Get Mystery Box with random crypto!

ከሲሳይ አየለ የምንማረው ምንድን ነው ድሬዳዋ ላይ ሲሳይ አየለን የማያውቅ የለም። አምባገነኖች | ሽፈራው የሶማው

ከሲሳይ አየለ የምንማረው ምንድን ነው

ድሬዳዋ ላይ ሲሳይ አየለን የማያውቅ የለም። አምባገነኖችን የሚታገለው፣ ጭቆናና መድሎን እምቢ የሚለውና የሚጠየፈው ሲሳይ ሳተናው !!

ሲሳይ በድሬዳዋ የተተከለውን አፓርታይድ የታገለ እና ወጣቱን ለማታገል የአቅሙን የሠራ ጀግና ነው። እነሲሳይ ተደራጅተው መብታቸውን ለማስከበር የወጣቶች አደረጃጀት ፈጥረው ሕጋዊ ሆነው ለመብታቸው ታግለዋል። አምባገነኑ ስርዓት ግን አልፈቀደላቸውም።
እንግዳያውስ ፖለቲካ ፓርቲ ሆነን እንታገል ብለው ፓርቲም መስርተዋል። ሆኖም የነሲሳይ ውሎና አዳር እሥርቤት ሆነ። ተስፋ የሚደረግበት ለውጥም የነሲሳይን የኢሕአዴግ ዘመን ያባሰ የግፍ መንገድ ሆነ።
አሁን እነሲሳይ የምስራቅ አማራ ፋኖን በመቀላቀል ትግላቸውን በሌላ አማራጭ ጀምረዋል መባሉን ሰማን።
ታዲያ በየክልሉ ያለን አማራዎች ከዚህ ምርጥ የአማራ ልጅ የምንማረው ምንድን ነው
የሐረር ልጆች ምን እንማራለን ? የናዝሬት ልጆች ከሲሳይ ምን እንማራለን? የሐዋሳ ልጆች ከሲሳይ ምን እንማራለን!? የጅማ ልጆች ምን እንማራለን!?
ጭቆና እና ጨቋኝ ብትሸሸውም ፣ ዝም ብትለውም አይተውህም!!
ማሰብ፣ መደራጀት፣ መሰልጠን፣ መመራመር፣ መታገል የዘመናችን ግዴታ ነው!! የእኛ ትውልድ እንዲህ እንዲኖር የታሪክ አንጓ ወስኖብናል ከመታገል በቀር አማራጭ የለንም!!

ድል ለአማራ !!

#AmharaStruggle
#Justice4Amhara
#AmharaGenocide