Get Mystery Box with random crypto!

Raya kobo communication

የቴሌግራም ቻናል አርማ raya_kobo_communication — Raya kobo communication R
የቴሌግራም ቻናል አርማ raya_kobo_communication — Raya kobo communication
የሰርጥ አድራሻ: @raya_kobo_communication
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 868
የሰርጥ መግለጫ

t.me/Raya_kobo_communication
ይህ ቻናል ስለ ራያ ቆቦ በየቀኑ ፣ በየሰዐቱ እና በየደቂቃዎች የሚወጡ መረጃዎችና አለም አቀፍ ድጊቶችን በፍጥነት ወደ ተከታታዮቹ ያደርሳል::
አስተያየት ካላችሁ https://t.me/Raya_Kobo_Com

☎️ 0333340269/756

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-07 10:33:04
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከመስከረም 30 ቀን 2015 ጀምሮ እንደሚሰጥ ተገለጸ::

ቆቦ፣ ነሐሴ 1፣ 2014 (ራ ቆ ኮ)

የ2014 የትምህርት ዘመን ብሔራዊ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ማጠቃለያ ፈተና ከመስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ለፋና ብሮድካስት በሰጠው መረጃ አስታውቋል፡፡
158 views07:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 21:16:05
የራያ ቆቦ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት በዓሉን ከነሃሴ 16-18 2014 ዓ.ም በራያ በድምቀት ለማክበር የቅድመ ዝግጅት ስራ እየሰራ ይገኛል፡፡

ሶለል- በራያ ቆቦ ሶለለ ሶለለ ይሄ የማነው ቤት ሶለለ የኮራ የፀዳ ሶለለ.....

የራያ ቆቦ ህዝብ የበርካታ ቱባ ባህሎች ባለቤት ነው፡፡ ከነዚህ ቱባ ባህሎች መካከል በየዓመቱ ከነሃሴ 16-18 በድምቀት የሚከበረው የልጃገረዶች በዓል ሶለል አንዱ ነው፡፡

ሶለል ማለት በራያ ቆቦ አካባቢ ባሉ ልጃገረዶች ዘንድ የሚከበር ሀይማኖታዊና ባህላዊ የልጃገረዶች የጭፈራ ስርዓት ነው፡፡ ይህ ባህላዊ ክዋኔ በላሊበላ አሸንድዬ፣ በሰቆጣ፣ ሻደይ እንዲሁም በራያ ቆቦ ደግሞ ሶለል በመባል በተመሳሳይ መንገድ ይከወናል፡፡

የአከባበሩም ሂደት በመጀመሪያ ደረጃ አሸንዳ የሚባል ቅጠሉ ሰፋፊ የሆነ የሳር ዘር ይነቀልና እሱን በገመድ ላይ በመደርደርና በማሰር በወገባቸው ዙሪያ በመታጠቅና ዳሌያቸውን ከግራ ወደ ቀኝ በማወዛወዝ የሚጨፈር የልጃገረዶች ባህላዊ ክዋኔ ነው፡፡

ከዚያም የባህል አልባሳትን እንደ ትፍትፍ፣ ማይማየ…የመሳሰሉትን በመልበስ፤ ባህላዊ የፀጉር አሰራሮችን እንደ አፈሳሶ፣ ሹሩባ፣ አንድእግራና ሌሎች የፀጉር ስሪት አይነቶችን በመሰራት ቀኑን ደምቀው ያደምቁታል።
248 views18:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 17:00:05
በራያ ቆቦ ወረዳ የአቅመ ደካማ የህብረተሰብ ክፍሎ ቤት ግንባታና ጥገና ተካሄደ::

ሐምሌ 28-2014 ዓ.ም ራያ ቆቦ ኮምኑኬሽን

በራያ ቆቦ ወረዳ የጎብየ ከተማ ወጣቶች ከማዘጋጃ ቤት ጋር በመተባበር የአቅመ ደካማ የህብረተሰብ ክፍሎችን ቤት ግንባታና ጥገና መደረጉን የወረዳው ስፖርት ፅ/ቤት አስታውቋል።

በቀጣይም ተግባሩ በሌሎች አካባቢዎች ተጠናክሮ እንደቀጥል ሁሉም ባለ ድርሻ አካላት አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ የወረዳው ስፖርት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ዮሃንስ ደጉ ጥሪ አስተላልፈዋል::
262 views14:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-01 15:47:14
የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ አመራሮች በራያ ቆቦ ወረዳ አራዶም ቀበሌ ሐምሌ 25 ቀን 2014 ዓ/ም የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሂደዋል።

በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ የግብርና ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ሐይለማርያም ከፍያለው፤ የቢሮው ምክትል ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር አልማዝ ጊዜው ጨምሮ የቢሮ አመራሮች፤ የሰሜን ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ እንዲሁም የራያ ቆቦ ወረዳ አመራሮች፤ ባለሙያዎችና አርሶአደሮች ተገኝተዋል።

በተጨማሪ በአካባቢው የሚገኙ የመከላከያ ሠራዊት እና የአማራ ክልል ልዩ ሀይል አባላት በችገኝ ተከላ መርሃ ግብር ተሳትፈዋል።

ዝርዝር ዜናውን ይዘን እንቀርባለን
371 views12:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 21:56:07 የራያ ቆቦ ወረዳ ወቅታዊ ምልእክት
======================
ሶለል የባህላችን ፈርጥ !!!
===============
ባህል ይወረሳል፣ ባህል ያድጋል ፣ ባህል ይዳብራል፣
ባህል ይሞታል ።
የሚያድገው የሚያሳድገው ማህበረሰብ ሲያገኝ ፤ የሚወረሰው የሚወርስ ተተኪ ሲኖር ነው ። በአንፃሩ ደግሞ የሚሞተው የሚንከባከበውና የሚከታተለው ማህበረሰብ ሲያጣ ነው ።

በራያ ቆቦ ከሚከበሩ ባህላዊ ሃይማኖታዊ ይዘት ካላቸው በአላት አንዱ ሶለል ነው ። ሶለል ከቅድመ አያቶቻችን የወረስነውና በየአመቱ ሳይቆራረጥ በልጃገረዶች የሚቀነቀን ጣእመ ዜማ ያለው ባህላዊ ሁነት ነው።

የሶለልን በአል አከባበርና ታሪካዊ አመጣጥ ስንቃኝ ሶለል በየአመቱ ከነሃሴ 16 ጀምሮ የሚከበር በአል በመሆኑ በአሉ ከመድረሱ ከ 5 ቀን በፊት ከ10-15 ቁጥር ያላቸው ቡድኖች ይደራጁና አለቃና ገንዘብ ያዥ ይመርጣሉ ።

ቆነጃጅቶች ጋሜና ቃሪሳ ፣ ጎበዝና ቆንጆ ፣ አንድ እግራና አፈሳሶ በሚባሉ የፀጉር ስሬቶች አምረውና ተውበው ቅድመ ዝግጅቱን ያጧጡፉታል ።

በሌላ በኩል ለሶለል የተመለመሉ ወጣት ሴቶች ባህላዊ አልባሳትን እንደ" ትፍትፍ"በተለያዩ ክሮች ያሸበረቀ" ሽራጦና መቀነት" ባህላዊ ጌጣጌጦች "ድኮት" በማጥለቅና ከእናቶቻቸው ያገኙትን "የብርድንብል" በደረታቸው ላይ ጣል አድርገው ጧት የወጣች ጀንበር መስለው ወደ በአሉ ይቀላቀላሉ ።

በበአሉ ቀን ማለዳ ተነስተው ከተቆጣጠሩና ለውበታቸው እርስበርስ አስተያየት ከተሰጣጡ በኋላ በመጀመሪያ የእድሜ ባለፀጋ የሆኑ አዛውንቶችና ታዋቂ ግለሰቦች ቤት በመሄድ በመረዋ ድምፃቸው ሶለልን ያንቆረቁሩታል ።

ሆኖም የዚህ በአል አከባበር ሂደት በ 2013 አ/ ም ክረምት ራያ ላይ በጦርነቱ ምክንያት የተቋረጠበት ሁኔታ በመፈጠሩና አሁንም ከጦርነት ስነ-ልቦናና እሳቤ ያልወጣንበት ወቅት ቢሆንም ባህሉን ለማሳደግና ባህላዊ ፈርጥነቱን ይዞ ዘመን እንዲሻገር ለማድረግ በዚህ አመት "ሃገር በቀል እውቀት ለተሻለ ማህበረ ኢኮኖሚ ፖለቲካዊና ባህላዊ እድገት" በሚል መሪ ቃል ይከበራል ።

ይህም ባህሉን ለትውልድ ለማስተላለፍ ብሎም በአለም የቅርስ መዝገብ እንዲመዘገብ የማድረግ አንዱ ተግባር ነው ።

ይህ ብቻውን ያለ ህብረተሰቡ እና የባለድርሽ አካላት ሚና ዋጋ ስለማይኖረው እንደተለመደው ከፍተኛ ርብርብ ማድረግ ይጠበቅብናል።
ስንል መልእክታችንን እናስተላልፋለን !!!

* ሶለል የባህላችን ፈርጥ ነው !!!
* ባህልን ማሳደግ የሁሉም ህብረተሰብ ሃላፊነት
ነው !!!

የራያ ቆቦ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት
ሃምሌ 21/2014
ቆቦ
372 views18:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 19:21:35 ʺአልደርቅ ያሉ የደም ቦዮች፣ አባሽ ያጡ እንባዎች"

እልፍ እንባዎች ፈስሰው፣ እልፍ ጊዜ ከንፈር ተመጥጧል፣ ቁጥሩ የማይታወቅ ሻማ ተበርቷል፣ ነጭ መብሩቅ ተወልቆ ጥቁር ማቅ ተጠልቋል፣ ሙሾ ተደርድሯል፣ ለቅሶ ተለቅሷል፤ የንፁሐን ሞት እልፍ ጊዜ ተወግዟል፣ ዳሩ የሻማው መብዛት፣ የከንፈር መምጠጡ መበርከት፣ ከሞት አላዳነም፣ እድሜ አልቀጠለም፣ ሰላም አላመጣም፡፡ አንደኛው ሻማ ሲጠፋ ሌላ ሻማ እየተበራ፣ የሞት ወግ በየቡናው እንደ ልማድ እየተወራ ቀናት አለፉ፣ ሳምንታት ከነፉ፣ ዓመታት ተከታተሉ፡፡
እናት ከጡቶቿ ተለይተው ስለሞቱ ልጆቿ ያለ ማቋረጥ ታነባለች፣ ከእቅፏ ተነጥለው የሰይፍ እራት ስለሆኑ የአብራኳ ክፋዮች የደም እንባ ታፈስሳለች፣ ወገቧን በገመድ አሥራ ትኖራለች፣ ዙሪያዋን በክፉ አድራጊዎች ተከባ ኤሎሄ ወይ ፍረድ ትላለች፣ ለጭንቄ ድረሱ ስትል ትጣራለች፣ ያጠለቀችውን ማቅ አላወለቀችም፣ የምታፈስሰውን እንባ አልገደበችም፣ ለማልቀስ እንጂ ለመሳቅ አልታደለችም፣ ስለሞቱት ልጆቿ እያለቀሰች፣ ስለ ቀሩት ልጆቿ ሕይወት ትንሰፈሰፋለች፣ የክፉ እጆች ቀሪ ልጆቿን ይቀስፍባታልና፡፡
ከሰይፍ ተርፈው የቀሩት ልጆቿን እንዳታጣቸው ትሰጋለችና፡፡

ትናንት ያለፈው አልፏል፣ ለነገው አይደገምም ተብላ ሌላ ሞት መጥቶ ልጆቿን ሲወስድባት፣ ባለቤቷን ሲነጥልባት፣ ጎረቤቷን ሲለይባት ተመልክታለችና፤
ዛሬም በቀሩት ላይ ክፉዎች እንደማይነሱ ማረጋጋጫ የላትም፡፡ ለዚያም ነው በስጋት የምታለቅሰው፡፡

ቀባሪ እስኪጠፋ ድረስ በአንድ ላይ ሄደዋል፣ በአንድ ጀንበር አልቀዋልና፡፡ መንገዳቸው ፊትና ኋላ አልሆነም፤ ብዙዎች በአንድ ቀን ላይመለሱ ሄዱ እንጂ፡፡ አስታምሞ መቅበር ብርቅ ሆኖባቸው፣ ዘመድና ወገን አቃብሩኝ ብሎ መጥራት ርቋቸው መኖር ግድ ብሏቸዋል፡፡
የሚያለቅሱት፣ ጥቁር ለብሰው ጥቁር ዘመን የሚያሳልፉት፣ እንባ እንደ ዥረት የሚያፈስሱት፣ አርሰው፣ አፍሰው የሚበሉ፣ አርሰው አፍሰው የሚያበሉ፣ ሐጥያት ያልተገኘባቸው፣ በደል የሌላቸው፣ በማንም ላይ ያልዘመቱ፣ በማንም ላይ ነፍጥ ያላነሱ ንፁሐን ናቸው፡፡

አርሰው በሚበሉበት፣ በሬና ገበሬ በአንድ ላይ በማሳ በሚውሉበት፣ ማሳው ተለስልሶ ዘር በሚበተንበት በክረምት ያላሰቡት ውርጅብኝ ወረደባቸው፣ የሞት ጥላ ጋረዳቸው፣ የእንባ ማዕበል አጥለቀለቃቸው፡፡ የተረፉት በክረምት ሸሹ፣ ከሞቀ ቤታቸው፣ ከሚወዷት ቀያቸው ተለይተው ነብሳቸውን ለማትረፍ ኳተኑ፡፡ ልጆች ከእናታቸው ጡት እየተነጠቁ ተሰዉ፣ ይድኑ ዘንድ መጠለያ ፈልገው በቤት የተደበቁ በክፉዎች እጅ እየታደኑ አለፉ፡፡ ፈሪ ሰው ነፍጥ የያዘውን ሸሽቶ በባዶ እጁ የተቀመጠውን ይገድላል፤ አፈሙዝ ወደ ያዘው አይተኩስም፣ ኾኖሎት አይዋጋም፤ ነገር ግን እርፍና ሞፈር የያዘውን ይገድላል፡፡ በኢትዮጵያን ባሕል ሞትን ሽሽት እንኳን ከቤቱ ከዛፍ ስር የተጠለለ ሰው ላይ ነፍጥ አይነሳም፣ ተተኩሶ አይገደልም፡፡ ጀግኖች ሀገር ሊያጠፋ የመጣ ጠላት እንኳን ፈርቶ ከዛፍ ስር ተጠልሎ እንዳይገድሉት ከጠያቀቸው አፈሙዛቸውን ያነሳሉ፣ ጎራዴያቸውን ወደ ሰገባቸው ይመልሳሉ፡፡ ለምን የተጠለለ አይገደልምና፤ የጀግና ወጉ ፊት ለፊት የገጠመን ገድሎ ማሸነፍ ነውና፡፡

ፈሪዎች ግን ልጇን የታቀፈችን እናት፣ ሞፈርና ቀንበር ተሸክሞ በሬዎችን የሚነዳ አባት፣ በሜዳው ያለ ክፋት የሚቦርቁ ሕጻናትን፣ ለፈጣሪያቸው ምሕላና ምልጃ የሚያደርሱ አዛውንቶችን በግፍ ይገድላሉ፣ የንጹሐንን ደም በግፍ ያፈስሳሉ፣ በሃይማኖት ተቋማት የተጠለሉ ንጹሐንን የሃይማኖታዊ ክብሩን ንቀው፣ የሰብዓዊነት ከፍታውን አዋርደው ያሻቸውን ያደርጋሉ፡፡ ንፁሐንን ገድሎ የክፉዎች ምድር መፍጠር ይሆን? ወይንስ በንፁሕ ደም ደስታን መሻት ይሆን? ዓላማቸው አይታወቅም፡፡ ቀን እየጠበቁ የንጹሐንን ደም ያፈስሳሉ፤ ቤት ያፈርሳሉ፣ ያልሰሩበትን ንብረት ይወርሳሉ፡፡

በንጹሐን እልቂት ብዙዎች አንብተዋል፣ በድርጊቱ ተሸማቅቀዋል፣ ብዙዎች አውግዘዋል ነገር ግን እንባው፣ ማውገዙና ማዘኑ የሚሞቱትን አላዳናቸውም፡፡ ሌላ ሞት እንዳይኖር ጠበቃ አልሆናቸውም፡፡ ከሰሞኑ የሽብር ቡድን ታጣቂዎች በምዕራብ በወለጋ ጊምቢ ወረዳ ባደረሱት ጥቃት ብዙዎች ላይመለሱ አሸልበዋል፤ በስቃይ ውስጥ አልፈዋል፡፡ እናት እና ልጅ ተለያይተዋል፣ በግፍ ከመጣው ሞት የተረፉ አዛውንቶች ጧሪ አጥተዋል፡፡ ከአንድ ቤተሰብ ውሰጥ ብዙዎች አልፈዋል፡፡

አልደርቅ ያሉ የደም ቦዮች፣ አባሽ ያጡ እልፍ እንባዎች ተበራክተዋል፡፡ ከዛሬ ነገ ይደርቃል፣ ሰላም ይመጣል፣ አጥፊዎች ቢቻል ልብ ገዝተው ካልተቻለ ራሳቸው ጠፍተው ንጹሐን አርሰውና አፍሰው የሚበሉበት፣ በሰላም የሚኖሩበት ዘመን አልደርስ ብሏል፡፡ ዜጎች ያለ እረኛ እንደ ተለቀቁ በጎች ተኩላው ከጎሬው እየወጣ እየበላቸው፣ ያለ ዘመናቸው እየወሰዳቸው ነው፡፡ የዜጎች እረኛም በአጥፊዎች ላይ በትሬን እያሳረፍኩ ነው ቢልም አጥፊዎች ደግሞ በንጹሐን ላይ በትራቸውን ማሳረፋቸውን አላቆሙም፡፡

ጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት እና ሌሎች የፀጥታ ኃይሎች በኢትዮጵያውያን ላይ እግራቸውን በሚያነሱ ጠላቶች ሁሉ እርምጃ ይወስዳል፡፡ ያለ እረፍት ይደክማል፣ ግን ዛሬም ሙሉ ለሙሉ ጠላቶቹን ማጥፋት አልቻለም፡፡ በጥላቻ የተገነባ ቡድን ተግባሩና ዓላማው ጥላቻ ብቻ ነው፡፡ ጥላቻ ልቡን ካጠፋው ቡድን ንጹሐንን ለማትረፍ ብስለት የተመላበት መንገድ መሄድ መልካም ነው፡፡

ማልቀስና መወቃቀስ ብቻ ንጹሐንን ከሞት አያድናቸውም፣ ማውገዝ ብቻም አያተርፋቸም፣ ንጹሐንን ከሞት ለማትረፍ እኔስ ምን አደረኩ? በምን መልኩ ኀላፊነቴን ተወጣሁ ? ማለት ግድ ይላል፡፡ የንጹሐን የደም ቦይ እንዲዘጋ፣ የግፍ ሞትም እንዲቀር በአንድነትና በብልሃት መነሳት፣ የጋራ ጠላትን በጋራ መቅጣት፣ ከፍ ሲልም ማጥፋት ያስፈልጋል፡፡ አንሁን በጋራ ለሚገድለን ጠላት በተናጠል አንወቃቀስ። አሁን የመወቃቀሻ ዘመን አይደለም፣ በአንድነት ቆሞ፣ በአንድነት ድል አድርጎ መኖርን ማረጋገጥ እንጂ፡፡
ጠላቶችን አጥፍቶ ንጹሐንን ለማትረፍ እንትጋ፣ ዜጎች የማይሳደዱበት፣ በቀያቸውና በመንደራቸው የሚኖሩባት፣ ሰላምና አንድነት የሰፈነባት ሀገር ትኖር ዘንድ ዛሬ እንነሳ፡፡ ክፉ ልምድ ክፉ ነው፣ በሁሉም በር እየደረሰ የሞት መርዶ ይነግራልና፡፡

በታርቆ ክንዴ (አሚኮ)
863 views16:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-06 20:48:59
በግለሰብ ቤት ተሸሽጎ የነበረ 23 የሞርተር ተተኳሽ ተያዘ።

ግንቦት 29-2014 የራያ ቆቦ ኮምዩኒኬሽን (ራቆኮ)

በደቡብ ወሎ ዞን አምባሰል ወረዳ ልዩ ስሙ 02 ቀበሌ ጢሳ አባሊማ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በግለሰብ ቤት ተሸሽጎ የነበረ 23 የሞርተር ተተኳሽ ተያዘ።

ከኀብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መሰረት በተደረገ ፍተሻ በአንድ ግለሰብ ቤት በመፀዳጃ ቤት ውስጥ 23 የሞርተር ተተኳሽ (ቅንቡላ) ተከዝኖ መገኘቱን የአምባሰል ወረዳ ሚሊሻ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

ተተኳሹ የተገኘበት ግለሰብም በህግ ቁጥጥር ሥር ውሎ ምርመራ እየተጣራበት እንደሚገኝ ተጠቁሟል። መረጃው የዞኑ ኮምዩኒኬሽን ነው።

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
920 views17:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-27 12:23:43 ራያ ቆቦ ሰላም ነው || አሁናዊ እንቅስቃሴውን ይመልከቱ


1.2K views09:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-26 11:01:36 የራያ ባህል በራያ ፈርጦች || @Dallol Media Center


1.3K views08:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-15 18:00:02 የከርሰ ምድር ውሀ ማውጫ ማሽን የሰራው ወጣት || @አማራ ሚድያ ማእከል amara media centre


1.2K views15:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ