Get Mystery Box with random crypto!

የስኬት ቁልፎች (The key to success)- ክፍል አንድ ስኬት አንድ የታቀደ እቅድ(ግብ) | ቀለማት

የስኬት ቁልፎች (The key to success)- ክፍል አንድ

ስኬት አንድ የታቀደ እቅድ(ግብ)በትክክል መፈፀም ማለት ነው፡፡ ከዚህ ዐረፍተ ነገረ መረዳት የምችለው ነገር ቢኖር ከስኬት በፊት ምንጊዜም የታቀደ ግብ ሊኖር እንደሚገባ ነው፡፡ ስኬት ግብ ለሚያቀምጡ ብቻ የተሠጠች ነች ማለት ነው፡፡ ለዚህም ነው “ If you fail to plan, you are planning to fail’ የሚሉት ምሁራን፡፡ ከስኬት ቁልፎች መካከል አንዱ ግብ ማስቀመጥ(Goal setting) ሲሆን ሌሎች ደግሞ የዉስጥ መነሳሳት(Motivation) እና ጽናት (persistence) ናቸዉ::

1. ግብ ማስቀመጥ ( Goal setting)

ማንኛውም ስኬታማ መሆን የሚፈልግ ሰው እቅድ ማቀድ እንዳለበት ከተስማማን እቅዱስ ምን ምን ማሟላት አለባቸው? የሚለውን ጥያቄ ማንሳቱ ጠቃሚ ነዉ፡፡ ማንኛውም ዓይነት እቅድ “SMART ” መሆን አለበት:: ትርጓሜውም እንደሚከተለው ይተነተናል፡፡
S- Specific ( ግልጽና የተወሠነ)
M-Measurable (የሚለካ)
A- Achievable (ሊሳካ የሚችል)
R- Realistic (እውን ሊሆነ የሚችል)
T- Time framed ( በጊዜ የተወሰነ)

i). specific ( ግልጽና የተወሠነ)

እቅድ (ግብ) በግልፅ የሚታወቅ መሆን ይገባዋል፡፡ ግልጽነት የሚጎድለዉ እቅድ እንዴት እንደምናሳካዉ ለማወቅ ከባድ ነዉ::ብዙ ሰዎች ግባቸውን ሲጠየቁ “የተሻለ” የምትለዋን ቃል በማስቀደም ሌሎችን ፍላጎታቸውን ያስከትላሉ፡፡ የተሻለ ትምህርት፣ የተሻለ ቤት፣ የተሻለ ገቢ ፣የተሻለ የስልጣን ቦታ ወዘተ ይላሉ፡፡ ይህ አይነቱ ግብ ግልጽነትና ዉሱንነት ይጎድለዋል፡፡ ለስኬታማነትም ሊያበቃን አይችልም፡፡ እንደነዚህ አይነት ሰዎች ብዙ ጊዜያቸው የሚያጠፉት ከአንዱ አንዱ በመንከራተትና በመወዛገብ ነው፡ የተረጋጋ ህይወት ለእነርሱ ተረት ነው፡፡ የተሻለ ገቢ ለማግኜት የሚያቅድ ሰውና የ3000 ብር ደመወዘኛ የ3200 ብር ደመወዝ ያለው የስራ ማስታወቂያ ከወጣ ያለ ጥርጥር ስራውን ይቀይራል፡፡ ምክንያቱም እቅዱ የተሻለ ማግኜት ነውና፡፡ ለዚህም ነው እንዳንድ ሰዎች ከእድሜያቸው በላይ መስሪያ ቤት ሲቀያይሩ የሚኖሩት፡፡ በተመሳሳይ የተሻለ ትምህርት የሚፈልግና ዲግሪ ያለዉ ሰው በአጋጣሚ መንገድ ጠፍቶበት በዩኒቨርሲቲ በር ሲያለፍ የድህረ-ምረቃ ትምህርት ማስታወቂያ ቢያነብ ትምህርቱ ይጥቀመውም አይጥቀመውም ዘሎ ገብቶ ይመዘገባል፡፡ ተምሮ ሲወጣ ግን በህይወቱ ምንም ዋጋ ላይጨምር ይችላል፡፡ በአጠቃላይ ግብ በግልጽ ተወስኖ የተቀመጠ መሆን ይገባዋል፡፡ የተሻለ ገቢ በማለት ፈንታ በወር ማግኜት የሚፈልገውን የገንዘብ መጠን ቢያቀምጥ ይመረጣል፡፡ የተሻለ ትምህርት በማለት ፈንታም ዲግሪ፣ ማስተርስወይም ፒ.ኤች. ዲ እና የመሣሰሉትን ቢያቀምጥ ይመረጣል፡፡

ii). Measurable (የሚለካ)

ሌላው ግብ ስናስቅምጥ ማስተዋል የሚገባን ነገር ግባችን የሚለካ መሆን አለበት፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰዎችን የሚረዳ ድርጂት ለማቋቋም ያቀደ ሰው ምን ያህል ሰዎችን እንደሚረዳ በግልፅ ማስቀመጥ አለበት፡፡ ቤት ለመሰራት ያቀደም ሰው ቢሆን የቤቱን ስፋት አይነት እና የመሳሰሉትን በግልፅ ማስቀመጥ አለበት፡፡ አለበለዚያ አንድ ሰው ብቻ የምታሰገባ ቤት ቢሰራም ቤት ቤት ነውና እቅዱን እዳሳሣካ ሊቆጥረው ይችላል፡፡ በመሆኑም ማንኛውም ግብ የሚያስቀምጥ ሰው ግቡ የሚለካ መሆን አለበት፡፡

iii). Achievable (ሊሳካ የሚችል)

አሁንም ግብ ስናስቀምጥ ግባችን ሊሳካ የሚል መሆኑን ማረጋገጥ አለብን፡፡ ይህን በምሳሌ ለማስረዳትም አንድ የ7ኛ ክፍል ተማሪ ዛሬ ላይ ሆኖ የዛሬ 10 ዓመት ፒ.ኤች.ዲ ዲግሪዉን እንደሚይዝ ቢያቅድ እቅዱ ሊሳካ የሚችል አይደለም፡፡ ምክንያቱም ስርዓተ-ትምህርቱ ከ7ኛ ክፍል ወደ ፒ.ኤች.ዲ. ዲግሪ በ10 ዓመት ያጠናቅቅ ዘንድ አይፈቅድለትም፡፡ በኢትዮጵያ ስርዓተ ትምህርት መሠረት ከ7ኛ ክፍል ፒ.ኤች.ዲ. ዲግሪ ለመያዝ ቢያንስ 14 ዓመታትን ይፈጃል፡፡ ስለሆነም ይህን እቅድ ያቀደ ሠው እቅዱን ሊያሳካ አይችልም፡፡ ስለዚህም ሁጊዜ ግብ ስናስቀምጥ ሊሳካ የሚችል መሆኑንና አለመሆኑን ማሠብ ይኖርብናል፡፡

iv). Realistic (እውን ሊሆን የሚችል)

አራተኛው ግብ ሊያካትተው የሚባው መስፈርት ደግሞ እውን ሊሆን የሚችል መሆኑን ነው፡፡ ይህ ቀጥታ ከተፈጥሮ ጋር የሚያያዝና ልንቀይራቸው የማንችላቸውን ነገሮች ማቀድ እንደሌለብን የሚያስገነዝብ ነው፡፡ “change the changeable, accept the unchangeable”
እንዲሉ ምሁራን በተፈጥሮ እውን ሊሆን የማይችልን ነገር ማቀድ ድካሙ ነው ትርፉ፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው “የዛሬ ዓመት መልዓክ ለመሆን ቢያቅድ እቅዱ እቅድ መሆኑ ቀርቶ ቅዠት ነው የሚሆነው፡፡ ስለሆነም ግባችን በገሃዱ አለም እውን ሊሆን የሚች መሆን አለበት፡

v). Time framed ( በጊዜ የተወሰነ)

የመጨረሻውና ግብ ስናስቀምጥ ማካተት ያለብን ነገር ግባችን በጊዜ-የተወሰነ መሆኑን ማረጋገጥ ነው፡፡ ይህ ችግር ከሌሎች ማሟላት ከሚገቡን ነገሮች የበለጠ ጎልቶ የሚታይ ነው፡፡ “መኪና ሳልገዛማ አልሞትም” ሲል የምንሠማው ሰው መኪና መቼ እንደሚገዛ ግን አያውቀውም፡፡ የዛሬ 20 አመትም ይህንን ሲደግመው እናሠማለን፡፡ ግብ ስናስቀምጥ ምን ጊዜም በጊዜ የተወሰነ መሆን ይኖርበታል፡፡ አለበለዚያ ነገ እሠረዋለሁ እያልን እድሜያችንን መፍጀታችን ነዉ፡፡

Via unknown source

ቀለማት - ሁሉም ሰው የራሱ የሆነ መድመቂያ ቀለም አለው።

Join us @qelemaat/ @qelemaat