናጀር የባንኩን ሱፐርቫይዘር ጠርቶ በአስቸኳይ ፖሊስ እንዲጠራ ነገረው፡ ሱፐርቫይዘሩ ግን፣ “ቀይ ተረጋጋ! እየውልህ፣ መጀመሪያ ከካዘና 10 ሚሊየን አንስተን ለራሳችን እንውሰድ። ከዚያም ባለፉት ወራት የወሰድነውን 70 ሚሊየን እንጨምርበት።ለፖሊስ ሪፖርት ማድረግ ያለብን ይህን ገንዘብ ዛሬ ከተዘረፈው ጋር ደምረን ነው” አለው። ይኼ “Swim with the tide” ይባላል፡ የተፈጠረን አስቸጋሪ ሁኔታ ለራስ ጥቅም ማዋል እንደማለት።

ሱፐርቫይዘሩም አለ፣ “በየወሩ ዘረፋ ቢካሄድብንእንዴት መልካም ነበር!” በሚቀጥለው ቀን። ከባንኩ የተዘረፈው ገንዘብ 100 ሚሊየን እንደሆነ በቴሌቪዥን ዜና ተነገረ። ዘራፊዎች ደነገጡ፤ የዘረፉትንም መቁጠር ጀመሩ፤ ማመን አቃታቸው፤ ደግመው ቆጠሩ፤ ያው ነው፡ ትንሽ ቆይተው እንደገና መቁጠር ጀመሩ፤ ተመሳሳይ መጠን 20 ሚሊየን ብቻ! በጣም ተናደዱ፣ “እኛ ህይወታችንን ለአደጋ አጋልጠን 20 ሚሊየን ብቻ ስናገኝ፣ የባንክ ማናጀሩ ቁጭ ብሎ 80 ሚሊየን እንዴት ያገኛል?” ከንፈራቸውን ነከሱ፣ ጠረጴዛውን በቡጢ ነረቱ ፡፡ሌባ ከመሆን መማር ይሻላል ማለት ይህ አይደል?።

(Africa's elites are lords of poverty! SA ማን ነበር?) የማናጀሩ ፊት በፈገግታ እንደ ማለዳ ፀሐይ አብረቅርቋል፤ የደስታ ግምጃ አድምቆታል፡፡ በሽርክና ገበያው የተፈጠረበት ጉድለት ተሞልቶለታልና። ይኼንን “Seizing the opportunity ይሉታል። | ዋነኞቹ ዘራፊዎች እነማን ናቸው..?


╔════ ════╗
             ውዴታ እስከ ጀነት
@remye3
╚════ ════╝
1.1K viewsR. N, 04:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 17:13:53 ፍቅር..!

አንድ ሰው በጣም የሚወዳትን ቆንጆ ልጃገረድ አገባ። ግን ልጅቷ የቆዳ በሽታ ያዛትና ቀስ እያለች ውበቷን ማጣት ጀመረች። ይህን የተመለከተው ባሏ ለጉብኝት ራቅ ወደላ ስፍራ ሄደና በሚመለስበት ጊዜ አደጋ አጋጥሞት ዓይኑን አጣ። ሆኖም የጋብቻ ህይወታቸው እንደተለመደው ቀጠለ።

.. እናም ቀናት እያለፉ ውበቷን ደረጃ በደረጃ አጣች። ዓይነ ስውር ባል ይህንን አያውቅም እናም በትዳራቸው ሕይወት ውስጥ ምንም ልዩነት አልነበረም፡፡ እሷም እሱን መውደዷን ቀጠለች እሱም በጣም ይወዳት ነበር፡፡

ይቺ በጣም የሚወዳት ሚስቱ አንድ ቀን በድንገት ሞተች፡፡ ድንገት በመሞቷ ታላቅ ሀዘን ተሰማው። ሀዘን ሲበረታበት ከዚያች ከተማ ለመልቀቅ ፈለገ። በአካባቢው ይኖሩ የነበሩ ሰዎች “አሁን እንዴት ብቻውን መሄድ ይችላል? በእነዚህ ሁሉ ቀናት ሚስቱ ነበር የምትረዳው።” ብለው ይወያዩ ነበር።

ሰውየውም: “አይነስውር አይደለሁም ይህን ያህል ጊዜ የማላይ መስዬ ነበር የቆየሁት፣ምክንያቱም የቆዳ በሽታ እንዳለባት አውቅ ስለነበር የሷን ስሜት እንዳይጎዳ ብዬ ነበር፡፡ ውበቷ ሲጠፋ መጨነቅ ስለጀመረች ምንም እነዳልሆነ እንዲሰማት ፈለግሁ ስለዚህ እንደማላይ ነገርኳት።እሷ ለኔ በጣም ጥሩ ሚስት ነበረች።እሷን ደስተኛ ማድረግ ብቻ ነበር የምፈልገው።" አላቸው:: ለካ ባለማየት ውስጥ ድንቅ ማየት አለ፤ ፍቅር የደስታ እና የሰላም ምንጭ ነው!!

╔════ ════╗
             ውዴታ እስከ ጀነት
@remye3
╚════ ════╝
1.2K viewsR. N, 14:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-21 10:33:45
በአንድ ላይ ቆመን ልናወግዝ ይገባል!
Tokkummaan dhaabbannee balaalefachuu qabna !
**
በሀገራችን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ጭካኔ በተሞላበት አኳሆን ክቡር የሰው ልጅ
ህይወት በቀላሉ በሁሉም የህገሪቱ ክፍሎች እየተቀጠፈ ማህበረሰቡም
ከመላመዱ የተነሳ ስለሞተ ሰው ትቶ ከየትኛው ወግን ነው ? በሚለው በወረደ
አስተሳሰ ውስጥ ተዘፍቆ ጉዳዩን እንደተራ ክስተት መቁጠር ከጀመረ
ሰነባብቷል::ዘቅዝቆ ከመስቀል ፣ በህይወት እያለ በእሳት እስከማቃጠል ፣
ከነጠላ ግድያ እስከጅምላ ፍጅት ፣ ከታጠቅው ህገ ወጥ ኃይል ህዝብን
ይጠብቃል በህግ ይመራል እስከሚባለው የጸጥታ ኃይል እጅ የፍጥኝ ታሰረው
እስከሚረሸነው ፣ የቱ ተነግሮ የቱ ይተዋል? ሰው ልጅን ጨርሶ ምንን ለማሳካት
ነው ? የሥልጣን ጥማት ያሰከራቸውም ከሆነ ባዶ መሬት ለማስተዳደር ነው?
ደም ደምንእንጂ ሌላን አይወልድም:: ባሳለፍነው ሳምንት እንኳን ከወሎ ከሚሴ
እስኸ ጋምቤላ ፣ቀጥሎ ወለጋ የንፁሀን ደም እንደ ጎርፍ እየፈሰሰ አብዛኛው ሰው
ሞትን ከመላመዱ የተነሳ የማን ጎሳ ነው ?ከየትኛው አከባቢ ነው? ከማለት
የዘለለ ሰው ልጅ ክቡር ነው ከየትም ይሁን ከማንም ወገን ለምን ይገደላል
አይልም ::ኤሬ ጎበዝ በአንድ ላይ በጋራ ቆመን ግድያን መፀየፍና ገዳዮችን
በድፍረት ማውገዝ አለብን:: መርጠን ማልቀስ የትም አያደርሰን ::ሁላችንም
እስክናልቅ ወይም ሞት ደጃችንን እስኪያንኳኳ መጠበ የለብንም።
╔════ ════╗
             ውዴታ እስከ ጀነት
@remye3
╚════ ════╝
ሼር ሼር
1.1K viewsረመዳን ነሥሩ, 07:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-17 07:20:25 ውዴታ እስከ ጀነት pinned « ምርጥ ትውልዶች ============ ‌ሰብር አድርገን እናንብበው በዑመር (ረድየሏሁ አንሁ) ዘመን ሶስት ወጣቶች አንድ ስውዬን ጎትተው በማምጣት ያዐሚረል ሙእሚኒን ይህ ሰው አባታችንን ገድሏል ሀድ/ ቅጣት/ እንደትወስንበት እንሻለን በማለት ተናገሩ። ‌‌ ለምን ገደልክ ? ሲሉ ዑመር ጠየቀ ‌‌ ‹‹ እኔ የግመል እረኛ ነኝ አንደኛው ግመሌ የአባታቸው መሬት ላይ ካለ ዛፍቅጠል ቀንጥሶ ሲበላ አባታቸው ድነጋይ…»
04:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-17 07:11:31 አራት ትልልቅ ጥቅሞቺ በጁምአ

➊ ለጁመአ ሰላት መዘጋጀትና መማለድ ያለው ጥቅም

ረሱል (ﷺ) እንዲህ አሉ፡-

ለጁምአ ሶላት ያስታጠበና የታጠበ ከዚያም የማለደና በመጓጓዣ ሳይሆን በእግሩ የሄደ ፡ ከኢማሙ ቀርቦ ሳያለግጥ ያዳመጠ ሰው፡

በየ እርምጃው ሌሊቱን ቁሞ ቀኑን ፁሞ እንዳሳለፈው አንድ አመት ኢባዳ ያገኛል ፡፡

የጁምዐ እለት ታጥቦና በሚቺለው ፀድቶ ቅባቱን ተቀብቶ ወይም ከቤተሰቡ ሽቶ እንኳን ቢሆን ተቀብቶ ወደ መስጅድ የሄደ፡ በሁለት ሰዎቺ መካከል ሳይለያይ አላህ ያለለትን ሰግዶና ኢማሙ ሲናገር ፀጥ ብሎ አዳምጦ የተመለሰ ሰው እስከሚቀጥለው ጁምአ ድረስ ያለው ወንጀል ይማርለታል ፡፡


➋ ረሱል (ﷺ) ሰላዋት ማውረድ ጥቅም


ነብዩ ﷺ እንዲህ አሉ ፡-

አንድ ግዜ በእኔ ላይ ሶለዋት ያወረደ ሰው

በእርሱ ላይ አላህ አስር ጊዜ ሶለዋት ያወርድበታል ፡ አስር መንጀልም ይሰረዝለታል፡ አስር ደረጃ ይጨመርለታል ፡፡


➌ የሱረቱ ከህፍ (ከዋሻ ምዕራፍ ) መቅራት ጥቅም

ነብዩ ﷺ እንዲህ አሉ ፡-

ከሱረቱ ከህፍ አስር አንቀፅ የሐፈዘ ሰው ከደጃል ተንኮል ይጠበቃል፡ ደጃልን ያገኝ ሰው በሱ ላይ ሱረቱል ከህፍ መግቢያ ያንብበት ብለዋል ፡፡

የጁምዓ ቀን ሱረቱል ከህፍን የቀራ ሰው አላህ በሁለቱ ጁምዓዎች መካከል ብርሃን ያበራለታል ፡፡

➍ በጁምዐ ቀን ዱአ ማረግ ጥቅም

አላህ በጁመአ ቀን የዱአ አድራጊን ዱአ የማይመልስበት (ዱአውን የሚቀበልበት ) አንድ ሰአት አለቺ ብለዋል ፡፡

ዑለሞቺ በተለይም የቀኑ መጨረሻ ሰአት ላይ እንደሆነ ተናግረዋል ፡፡

አላህ የምንጠቀምበት ያድርገን !!!

╔════ ════╗
             ውዴታ እስከ ጀነት
@remye3
╚════ ════╝
2.2K viewsረመዳን ነሥሩ, 04:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-08 09:49:53
እንንቃ እንሰብሰብ!!
ለወንድሞቻችን ዘብ እንቁም!!
ሼር ይደረግ!!


ጎንደር ላይ እየሆነ ላለው ጭፍጨፋ እና ከልክ ያለፈ ኢስላም ጠልነት ተገቢውን መልስ መስጠት የሚችል መንግስት ያለ መስሎን ከምንጮህ ባይሆን እዝያው ሄደን ለችግሩ መፍትሄ የምናበጅበት መንገድ መፈለጉ ይሻላል።

በየ ቦታው የሚፈጠሩትን ችግሮች የትኛውንም የመንግስት አካላትን ሳንጠብቅ በግል ተንቀሳቅሶ አፀፋዊ ምሽላ የሚሰጥ ኢስላማዊ ቡድን ያስፈልጋል እስከመቼ ማለቃቀስ እስከመቼ ልመና እኛ ዛሬ ይህንን ቡድን እንደሚያስፈልግ ሁላችንም እናምናለን ግን ማን እንዲያርግገው ነው ምንጠብቀው ሁላችንም ለሙስሊም ወንድማችን ዘብ መቆም ሀላፊነት አለብን ።

እስከዛሬ እኛ ሀገር ላይ ሙስሊም ችግር ደርሶበት እምባውን ያበሰ መንግስት በእድሜያችን አላየንም።

ይህንን መልዕክት ሼር ይደረግ ሙስሊሙን ወጣት መንቃት አለበት ተንቀናል ይብቃን እስኪ ንቀቱ።

ፍትህ ለጎንደር ሙስሊሞች ለነብስ አድን ጥሪ መልስ የምንሰጥ ወንድ አሏህ ያድርገን።
╔════ ════╗
             ውዴታ እስከ ጀነት
@remye3
╚════ ════╝
2.5K viewsረመዳን ነሥሩ, edited  06:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-05 19:10:34
ያ ጀመዓ


ለይሉ ጁምዓ ነው ሰሉ አለ ሀቢብ
ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም ።
╔════ ════╗
             ውዴታ እስከ ጀነት
@remye3
╚════ ════╝
1.4K viewsረመዳን ነሥሩ, 16:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-01 18:43:48
ሰበር ዜና


በበርካታ የሳዑዲ ዓረቢያ አካባቢዎች ጨረቃ ስለታዬች፤
ነገ ቅዳሜ ረመዿን 01 ይጀመራል።
የረመዳን ጨረቃ በመታየቶ
ነገ ቅዳሜ ረመዳን አንድ ብሎ
ይጀምራል ።
እንኳን አደረሰን!
ወቅታዊ መረጃ እንዲደርሶ
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ
https://t.me/+UAKV32q7U2HKzEMf
253 viewsረመዳን ነሥሩ, 15:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-01 18:14:34 አሰላሙ ዓለይኩም ያጀመዓ
አሏህ ከረመዳን መልስ በሰላም በአማን ያገናኘን።

እስከዛም አንድ ልዩ ቦት ልጋብዛችሁና እርሱ ላይ ቁርዓን አቀራራችሁን አሳምሩ
﷽‎
@BismillahBot

ይህ ቦት አንዴ ትነኩትና የቁርዓን ቁጥር ብቻ ስትፅፉለት ያቀርብላችዋል ።


የአሏህ ሰላም እናንተ ላይ ይሁን።

መልካም የኢባዳ ወር
225 viewsረመዳን ነሥሩ, 15:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-30 17:18:19 Channel photo updated
14:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ