Get Mystery Box with random crypto!

ክረምታችሁን እንዴት እያሳለፋችሁት ነው ክረምት ላይ የእረፍት ጊዜዬን እንዴት ባሳልፈው ላተ | ቀለማት

ክረምታችሁን እንዴት እያሳለፋችሁት ነው

ክረምት ላይ የእረፍት ጊዜዬን እንዴት ባሳልፈው ላተርፍበት እችላለው

Written by: ቻLu
Reviewed by: Getachew


ብዙዎቻችን እድሚያችን እየገፋ ሲሄድ እንደተሸወድን የሚገባን ፣ ክረምት ላይ ያኔ ብናረጋቸው ኖሮ የኑሯችን ስንቅ ይሆኑን የነበሩ ተግባራት ብለን ልናስባቸው የምንችላቸው አሁን ላይ ብናደርጋቸው ጥሩ ትዝታ ህይወታችን ላይ ደርበውልን የሚያልፉ ሰበዞች

ደስ ያላችሁን ምረጡ እና ወደ ተግባር ግቡ እመኑን፣ የኋላ ሗላ በምርጫችሁ ትኮራላችሁ!

የክረምት ወቅት ለብዙዎቻችን ያሳለፍነውን ዓመት ጊዜ ገዝተንና ትዝታ ተዝተን እንዴት እንዳለፈ እና እንዳሳለፍነው ወደኋላ መለስ ብለን የምንቃኝበት፣ የተለየ የእረፍት ጊዜ የምናሳልፍትበት፣ ሩጫና ውድድር ከበዛበት ዓለም ትንሽ ፋታ አግኝተን ከራሳችን ጋር የምንሆንበት፥ የምናወራበት፣ ለወደፊታችንም ወይም ለሚመጣው ዓመት የምንዘጋጅበት ደስ የሚል ወቅት ነው! ተማሪዎች ማጠናከሪያ ትምህርት ይማራሉ፤ መጽሐፍ ያነባሉ፣ ከጓደዶቻቸው ጋር ጊዜ ያሳልፉሉ (በተለይ የግቢ ተማሪዎች ሌላ ጊቢ ካሉ የቀድሞ የhigh school ጀለሶቻቸው ጋር ተገናኝተው የፈረደበትን አስተማሪ ሲጨፈጭፉ (F የጠጡበት ኮርስ ካለማ አይጣል ነው፤ አይምሩትም )፣ ግቢ ውስጥ ያለችውን crushቸውን ልክ ፍቅረኛቸው እንደሆነ/ች አድርገው ሳክሳቸውን ሲቶኩ )፣ ሰራተኞች የትምህርት ደርጃቸውን ከፍ ለማረግ የክረምት ትምህርት ይማራሉ ፣ ብዙዎች ዘመድ ጥየቃ ብለው ከተሜዎች ወደ ገጠር ፣ የገጠር ተወላጆች ደግሞ ወደ ከተሜዎች ይመጣሉ...... በጣም ብዙ
እናንተስ ዘንድሮ በዚህ ክረምት ምን አሰባችሁ? የሚቀጥሉት ዝርዝሮች ሊጠቅሟችሁ ከቻሉ ብለን አዘጋጀንላችሁ! መልካም ንባብ

መንፈሳዊ ትምህርቶችን መማር(ነገረ መለኮት፣ መጽሐፍ ቅዱስ ማንበብ)

ለነፍስ ምግቧ የእግዜብሔር ቃል ነው እንዲል መጽሐፍ የቅዱሳት መጻሕፍት ጥናቶች መርሃ ግብር ውስጥ መሳተፍ፣ መዝሙር ማጥናት፣ የአብነት ትምህርት ቤቶች በክረምት የሚሰጧቸው ትምህርቶች ካሉ በየ ቤተ-ክርስቲያናችሁ አጥቢያ ፈልጋችሁ መመዝገብ እና የእግዚአብሔርን ቃል መማር አንዱ በክረምት ልታረጉት የምትችሉት ነገር ነው።


ልዩ ልዩ የኪነ- ጥበብ እና የግብረ ገብ ስልጠናዎችን መወሰድ


እንዲህ አይነት ስልጠናዎች ለትምህርት እና ለሞያ ህይወታችሁ ላይጠቅሟችሁ ይችላሉ ፣ ነገር ግን ራሳችሁን በተለየ መንገድ የምተገልጹበትን እና በራስ መተማመናችሁን ልታሳድጉበት የምትችሉባቸው አማራጮች ናቸው። ደግሞም ሁሉም ለሞያችሁም ሊጠቅሟችሁ ይችላሉ። ለምሳሌ እንደ በገና ያሉ የዝማሬ መሳሪያዎችን መማር ፣ የምግብ አሰራር ሙያ መማር ፣ የጓሮ አትልክታችሁን እንዲሁም ግቢያችሁን ጋርደኒንግ ማስዋብ ፣ የግጥም ፣ የስነ ፅሁፍ ፣ የትወና እና ሌሎች መሰል ክህሎቶችን እንደየ ምርጫችሁ መማር እንዲሁም መሳተፍ እንደ ቆንጆ አማራጭ ልትወስዱት ትችላላችሁ።

ትምህርታዊ እና ሙያዊ ስልጠናዎችን መውሰድ


ይህንን ከ ግብረ ገብ ስልጠናዎች ለይቼ ያወጣሁት ከዛኛው የተለየ ዓላማ ያለው ይዘቱም የተለየ ነው ብዬ ስላሰብኩ ነው። በተለይ በሚቀጥለው ዓመት የትምህርት እና የስራ ህይወታችሁ ላይ መሻሻልን ማየት ከወደዳችሁ ፣ እንደያላችበት Department እና የትምህርት ደረጃ ሊጠቅሟችሁ የሚችሉ የአጭር ጊዜያት ስልጠናዎችን መውሰድ ፣ ክፍያ ያለውም የሌለውም Internship መስራት፣ ባላችሁበት የትምህርት field Volunteer ማድረግ፣ በጣም excel ማረግ የምትፈልጉትን የትምህርት በእውቀትም በልምድም እንድትበስሉበት በሙያው ዘርፍ ያሉ ሰዎችን በስልክም በአካልም ማውራት፣ እውቀታችሁ advanced እንዲሆን ከፈለጋችሁ ደግሞ ለፈተና ካጠናችሁበት መንገድ ወጥታችሁ ገጽ በገጽ ጊዜ ሰጥታችሁ ማንበብ ሌላኛው ክረምታችሁን ውብ የምታረጉበት አማራጭ ነው።


የማህበረሰብ አገልግሎት ተሳትፎ ማድረግ

ሰዎችን መርዳት እጅግ ከማስደቱም በላይ በእንዲህ አይነት የማህበረሰብ ግብረ ሰናይ ተሳትፎች ላይ መሳተፋችሁ ፣ ሰዎችን በማገልገል ውስጥ ያለውን በጎ የህይወት ትርጉም የምታጣጥሙበት ፣ ከተለያዩ አዳዲስ ሰዎች ጋር የምትተዋወቁበት ፣ ለተለየ የስራ እና የትምህርት እድል የምትታጩበት ፣ ከዚያም አልፎ ደግሞ ተገቢውን እውቅና እና ሽልማት ልታገኙበት የምትችሉበት መድረክ ነው። ልብ በሉ ፣ አሁን ላይ ያሉ የሰራ ዕድሎችን ለማግኘት ፣ ከውጭም ሆነ ከሃገር ውስጥ ነጻ የትምህርት እድል ለማግኘት ፣ የተለያዩ ተቋማት ላይ ለተለያዩ የስራ መደቦች ላይ ለመሾም እንዲህ አይነት ተሳትፎዎች ላይ መኖራችሁ የራሱ የሆነ ድርሻ አለው። የበጎ አድራጎት ተሳትፎዎች ከማንም ምንም ሳትጠብቁ ለነፍሳችሁ ሃሴት የምተሰሩዋቸው መልካም ሰራዎች ቢሆኑም ፣ እንዲህም አይነት እድሎች እንዳሉ ማውቁ አይከፋም።

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማረግ

የሰውነት ከብደታችሁን መጨመር አልያም መቀነስ የምትፈልጉ ፣ የሰውነት ቁመናችሁን በማስተካከል ሸንቀጥቀጥ ማለት ለምትፈለጉ ፣ ሰውነታችሁ በቂ እረፍት እየሰጣችሁ ፍርጥምጥም ለማለት ክረምት አመቺ ጊዜ ነው። በየ አካባቢያችሁ የጂም ፣ ካራቴ ፣ ቴክዋንዶ እና የስፖርት ቡድን ውስጥ በመግባት መስራት፣ ቤት ውስጥ ወይም በአካባቢያችሁ ባለ ነገር መስራት ትችላላችሁ። እንደየ ምርጫችሁ እና አቅማችሁ።

ቤተሰብ፣ ዘመድ ጥየቃ እና ሀገር መጎብኘት

እንዲሁ ሲታይ ቀላል ሊመስል ይችላል፤... የናፈቋችሁ ቤተሰቦቻችሁ ጋር አብሮ ማሳለፍ፣ ዘመዶቻችሁን መጠየቅ ግንኙነታችሁንም ከማስቀጠል ባለፈ ሆቴል Book እንደማስደረግ በሉት ፣ ምንም ባልቸገራችሁ እና ባላጣችሁበት ጊዜ የጀመራችሁት ዝምድና ፣ ኋላ ላይ ከችግር ያወጣችኋል ፣ ድንገት ሩቅ አገር ለ ስራ ወይ ለትምህርት መሄድ ቢኖርባችሁ ፣ ለትንሽ ቀናት ሰፈር መቀየር ቢኖርባችሁ ፣ በቃ ዘና ብላችሁ የምትቆዩበት ፣የምታድሩበት ቦታ አገኛችሁ ማለት አደል ፣ ሊያውም ባይተዋር ሳትሆኑ ፣ ያ ብቻ አደለም ሃገሩን እና ሰፈሩን መውጫ መውረጃውንም ለማወቅ ይጠቅማችኋል።

ለስለስ ያሉ ሙዚቃዎችን መስማት፣ ከዚህ ቀደም እንሰማቸው፣ እንከታተላቸው የነበሩ የሬዲዮ ወይም የቲቪ ፕሮግራሞች ግቢ ከገባን በኋላ ግን ጊዜ በማጣት ወይም በሌላ ምክንያት መስማት፣ መከታተል አቋርጠን ከነበር እንደ አዲስ መከታተል፣ መስማት መጀመር ጥሩ ስሜት ሊፈጥርብን ይችላል። እንዲሁም እንደ አዲስ ሰምተን የእኛን ብስለት ልንለካበት እንችላለን። ይሄም ጥሩ የክረምት ጊዜ ማሳለፊያ አማራጭ ነው።

እናንተም ጨምሩበት፤ የተለየ ልምድ ካላችሁ ደግሞ አጋሩን። ክረምታችሁ የእረፍት ጊዜ የሆነላችሁ ተማሪዎች መልካም የክረምት ጊዜ እንድታሳልፉ ምኞታችን ነው

ቻLu | ጌታቸው- Upcoming Psychologist at AAU

ለማት | ሁሉም ሰው የራሱ የሆነ መድመቂያ ቀለም አለው!

JOIN US NOW : @qelemaat |  @qelemaat