Get Mystery Box with random crypto!

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ወደ ክርስትናው ከተመለሰ በኋላ ገዳም ሲሔድ ይዞት የሔደው መጽሐፍ ቅዱስን | ረከብኪ ቲዩብ | Rekebki Tube

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ወደ ክርስትናው ከተመለሰ በኋላ ገዳም ሲሔድ ይዞት የሔደው መጽሐፍ ቅዱስን ነበር፡፡ ሌሎችም አባቶች ለመጽሐፍ ቅዱስ ልዩ ፍቅር ነበራቸው፡፡ ዛሬ እንዲህ ስማቸው ገንኖ እንዲሰማ ያደረጋቸው መፍቀሪያነ መጻሕፍት ስለ ነበሩ ነው፡፡ የሕይወታቸው ምሥጢር መጽሐፍ ቅዱስ ነበር፡፡ የሚጸልዩት መጽሐፍ ቅዱስን ነበር፤ ያውም በቃላቸው አጥንተዉት! በተለይ መዝሙረ ዳዊት እጅግ የተወደደ የጸሎት መጽሐፋቸው ነው፡፡
እነዚህ ቅዱሳን አባቶች ለመጻሕፍት የነበራቸው አመለካከት በእጅጉ የተለየ ነው፡፡ እንደ እነርሱ እያንዳንዱ ምእመን በሚገባው ቋንቋ መጻሕፍት ማንበብ አለበት፡፡ በሔዱበት አገር ፊደል ላለው በፊደሉ፣ ፊደል ለሌለው ደግሞ ፊደል ቀርጸው አስቀድመው ማንበብ እንዲችል ያስተምሩት የነበረውም ለዚህ ነው፡፡
በኢትዮጵያ ደረጃ ያለውን ስንመለከተውም ከዚህ የተለየ አይደለም፡፡ ከፊደላችንና ከቋንቋችን አንጻር የአባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን አስተዋጽኦ የሚዘነጋ አይደለም፡፡ ብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ. ታሪክ በጻፉበት መጽሐፋቸው ላይ ቤተ ክርስቲያን ለአገር ምን እንዳበረከተች ሲገልጹ፡- “ሙሉ ትምህርት፣ ፍጹም ቋንቋ ከነፊደሉ፣ ሥነ ጽሑፍ ከነጠባዩ ከነሙያው” ያሉትም ይህን ፍንትው አድርጎ የሚያስረዳን ነው፡፡
ነገር ግን ከዚህ መረዳት እንደምንችለው ቤተ ክርስቲያን ይህን ያደረገችው የራሳችን ፊደል አለን፤ የራሳችን ቋንቋ አለን ብለን እንዲሁ እንድንኩራራ ሳይኾን እንድናነብ ነው - እንድናነብ!!!