Get Mystery Box with random crypto!

ረቡኒ 🙏🙏🙏 አንዲት ቤተክርስትያን አንድ ሲኖዶስ አንድ መንበር 🙏

የቴሌግራም ቻናል አርማ rebuniy — ረቡኒ 🙏🙏🙏 አንዲት ቤተክርስትያን አንድ ሲኖዶስ አንድ መንበር 🙏 ረ
የቴሌግራም ቻናል አርማ rebuniy — ረቡኒ 🙏🙏🙏 አንዲት ቤተክርስትያን አንድ ሲኖዶስ አንድ መንበር 🙏
የሰርጥ አድራሻ: @rebuniy
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.04K
የሰርጥ መግለጫ

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ሰላም የ ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስትያን አማኞች
ይሄ ቻናል አላማው የተለያዩ
✤ትምህርቶችን መረጃዎችን
✤መዝሙሮችን እያቀናጁ ወደናንተ ማቅረብ ሲሆን በተጨማሪም መንፈሳዊ ነገሮችን ብቻ እያነሱ መማማር ነው።
ፔጅ @Rebuniy
ለአስተያየት @BotMsganabot

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-28 01:40:53 በገና ማለት ምን ማለት ነው

በገና መጀመሪያ የጀመሩት እነማን ናቸው ለምንስ ተጠቀሙበት

የበገና መዝሙር ከበገናው አውታር ወይስ ከእንጨቱ

በገና እንዴት መደርደር እንችላለ?

እንዲሁም ሌሎች የዜማ መሳሪያዋችን መግዛትም ሆነ መለማመድ የምትፈልጉ ሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ ላላችሁ ያላችሁበት ቦታ እንልካለን።

በተጨማሪም ነፍስን የሚያድሱ መዝሙሮች ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ። ለመቀላቀል OPEN የሚለውን ንኩት።




ይህን ይጫኑት ... ይህን ይጫኑት
.
█▓▒░        ►OPEN◄░►OPEN       ▒▓█
█▓▒░         ►OPEN◄░►OPEN      ▒▓█
█▓▒░         ►OPEN◄░►OPEN      ▒▓█
█▓▒░        ►OPEN◄░►OPEN       ▒▓█



OMEGA PROMOTION

.
2 viewsመንፈሳዊ 0K, 22:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 23:15:19
የተማሪዎች ምረቃ መርሃ ግብር
‹‹ የእግዚአብሔር ቃል በሙላት ይኑርባችሁ፡፡ በጥበብ ሁሉ እርስ በእርሳችሁ አስተምሩና ገሥጹ፡፡ በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊም ቅኔ በጸጋው በልባችሁ ለእግዚአብሔር ዘምሩ፡፡ ›› ቆላ 3÷16 የሚለውን የሐዋርያውን ቃል ይዘው ለተከታታይ 4 ዓመት የመንፈሳዊ ትምህርት ሲከታተሉ የነበሩት ተማሪዎች ምርቃት መርሃ ግብር እሁድ ነሐሴ 22 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት ይከናወናል፡፡
በዕለቱም ፡-
 ቃለ ወንጌል
 ያሬዳዊ ዝማሬ
 ስነ ጽሑፍ
 የምስጋና እና የእውቅና መርሃ ግብር
 ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ በሊቃነ ጳጳሳት ይሰጣል!
ያስታውሱ እሁድ ነሐሴ 22 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ ቀጠሮዎ ከእኛ ጋር ይሁን!
ቦታው፡- መሃል መርካቶ ደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ቤ/ክ ስብከተ ወንጌል አዳራሽ
57 views#Msgana Lemaryam, 20:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 21:44:01
254 views#Msgana Lemaryam, 18:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 21:43:10 ቡሄ ማለት ምን ማለት ነው??
"""""""" """""""""""""""""""""""""""""
የኢትየጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከምታከብራቸው ዘጠኝ ዓበይት በዓላት አንዱ የደብረ ታቦር በዓል ነው። በየዓመቱ ነሐሴ ፲፫ ቀን የሚከበረው ይህ በዓል መሠረቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ደብረ ታቦር ኢየሱስ ክርስቶስ ሦስት ደቀመዛሙርቱን ይዞ ወደ ተራራው የወጣበትና ፊቱ እንደ ፀሐይ የበራበት፣ ልብሱም እንደብርሃን ነጭ የሆነበት፣ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት ተራራ ነው።
ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው። በፊታቸውም ተለወጠ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ፥ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ። እነሆም፥ ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው። ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን ጌታ ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ በዚህ ሦስት ዳስ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ለኤልያስ እንሥራ አለ። እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፥ እነሆም፥ ከደመናው። በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ። ደቀ መዛሙርቱም ሰምተው በፊታቸው ወደቁ እጅግም ፈርተው ነበር።
ኢየሱስም ቀርቦ ዳሰሳቸውና፡ ተነሡ አትፍሩም አላቸው። ማቴ. ፲፯፡፩-፭ በቤተ ክርስቲያን ደብረታቦር ከቤተክርስቲያን ውጭ አከባበሩ ቡሄ እየተባለ የሚከበረው በዓል በሀገራችን በየዓመቱ ነሐሴ ፲፫ ቀን በታላቅ ድምቀት ይከበራል፡፡ ቡሄ ማለት ብራ፣ ብርሃን፣ ደማቅ ገላጣ፣ የተገለጠ ማለት ነው፡፡ ቡሄ ሲመጣ የክረምቱ ጨለማነት አልፎ ወደ ብርሃን፣ ወደ ጥቢ የሚያመራበት፣ ወደ መፀው የሚዘለቅበት ወገግታ ፣ ሰማይ ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት፣ የሚሸጋገርበት ወቅት በመሆኑ ከቡሄ በኋላ የጠነከረ ክረምት አይኖርም፡፡ በዚህ መሰረት የክረምቱ አፈና ተወግዶ የብርሃን ወገግታ የሚታየውም በዚህ በዓል አካባቢ ስለሆነ ይቺ ዕለት 'ቡሄ' የሚለውን ስያሜ አገኘ። ቡሄ ማለት ገላጣ፣ የተገለጠ ማለት ነው፡፡ ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት፣ ብረሃን የታየበት ድምጸ መለኮት የተሰማበት ስለሆነ፤ ችቦ ስለሚበራ የብርሃን በዓል በማለት የቡሄ በዓልም ይባላል፡፡
@Rebuniy
በገጠርም ሆነ በየከተማው ልጆች ጅራፋቸውን ገምደው ሲያጮሁ ይሰነብታሉ። እናቶችም ለበዓሉ ዝግጅት ስንዴ ሲለቅሙ፣ ሲፈትጉ፣ ሲፈጩ ይሰነብታሉ። መነሻ የሆናቸው ትውፊት ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት ዕለት ጊዜው ምሽት ነበር፡፡ እረኞችም ከብርሃኑ የተነሣ እየተገረሙና እየተደነቁ ወደ ቤት አልተመለሱም ነበር፡፡ የልጆቹን መዘግየት ያዩ ወላጆች ችቦ አብርተውና ዳቦ ይዘው ፍለጋ ወጥተዋል ፡፡ያንን ለማስታወስ «ቡሄ» ለሚሉ ልጆች ሙልሙል ዳቦ የሚሰጠውና ችቦ በማብራት በዓሉን የሚከበረው ከዚህ በመነሣት ነው፡፡ የንጋት ወጋገን ሲፈናጠቅ ልጆች በከባድ ድምጽና በጅራፍ ጩኸት የሚታጀብ፣ በገደላገደል ስር እንዲያስተጋባ ተደርጎ ብዛት ባላቸው ህጻናት በከፍተኛ ድምጽ የሚዘመር ነው ቡሄ ። የጅራፉ ጩኸትም እግዚአብሔር አብ “የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት” ሲል ሐዋርያት ራሳቸውን ስተው የወደቁበትን የመለኮት ድምፅ ለማስታወስ ነው፡፡
ደብረታቦር ወይም ቡሄ በአብነት ተማሪዎች “ስለ ደብረ ታቦር" እያሉ እህል፣ ፣ ጌሾ ለምነው ጠላውን ጠምቀው፣ ዳቦውን ጋግረው፣ ቆሎውን ቆልተው ለደብረ ታቦር ዕለት ሊያስቀድሱ የመጡትን ምዕመናን በመጋበዝ በታላቅ ድምቀት ያከብራሉ፡፡ ይህ ትውፊት መምህረ ሐዋርያት የነበረው ኢየሱስ ክርስቶስ ሦስቱን ተማሪዎቹን ጴጥሮስን፣ ያዕቆብንና ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ደብረ ታቦር ይዞ ሄዶ የተገለጠ ምስጢር ስለሆነ ከመምህራቸው ጋር በመሆን በዓለ ደብረ ታቦርን /ቡሄን ያከብራሉ፡፡ ስሙን ይጠራሉ፡፡
የበዓሉ እረዴት በረከት ይደርብን
አሜን።

#share
324 views#Msgana Lemaryam, 18:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 23:17:30 +++ፆመ ፍልሰታ
(ፆመ ፍልሰታ) ፍልሰታ ፆም(ፆመ ለማርያም) ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር እንዲሉ ፤ የፍልሰታ ፆም ከነሐሴ ፩ እስከ ፲፭ ነው። በቤተ ክርስትያናችን እንደሚገለፀው "እመቤታችን ያረፈችው ጥር ፳፩ ቀን ነው። ሐዋርያት በድኗን ሊቀብሯት ወደ ጌቴሰማኒ ይዘዋት ሲሄዱ አይሁድ አይተዋቸው በተኗቸው። በዚህ ጊዜ መላእክት የእመቤታችንን አስክሬን ወስደው በገነት አኑረውታል። በ፰ ወር በነሐሴ ሐዋርያት አስክሬኗን እንደገና ከጌታ ተቀብለው በጸሎትና በምህላ ቀብረዋታል። በዚህ የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ ከ፲፪ቱ ሐዋርያት አንዱ ቶማስ አልነበረም።

ቅዱስ ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ በደመና ተጭኖ ወደ እየሩሳሌም ሲመጣ ያገኛታል። በዚህ ጊዜ ትንሣኤዋን ሌሎች ሐዋርያቶች አይተው ለእሱ የቀረበት መስሎት ተናዶ፤ በፊት የልጅሽን ትንሣኤ ሳላይ ቀረሁ፤ አሁን ደግሞ የአንቺን ትንሣኤ ሳላይ ቀርቼ ነበር ብሎ ከደመና ሊወረወር ቃጣው። በዚህ ጊዜ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቶማስን አጽናንታ ከእሱ በቀር ሌላ ትንሣኤዋን እንዳላየ ነገረችው።

ቶማስም ሐዋርያት ወዳሉበት እየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ እመቤታችንን ቀበርናት ብለው ነገሩት። እሱም አውቆ ምስጢሩን ደብቆ አይደረግም ፤ ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር እንዴት ይሆናል አላቸው። ለማሳየትም መቃብር ሲከፍቱ አጧት በዚህ ጊዜ "እመቤታችን ተነስታ አርጋለች" ብሎ ሁኔታውን ተረከላቸው። ለምስክርም ይሆናል ብሎ የሰጠችውን (ሰበኗን) አሳያቸው

ሰበኗንም ለበረከት ቆራርጠው ተከፋፍለው ወደየ ሀገረ ስብከታቸው ተበታትነዋል። በዓመቱ ትንሣዬሽን ቶማስ አይቶ እንዴት እኛ ይቅርብን ብለው ከነሐሴ ፩ ቀን ጀምሮ ፪ ሱባዔ ቢገቡ በነሐሴ፲፬ ቀንም ሁሉን ማድረግ የማይሳነው ጌታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፤ አምላክ ዘሰብእ የዕለት ትኩስ በድን አድርጕ አምጥቶ ሰጣቸው ። ከቀበሯትም በኋላ በነሐሴ ፲፮ ቀን ተነስታለች። በዚህ ቀን ጌታችና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቀድሶ እመቤታችንም በልጇ እጅ ቆርባለች። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የሐዋርያት ቤተክርስትያን ቅድስት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን በየ አጥቢያው በሰዓታት፤ በፆምና በጸሎት የእመቤታችንን በረከት ለማግኘት ልጅ አዋቂ ሳይቀር በፍቅር ይህችን ጊዜ በፍጹም ፍቅር ትፆማለች።

የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ረድዔትና ፥ በረከቷ አማላጅነቷ በአገራችን በኢትዮጵያ ከሁላችንም ጋር ይሁን እናትነቷ ይብዛልን። አሜን!!! መልካም የፍልሰታ ፆም ይሁንልን!!! አሜን!!!
455 views#Msgana Lemaryam, 20:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 10:41:52
624 viewsዮሴፍ, 07:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-27 23:01:54 ሰኔ 20 እና 21
ⓇⒺⒷⓤⓝⓘⓎ ⓅⒶⒼ ከእመቤታችን 33ቱ በዓላት አንዱ ነው፤ህንጸተ ቤተክርስቲያን ይባላል። የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን የታነጸው በዛሬዋ ቀን ነው አናጺውም እራሱ ባለቤቱ ጌታችን መድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ነው፤ ቦታው ፊልጰስዩስ ነው፤ ቤተክርስቲያኗየተሰየመችው ደግሞ በእመቤታችን ስም ነው። ጴጥሮስ፤ ዮሐንስ በርናባስና ሌሎችም ሐዋርያት በፊልጰስዩስ ተሰብስበው ሳለ ጌታችን መድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በኪሩቤል ጀርባ ላይ ሆኖ እልፍ አእላፍ መልአክትን አስከትሎ ይወርዳል እመቤታችን በቀኙ ነበረች፤ 3 ድንጋዮችን አንስቶ ጎተታቸው እንደ ሰም ተለጠጡ እንደ ግድግዳም ሆኑ ዳግመኛም የብርሃን ምሰሶ ወረደ በሰማያዊቷ እየሩሳሌም አምሳያ አድረጎ አነጻት ሁለንተናዋም ተጠናቀቀ፤ ዳግመኛ በበነጋው #ሰኔ 21 ቀን እመቤታችንን እና ቅዱሳን መልአክትን አስከትሎ ይወርዳል ቅዳሴ ቀድሶ ለሐዋርያቱ አቆረባቸው ፍጹም ደስታም ሆነ።
 ከዚህ በኃላ ሐዋርያት ከጌታ እንዳዩት በዓለም ዞረው ቤተክርስቲያን አንጸዋል። ከዚያ በፊት የነበረው የነሶሎሞን ቤተመቅደስ የአይሁድ ምኩራብ የአይሁድ ስርዓተ አምልኮ መፈጸሚያ እንጂ የአዲስ ኪዳን የቁርባንም ሆነ የጥምቀት ስርዓት መፈጸሚያ አልነበረም፤ ታዲያ ሐዋርያት የት ነበር ህዝቡን የሚያጠምቁት የሚያቆርቡት ካሉ በየሰው ቤት ነበር። 

➨ዳግመኛ በዛሬዋ ቀን ታላቁ ነብይ ኤልሳዕ አረፈ። ይህ ነብይ በ 12 ጥማድ በሬ ሲያርስ ቴስቢያዊው ነብዩ ኤልያስ ተከተለኝ አለው ምንም ሳያቅማማ ሀብት ንብረቱን ትቶ ተከተለው፤ ኤልያስ በእሳት ሰረገላ ከማረጉ በፊት ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ ይለዋል ባንተ ላይ ያደረ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ እጥፍ ድርብ ሆኖ ይደርቢኝ ይለዋል፤ እንደ ቃሉ ሆነለት ተደረገለት፤ ኤልያስ አንድ ሙት ሲያስነሳ ኤልሳዕ ሁለት ሙት አስነስቷል፤ ኤልያስ አንድ ጊዜ ባህር ሲከፍል ኤልሳዕ ሁለት ጊዜ ባህር ከፍሏል። እምቤታችንን የኤልሳዕ ጋን ይላታል ኤልሳ የመረረውን ውኃ እንዳጣፈጠ እመቤታችንም ይህን መራራ ዓለም ጌታን በመውለዷ አጣፍጣዋለች፤ የዚህ ነብይ ድንቅ ታሪኩ 2ኛ ነገስት ላይ በስፋት ተጽፏል ሰኔ 20 ቀን እረፍቱ ነው ቤተክርስቲያን የዛሬውን ቀን እመቤታችንን እና ነብዩን አስባ ትውላለች። ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን።
አሜን
ምንጭ ፦ተዋህዶ ሐይማኖት
@Rebuniy
@Rebuniy
@Rebuniy
#Join and share
743 viewsMsgana, 20:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 21:14:10 በዚህች ዓለም ውስጥ የማይለወጥ ምንም የለም " ✥✥✥
@Rebuniy @Rebuniy
#join and.#share
እግዚአብሔርን የምትወዱት ይልቁንም እግዚአብሔር የሚወዳችሁ ክርስቶሳውያን ይህን እናውቅ ዘንድ እላችኋለሁ ።
በዚህች ዓለም ያለ ነገር ሁሉ መለወጡ አይቀርም ። ጤንነት በደዌ መለወጡ አይቀርም ፤ ሀብት በድህነት ፤ ክብር በውርደት ፤ ሹመት በሽረት ፥ ጥጋብ በረኀብ ፥ ሰላም በጦርነት ፥ ኃይል በድካም ፤ መግዛት በመገዛት ፥ ውበት በጉስቁልና ፥ ነጻት በባርነት ፥ አንድነት በብቸኝነት ፥ ዝና በኀፍረት ፥ ደስታ በኀዘን ይለወጣል ። ሕይወት በሞት ይለወጣል ።
ሰዎች እነዚህን ጉዳዮች መዘንጋታቸው ሁለት ችግሮን ያመጡባቸዋል ። የመጀመሪያው እጅግ ከመቀናጣት የተነሣ ቸልተኞቾ ፥ ለመንፈሳዊነት ግድ የለሾች ፤ ለሥርዓተ ቤተክርስቲያን ደካሞች ፥ ጥጋበኞች ይሆናሉ ። እነዚህ ሰዎች ለፍላጎታቸው የሚስማማ እምነት በተነሣ ቁጥር ይኮበልላሉ ። ለሰውም የማያዝኑ አረመኔዎች ፥ ድኻ አስጨንቀው ቀምተው የሚከብሩ ፥ ሕዝብ ገድለው የሚሾሙ አውሬዎች ይሆናሉ ።
@Rebuniy @Rebuniy
ሁለተኛ ደግሞ እንዲህ አይነት ሰዎች ቁሳዊያን ናቸውና የዓለምን ከንቱነትን ያልተረዱ የዓለምን ግሣንግሥ መሠረት አድርገው የሚደሰቱ ስለሆኑ አንድ ነገር በጎደለ ቁጥር ጭንቀታሞች ናቸው ። ሳይነኳቸው ይደማሉ ፥ ሳይገድሏቸው ይሞታሉ ፥ እየተመሰገኑም ተሰደብን ይላሉ ። የዓለም ነገር ደስታነቱ ለዚያች ሰአት ብቻ ስለሆነ ቀጥሎ ደግሞ ሌላ ደስታ ያሻልና ዓለምን የሚወድ ሰው ሁል ጊዜ ብኩን ይሆናል ።
ከቅዱሳን አንዱ እንዲህ አለ ። ይህቺን ዓለም የሚወድ ሰው የአዳኞችን ውሻ ይመስላል ። የአዳኞች ውሻ አድኖ እንስሳ ባይዝም ይደበደባል ። ቢይዝም ይደበደባል ። ቢይዝ የሚደበደበው የያዘውን እንስሳ በአዳኞች ስለሚፈለግ እንዳይበላው ነው ። ባይዝ መደብደቡ ለምን አልያዝክም ተብሎ ነው ። ይህቺን ዓለም የሚከተል ሰውም እንዲሁ ነው ። ባያገኝ በማጣቱ ያዝናል ፤ ቢያገኝ በመለየቱ በማለፉ ያዝናልና ።
እንዲህም ስለሆነ በተሾምህ ጊዜ እንደምትሻር አስብና ቅን ፍረድ ። ባገኘህ ጊዜ እንደምትደኸይ አስበህ ሥጥ ፥ ንብረትህ ፈጥኖ ሳይሸሽህ አንተ ለድኾች በመስጠት ቅደመው ፥ በጤንነትህ ጊዜ ደዌ እንዳለ አውቀህ የታመመ ጠይቅ ካለህ ጊዜ ድኾችን የታመሙትን ለመጎብኘት ጊዜ ይኑርህ ፤ ዝና ባለህ ጊዜ የሚበልጡህ ዝነኞች ሲመጡ እንዳትዋረድ ሰዎችን አታዋርድ ። ኃይል ባጣህ ጊዜ ኃይለኞች እንዳያስጨንቁህ በኃይልህ ዘመን ሰው አትግፋ ። ደስ ሲልህ የኀዘን ቀን አለና ከተጨነቁት ጋር አብረህ እዘን ። ውበትህ የሚጎሰቁልበት ዘመን ይመጣልና ውበቴ ይታወቅልኝ አትበተል ፥ ነገ በሚገሰቁል ውበትህ ሰዎችን አሰናክለህ የዘለዓለም ጉስቁልና እንዳያስከትልብህ ተጠንቀቅ ። ይህ ዓለም ቁም ነገር አይምሰልህ ፤ ለመጣል ይስብሃል እንጅ ስትወድቅ የሚያነሣህ አይምሰልህ ። ስለዚህ ብላሽ የሆነን ዓለም አገኘሁ ብለህም ደስ አይበልህ አጣሁት ብለህም አትዘን ።
@Rebuniy @Rebuniy
ዓለምን መውደዴን በምን አረጋግጣለሁ ትለኝ እንደሆነ አንድን ነገር ፈልገኸው ስታጣው የምታዝን በመሆንህ ነው ። ዳግመኛም አግኝተኽ በማጣትህም ስትተክዝ ነው ። ዓለም ከንቱ ነው ካልክ መመሪያህ የጻድቁ ኢዮብ ሕይወት ይሆናል ። ስታገኝ እግዚአብሔር ሰጠ ስታጣም እግዚአብሔር ነሣ ትላለህ ማለት ነው ። ክርስቲያናዊ ሕይወትህ በማጣትና ማግኘት ላይ እንዳይመሠረት ተጠበቅ ። ሳገኝ እንዲህ አደርጋለሁ አትበል ፥ በሌለህ ነገር እግዚአብሔር አይፈርድብህምና ። ስለሌለኝ ነው መልካም ያልሆንኩት ብለህም አታመካኝ ። ድኽነት ከጽድቅ አያስቀርምና ። መንግሥተ ሰማያትን ሰብከው ያወረሱ አንዳች የሌላቸው ሐዋርያት ናቸውና ።
ዓለም መለወጡ የማይቀር ነው ስንል በክፉ ብቻ አይደለም ። በመልካምም ነው እንጅ ። መልካሙ በክፉ እንዳለፈ ክፉውም በመልካም ማለፉ አይቀርም ። ሠለስቱ ደቂቅን ያከበሩ ባቢላውያን ማክበራቸውን ትተው በእሳት የወረወሩበት ቀን መጥቷል ። ከእሳቱ ደኅና ወጥተው ንጉሡ ራሱ እንደሰገደላቸውም ግን አትዘንጋ ።
የፈርዖን ጭካኔ እንደነበረ የሙሴ ነጻነት መጥቶ የለምን ? ምን በዚህ እንደነቃለን ! የአምስት ሺው ዘመን የዲያብሎስ መንግሥት በክርስቶስ መስቀል ፈርሶ የለምን ! ምንም መከራ ቢደርስብን መከራው እንደሚያልፍ እንወቅ ፥ እስንሞት የማያልፍ ቢሆን እንኳን ስንሞት እናርፈዋለንና ለመንግሥቱ እንቸኩል ።
ይህን በዐይነ መንፈስ ያየ ቅዱስ ይስሐቅ እንዲህ አለ ፦
" ኢተሃሊ ከመ ምንትኒ ዘውስተ ዓለም ዘኢይትወለጥ ከመዝ ሀሉ - በዚህ ዓለም ካለው ምንም ምን ቢሆን አይለወጥም
አትበል ። ዓለም ኃላፊ ነው እያልክ እንዲህ ሆነህ ኑር እንጅ "
ይቆየን
@Rebuniy
@Rebuniy
623 viewsMsgana, 18:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 13:15:19
"አርእይኒ ገጸ ዚአኪ ማርያም ምእረ፤ ዘኢይሰምዖ ካልዕ እንግርኪ ነገረ"
"ማርያም ሆይ፣ ለሌላው የማልነግረውን ነገር እነግርሽ ዘንድ አንድ ጊዜ ፊትሽን አሳይኝ"

መልክአ ማርያም
547 viewsBirukti, 10:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ