2022-01-30 09:29:09
*እራስን ማወቅና ማመን..*
በርካታ ሰዎች በተጨባጭ አላዋቂ ሆነው ሳለ «ጃሂል» ሲባሉ ይከፋቸዋል። ችግሩ ይህ ብቻ እይደለም። የዓሊም መገለጫ ሲሰጣቸው ደስ ይላቸዋል። ጃሂል ሲባሉ እንደሚከፋቸው ሁሉ ዓሊም ሲባሉም ቢከፋቸው ደግ ነበር።
አንድ ሸይኽ እንደሚሉት ከሆነ፤ መንገድ ላይ ሁለት ሰዎች በሆነ ነገር ሳይግባቡ ቀሩና አንዱ ሌላኛውን «ያ ጃሂል!» አለው። ከዛ ግብዳ ድንጋይ አንስቶ ሊጭንበት ሲል አንድ ሸይኽ ደረሱና «እንደ? ለምን? ተው እንጂ!» ብለው አስጣሉትና በምን እንደተጣሉ ሲጠይቋቸው «ጃሂል» ብሎ ሰደበኝ አለና አሰሞተ።
እርሳቸውም ጅህልናውን ለማረጋገጥ «አንተ እንደት "ጃሂል" ትለዋለህ? ቢያንስ "ሙናፊቅ" እንኳ አትለውም ነበር?» ሲሉ ጠየቁት ሰዳቢ የተባለውን ሰው።
የተሰደበውም «ሙናፊቅማ ቢለኝ አንድ ነገር ነበር (ይባል ነበር!)» አለና አላዋቂነቱን በራሱ ላይ መሰከረ።
እና ምን ለማለት ነው፦ አላዋቂ መሆን ያለ ነው። በዛው ላይ ግን መዘውተር የአንተ ምርጫ ነው። ብቻ ግን ከትናንትህ ዛሬህ በሆነ መልኩ ለውጥ ይኑረው።
ሁሌም የኳተረ ውሃ አትሁን። ተንቀሳቀስ! አላዋቂ መባል መጥላት ብቻ ሳይሆን በማወቅ አስወግደው። እዛው አላዋቂነት ላይ ተኝተህ ሳለህ አላዋቂ ስትባል አይክፋህ። ጭራሽ እንደ አዋቂ ስትደረግ ደግሞ ደስ አይበልህ።
መልካም ቀን
1.3K views06:29