Get Mystery Box with random crypto!

◌◌ ◌◌#ሁዳ_ዓረፋ_ሾው◌◌ ◌◌ #ያስሚና:- #ያስ:- #ያስሚና:- #ኒብራስ:- #ያስ | TEAM HUDA

◌◌ ◌◌#ሁዳ_ዓረፋ_ሾው◌◌ ◌◌

#ያስሚና:- <<ሰዐቱ እየደረሰ ነው.... ሁላቹም ተዘጋጅታችኋል? >>
#ያስ:- <<ዝግጁ >>
#ያስሚና:- <<ካሜራ ማን Ready? >>
#ኒብራስ:- <>
#ያስሚና:- <<1.....2.... and.... action >>

★◌◌◌◌◌◌◌◌☆◌◌◌ ◌◌◌☆◌◌◌◌◌◌◌◌★

#ሪዛል:- <<አሰላሙ ዐለይኩም ውድ ቤተሰቦቻችን.... እንደምን ከርማችኋል? እንኳን በሰላም ለዒድ-አል-አድሃ በዓል በሰላም አደረሳቹ አደረሰን ። ይህ በናፍቆት ስትጠብቁት የቆያችሁት የሁዳ ሾው መሰናዷችን ነው።>>
#ያስ:- <<ከመክረም አላለፍንም ብለሽ ነው? >>
#ሪዛል:- <<እሱስ በጣም ..... እንኳን አንባቢያኑ እኔ ራሱ ሁዳ ሾው ናፍቆኝ ነበር >>
#ያስ:- <<ሁላችንም እሱን ስሜት የምንጋራሽ ይመስለኛል ..... አልሃምዱሊላህ ለሶስተኛ ጊዜ ስቱድዮአችንም አሸብርቆ ፣ እኛም በዒድ አልባሳት ፍክት ብለን ...>>
#ሪዛል:- << (ሂባ ከስቱድዮአችን ውጪ ኬኩን ሊጨርሱት መሆኑን እያስፈራራችን ) >>
#ያስ:- <<(አያልፍልሽ .... እስክንወጣ ሶብሪ)....በዒድ ሾው ዳግም ተገናኝተናል። ወደ ዝግጅቶቻችን ከማለፋችን በፊት ግን ለዚ ረዥም መጥፋት በቅድሚያ ይቅርታ ከመጠየቅ ብንጀምር የተሻለ አይመስልሽም?>>
#ሪዛል:- <<በደስታ.... >>
#ያስ:- <<የተወደዳቹ ቤተሰቦቻችን ባለፉት ወራት በሁኔታዎች አለመመቻቸት የተለመዱትን መሰናዶዎቻችን ወደናንተ በአግባቡ ማድረስ ባልቻልንበት ወቅት ከጎናችን ሆናቹ የኛን መመለስ ለጠበቃቹት በሙሉ ራህማኑ ጀዛቹን ይክፈልልን >>
#ሪዛል:- <<ከዛም በተጨማሪ በአስተያየት መስጫ ሳጥናችን ከጎናችን ያልተለያቹ በሙሉ ኢላሂ አስታዋሻቹን ያብዛላቹ >>
#ያስ:- <<አሚን..... ያንቺንም ያብዛልሽ >>
#ሪዛል:- <<አሚን .... ይሄን ካልን ብዙ ሳናስጠብቃቸው ወደ መሰናዶዎቻችን ብናመራስ?>>
#ያስ:- <<መርሃባ.... ውድ አንባቢያኖቻችን ሁዳዎች ደፋ ቀና ብለው...>>
#ሪዛል:- <<ጊዜያቸውን አሸጋሽገው የሚል ጨምሪበት >>
#ያስ:- <<ሃሃህ.... ፈተና ያጨለለው ሰው ንግግር ። .... ዓላ ኩሊ ሃል... ያሰናዳንላቹ መሰናዶዎች ተራቸውን እየጠበቁ ወደናንተ የሚደርሱ ይሆናል። በቅድሚያ ግን ዝግጅታችን በረካ እንዲኖረው የራህማኑን ቃላት አዳምጠን እንመለስ... >>
#ሪዛል:- <<በድጋሚ.... ዒዱኩም ሙባረክ >>

@Re_ya_zan