Get Mystery Box with random crypto!

የዛሬ ማለፊያ ለክፉ ንግግሮች ሁሉ ከዝምታ የተሻለ መልስ ይኖር ይሆን!? ዝምታ የደስታ መባቻ ነው. | QesemAcademy

የዛሬ ማለፊያ
ለክፉ ንግግሮች ሁሉ ከዝምታ የተሻለ መልስ ይኖር ይሆን!? ዝምታ የደስታ መባቻ ነው.... ቅበላ!
ንግግር ጊዚያዊ ነው ፤ ዝምታ ግን ዘላለማዊ ነው። በድካም የተገኘ ዝምታ ነፃ ያወጣል። አብዝቶ አላውቅም ማለት ያላዋቂነት ምልክት ነው እንዴ? ወትሮም ከውሎህ ስትነጠል ማታ የምትተኛው ከአጋፋሪዎችህ ጋር ሳይሆን ከህሊናህ ጋር ነው። ለህሊናህ ታመን! ሰው ራሱን ከክፉ ስራ ይከለክል ዘንድ ህሊናውን ዳኛ አድርጎ ካልሾመ በቀር ሌላ ምንም ከልካይ የለውም።
ማንም በጣም ስለጮኸ በጣም አይሰማም። ሙያ በልብ ነው። ከመልካም ስራ ሁሉ ትልቁ ደግሞ ተደርጎ ያልተነገረ ስራ ነው። መልካም አድርገህ ዝም ማለት አማኝነትን ይሻል። ማቅለል ከባድ ነው! ማክበድ ግን ይቀላል። አንዳንዴ ሀሳቤ ሳይሆን ማሰቢያየ እንዳይሰረቅ ነው የምሰጋው።

“ልዩ ነኝ!" ብሎ ማሰብ ያለመብሰል ምልክት ነው። ልዩ ነኝ ብሎ በማሰብ ብቻ የሚመጣ ልዩነት የለም። “Fake people have an image to maintain, real people just don't care." ነኝ ብዬ ካሰብኩት የውሸት መስፈርት በላይ ያለው እውነት ምንድን ነው? ነው ጥያቄው። የህይወት ግቡ ድክመታችን ላይ መድረስ እንጅ ያላወቅነውን ነገር ማወቅ አይደለም። በምድር ምንም ነገር የኛ አይደለም። አሁን የጨበጥነው የመሰለንና የኛ ነው ብለን ያልነው ነገር አብሮን የተወለደ አይደለም፤ አብሮንም አያልፍም። ይሄ ሁሉ ያንተ ካልሆነ ምንስ ማጣት ትፈራለህ? የሰው ልጆች ግን አለማወቅን ሳይሆን ሰይጣንን ይፈራሉ። መፍራት ልማድን ነው። ሁልጊዜም ነው ብለን ከደመደምነው ነገር በላይ ጥልቅ ሌላ እውነት እንዳለ ሰርክ አንርሳ። የሰው ልጅ ከሚያውቀው የማያውቀው ነገር እንደሚበልጥ እስኪያምን ድረስ ወደ ቀጥተኛው መንገድ አይመጣም። ትልቁ ገንዘብ መገንዘብ ነው።
ጌታቸው

ቀለማት | ሁሉም ሰው የራሱ የሆነ መድመቂያ ቀለም አለው!

Join us : @qelemaat |  @qelemaat