Get Mystery Box with random crypto!

በከፍተኛ ውጤት አንደኛ የኾነው ተማሪ ሚኪያስ አዳነ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቹ በውጭ ሀገር የተሻለ ትም | QesemAcademy

በከፍተኛ ውጤት አንደኛ የኾነው ተማሪ ሚኪያስ አዳነ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቹ በውጭ ሀገር የተሻለ ትምህርት እንዲያገኝ እንዲያግዙት ጠየቀ፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ 666 ውጤት በማስመዝገብ አንደኛ የኾነው ሚኪያስ አዳነ ከተለያየ አቅጣጫ ድጋፍ ለማድረግ ፍላጎት ያላቸው ሰዎች እንዳገኙት ተናግሯል፡፡

ድጋፍ ለማድረግ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቹ ጥረት እያደረጉ በመኾኑ መደሰቱን የተናገረው ሚኪያስ አሁንም መረጃው ደርሶ አስፈላጊው ድጋፍ እንዲደረግለት እንደሚፈልግ አስረድቷል፡፡

ተማሪ ሚኪያስ አዳነ ማጥናት የሚፈልገው አስትሮ ፊዚክስ እንደኾነም ገልጿል፡፡ አስትሮ ፊዚክስ በሀገር ውስጥ በሁለተኛ ዲግሪ እንጅ በመጀመሪያ ዲግሪ እንደማይሰጥ የተናገረው ተማሪው ትምህርቱን ለመማር የውጭ የትምህርት አድል ማግኘት ግድ እንደሚለው ነው ያስገነዘበው፡፡

ውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እንዳገኙት የተናገረው ተማሪ ሚኪያስ አዳነ ውጭ ሀገር ወጥቶ እንዲማር የትምህርት እድል እንደሚያመቻቹለት እንደነገሩት አስረድቷል፡፡ ተማሪ ሚኪያስ አዳነ ወደ ውጭ ሄዶ የተሻለ ትምህርት አግኝቶ ሀገሩን ለማገልገል እንዲመለስ አስፈላጊውን እገዛ እንደሚፈልግ ነው የገለጸው፡፡

አስትሮ ፊዚክስ መማር ቢችል ወደ ሀገሩ ተመልሶ የራሱን ድርጅት በመክፈት ወገኖቹን መርዳት ምኞቱ እንደኾነም ከአሚኮ የኦን ላይን ሚዲያ ክፍል ጋር ባደረገው ቆይታ አስረድቷል፡፡

የአዳሪ ትምህርት ቤቱ እንደጠቀመው የተናገረው ተማሪው በዛ ያሉ አዳሪ ትምህርት ቤቶች እንደ ክልልም እንደ ሀገርም ቢኖሩ የተሻለ ተጠቃሚ እንደሚያደርጋቸው ተናግሯል፡፡

ተማሪዎች ከገንዘብ በላይ የተሻለ ትምህርት እንዲያገኙ እገዛ ቢደረግ ውጤት እንደሚኖረው ነው ያስረዳው።(አሚኮ) !
JOIN: @QesemAcademy
JOIN: @QesemAcademy