Get Mystery Box with random crypto!

ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች። Nur.k እኔ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ነው የተማርኩት። ጊቢው በወቅቱ እጅግ አ | QesemAcademy

ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች።
Nur.k
እኔ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ነው የተማርኩት። ጊቢው በወቅቱ እጅግ አስቀያሚ ነበር። በዛ ላይ ሙቀቱ። ደግሞ የአስተማሪዎች ጢባር ሁሉን ነገር እንድጠላ አድርጎኝ ነበር። የመጀመርያው ሴሚስቴር እጅግ እጅግ ፈታኝ ጊዜ ነው። ያው መታገስ ስለነበረብኝ ታገስኩኝ። ሁሉም ተለመደ። ወዳጅ አፈራሁ። በለው እንደውም ዕረፍት ስሄድ የጊቢ ህይወት ይናፍቀኝ ጀመረ።

ጊቢ ብጥብጡ ሁሉ ይናፍቅሃል። እኔ ያው የተለያዩ ዴይዎችን(day's) ብዙ የማክበር ፍላጎቶች ስላልነበሩኝ እንቅስቃሴዎቼ የተገደቡ ነበሩ ፣ ቢሆንም አሰልቺ ሳይሆን አስደሳች ጊዜ ነበረኝ።
ሙሌ(ቦንጋ) ማሜ (ሸዋሮቢት) አንለይ(አጋሮ፣ በህይወት የለም) የዶርሜ ልጆች አልረሳችሁም።

ብቻ በዚህም በዚያም ተመርቀን ወጣን።አለን አሁንም።
___
ወንድሜ -: ያዝ ይህን ምክሬን

ጊቢ ስትሄድ አስተውል!! የመጀመርያው ወር ወይም ሴሚስቴር ትንሽ ይከብድሃል። ምታውቀውን ሁሉ ትተህ ነው ምትሄደው። ጓደኛ እስክታፈራ መታገስ አለብህ።

ለውሳኔ እንዳትቾክል። ሁሉም ሲለመድ ውይ ለዚሁ ነው ትላለህ። ወላሂ ተረጋግተህ ነገራትን እይ።
ሁልጊዜ መርሳት የሌለብህ ነገር አለ። እንኳን አዲስ ሀገር አዲስ ሰፈር ስትሄድ እስክትለምድ ጊዜ ይወስዳል።

አንተ መሠናክሎችን ስታስብ ግሬድ ከመስራት እንዳትዘናጋ። የመጀመርያ ነጥብህ ወሳኝ ነው።
በመዘናጋትህ ውስጥ ዕድሎችህን እንዳታባክን። ዕድል አንዴ ነው ፣ ካመለጠህ ወዲያ ብትነቃ የሚመለስ ነገር የለም።

አውቃለሁ ብዙ ጓደኛ ፣ ብዙ ወዳጅ እና ምርጥ ቤተሰቦችህን ትተህ እየሄድክ ነው። ይህ ይከብዳል። ቢሆንም ሁሉም ይለመዳል። መንፈስህን ጠንካራ አድርገው። አሻግረህ ተመልከት። ስለ ወሳኙ ግብህ፣ ስለ መድረሻህ እይ። ተምረህ ተመርቀህ ስላለው ነገር አስብ። በመመረቅህ የናትህንና የአባትህን የደስታ እምባ አሻግረህ ተመልከት።

በጊዜ ሂደት ያንተ ያልነበረ ያንተ ይሆናል። የማይለመደው ይለመዳል። የሚያስከፋ የነበረው አዝናኝ ሆኖ ታገኘዋለህ። ብቻ ተረጋግተህ ነገራትን አድርግ። በህይወት ውስጥ ቋሚ ነገር ለውጥ ብቻ ነው። ሁሉም ይለወጣል። የማይለወጠው ለውጥ ብቻ ነው። ለሚለወጥ እና አንዱ አንዱን መተካቱ ላይቀር በአንዱ ነገር ላይ ስትደበር በመጪው ህይወትህ ዋጋ እንዳትከፍል።

በዚህ ሁሉም ያንተ መሠል ፍሬሾች ድባቴ(ድብርት) ውስጥ በሚሆኑበት ጊዜ አንተ ነቃ በልና ውጤት ለመስራት ተነቃቃ። ዛሬ ዋጋ ከፍለህ የሰራኸው ጥሩ ውጤት ቀጣዩ ጉዞህ በሳቅ የታጀበ እንዲሆን ያደርገዋል።

አጥብቄ መክርሃለሁ !!በፍፁም ሁለት ነገሮችን አትርሳ የትም ፣ ከማንም ጋር ሁን ሰላትና ቤተሰቦችህን ዝያራ!!

ክፍል ሁለት ይቀጥላል......

ከHigh school እስከ Campus አበረናችሁ ነን !
SHARE SHARE
╔══════════════
JOIN: @QesemAcademy
JOIN: @QesemAcademy
╚══════════════