Get Mystery Box with random crypto!

ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች 2 nur.k _ ጊቢ እያለን ማደርያ ዶርማችን ውስጥ ፤ ሶስት | QesemAcademy

ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች 2
nur.k
_


ጊቢ እያለን ማደርያ ዶርማችን ውስጥ ፤ ሶስት ክርስትያን እና ሁለት ሙስሊሞች ነበር አብረን የምንኖረው። ወይ ፍቅር ወይ መተሣሠብ ወላሂ አጃኢብ ነው እኮ። ያ ጊዜ ባያልፍ(ትምህርቱን አላልኩም እሱማ ይለፍ የታባቱ)።

በጣም የሚገርመው የመጣንበት አከባቢ መራራቁ እና ብሔራችንም አንድ አለመሆኑ ነበር። አንደኛው ልጅ ከሸዋሮቢት ፣ ሌላው ከቦንጋ ፣ ሌላኛው ከአጋሮ(በቅርቡ ህይወቱ አልፏል)*! ፣ ከጎጃም ደምበጫ ሚባል አከባቢ እና እኔ ትውልዴ በደሌ እድገቴ አጋሮ የሆንኩ ነበርኩ።

እውነት ጫወታና ቁምነገራችን ሰው ሰው የሚሸት ነበር።እንከባበራለን።እንዋደዳለን። ሁላችንም በሚገባ ለመተዋወቅ ሞክረናል።ተዋውቀናልም።

ሰው ልጅ ሰው መሆን ከቻለ ምንም ነገር ለማድረግ ምንም አያግደውም። ከተራራው ጀርባ ለመመልከት ሰው መሆን በቂ ነው ፤ ባለህበት ቆመህ አታላዝን ተራራው ላይ ውጣና አሻግረህ ተመልከት።

በርህን ዘግተህ የሌባ መጫወቻ አትሁን።በርህን ክፈት። በተከፈተ በር እንግዳ እንጂ ሌባ አይገባም። በተዘጋ በር ሌባ እንጂ እንግዳ አይገባም።

ልብህን ክፈት። እንግዳ ሀሣብ ተቀበል። ልብህን ዘግተኸው የሰነበተ ሀሣብ ዕስረኛ አትሁን።የክፋት ምንጩ ልብ ተዘግቶ ጭንቅላት መሪ መሆኑ ነው።

ምቀኝነትና ሐሜት ፣ ተንኮል፣ ደባና አስመሣይነትን አውልቀህ ጣላቸው። ሃሣብless ማንነትህን በማንበብ ገንባው። ጎጠኝነት ሰዋዊ ባህሪ አይደለምና ሰዋዊነትን አስሰህ የግል ርስትህ አድርገው።

በጊቢ ህይወት አትጥበብ። ብሄርና እምነት አጥር ሆነው እንዳይከልሉህ። ከምነትም ከብሄርም በፊት ሰውነት ይቀድማል። አጠገብህ ያለው ወንድምህ ያው ያንተ ቢጤ ሰው ነው። እዘንለት ፣ውደደው ፣ አክብረው።

እመክርሃለሁ!! የትም ሁን ከማንም ጋር ብርሃንህን በጨለማ አትለውጥ! ዘረኝነት ነው ጨለማ!!!

nur.ክ

ሌሎች ለተማሪዎች ይጠቅማሉ የምትሉትን ፅሁፎች በ : @Qesem_support ላይ አድርሱን



ከHigh school እስከ Campus አበረናችሁ ነን !
SHARE SHARE
╔══════════════
JOIN: @QesemAcademy
JOIN: @QesemAcademy
╚══════════════