Get Mystery Box with random crypto!

' ባነበበ አይደለም በገባው ነው' ይባላል ፣ ግን የምር እንደዛ ነው ወይ? ሲጀመር ማንበብ ም | ቀለማት

" ባነበበ አይደለም በገባው ነው" ይባላል ፣ ግን የምር እንደዛ ነው ወይ?

ሲጀመር ማንበብ ምን ይጥቅማል እውነት እኮ ነው ፣ የተማረ የት ደረሰ በቃ ማወቅ ማለት ንድፈ ሃሳብን ማራቀቅ ማለት ነው

በእውነት የትምህርት ስርዓቱ አክትሞለታል በቃ የምንማረው ትምህርት ትርኪ ምርኪ ነው ማለት ነው?

ኢትዮጵያ ሃገራችን እውነትም ሙያችንን እና ክህሎታችንን እንዲናሳድግ የሚያስችል እድሎች የላትም ወይ? ያለን አማራጭ ሀገር ለቆ መጥፋት ነው?

አንዳንድ ሰዎች "ባነበበ አደለም ፣ በገባው ነው።" ሲሉ ሰማለሁ ግን ስናነብ የግድ ሊገባን ይጠበቃል ወይ ? ዶ/ር ዳንኤል የሚባሉ መምህሬ "ግራ ከገባችሁ አስተምሬያለሁ ማለት ነው" ሲሉ ትዝ ይለኛል። ለተከታታይ ዓመታት ባነበብን እና ባወቅን ቁጥር መጨረሻ ላይ የሚገባን ነገር ግራ መጋባታችን ነው ፣ ግራ መጋባታችንም ይመስለኛል ለተሻለ ነገ እንድንተጋ የሚያረገን ፣ የሆነ ያልፈታነው እንቆቅልሽ እንዳለ ማወቃችን ዘና ብለን የተደላደለ ህይወት እንድንኖር አያስችለንም ፣ አጋጣሚውን ሁሉ እየጠበቀ በአይምሯችንን ይመላለሳል ፣ ነገ ፈተና እንዳለ እያወቃችሁ ዛሬን ሰላማዊ እንቅልፍ እንደመተኛት ቁጠሩት ፣ በደንብ እስካልተዘጋጃችሁ ድረስ "አንዲት ወረቀት ህይወቴን አትወስንም " ብላችሁ ለሽ ለማለት ብትሞክሩ እራሱ የሆነ ቅር የሚላችሁ ስሜት አለ ፣ ሰላም የማይሰጥ ፣ በጣም የሚረብሽ። ታዲያ አኗኗራችንን ለማሻሻል የሚኖረን ተነስሽነት የሚጀመረውም ከዚህ ይመስለኛል።

ድንገት ስትባንኑ ፣ ብዙ ያለተፈቱ ችግሮች በኑሯችሁ ላይ ፣ በአካባቢያችሁ እና በአገራችሁ ላይ ታያላችሁ። መማር ማለት ችግር የማይመስሉ ግን ብዙ መፈታት ያለባቸው ተግዳሮቶች እንዳሉ ማውቅንም ያካትታል። ምክንያቱም ስትማሩ የትኛው ትክክል የትኛው ደግሞ ስህተት ነው የሚለውን ለማውቅ እድል ስለሚሰጣችሁ ፣ ከምታዩት እያንዳንዱ አጋጣሚ ጋር እየሄዳችሁ ትላተማላችሁ። ይሄ እንዲህ ቢሆን ፣ ያ እንዲያ ቢሆን ማለት ትጀምራላችሁ ፣ ይሄን እንዲህ ቢያስተካክሉት ያንን ደግሞ ቢያሻሽሉት ማለት ስትጀመሩ ፣ ወስጣችሁ በእምቅ ሃይል መሞላት ይጀምራል ፣ ክዚህ በኋላ ግን የሚትኖሩት ዓለም የተለየ ነው ፣ እንኳን ወደ ስራው ዓለም በሰላም መጣችሁ!

አሁን የሆነ ማስተካከል የምትፈልጉት ነገር እንዳለ አምናችሁ ፣ ወደ ተግባር ገብታችኋል ፣ ሊሰራ የማይወድ አይብላ እንደሚል ቃሉ ፣ እናንተም ማስተካል ለምትፈልጉት ነገር ሁሉ ለመልፋት ስትወስኑ የምርም እናንተ ማስተካክል የምትፈልጉትን ነገር በቅጡም ቢሆን ያስተካከሉ ፣ እናንተ መስራት የምትፈልጉትን የሰሩ ፣ እናንተ መፅሃፍ እንደምትፈልጉት የፃፉ ሰዎችን መምህራችሁ ማረግ ትጀምራላችሁ ፣ በአካል ካሉ በአካል ስታወሯቸው ፣ መፅሃፋቸውን ስታነቡ ፣ ታሪካቸውን ስትሰሙ ፣ ቀስ በቀስ ሁሉም እየገባችሁ ያለ ይመስላችሗል። እና "የህወቴን ትርጉም አገኘሁት " ማለት ስትጀምሩ አንድ ያልታሰበ ተራራ ከፊታችሁ መቶ ይደቀናል። ብዙ ሰዎች እስከዚህ ድረስ ብቻ ነው መንገዳቸውን የሚመጡት ፣ ምክንያቱም ከዚህ በኋላ ያለው ፣ እራስን ማስተማር ፣ ዝቅ ብሎ መጠየቅ ፣ ሞክሮ መሳሳት ፣ ከሚጠበቅብን በላይ መስራት፣ ክህሎትን ማሳደግ ፣ እያለ የሚቀጥል ለምውጣት እንኳን የሚከብድ አድካሚ ተራራ።

አሁን "ያልታሰብ እንጀራ ይስጥህ " ተብዬ የተመረኩት ምርቃት ምናለ ቢሰራልኝ ብላችሁ ትመኛላችሁ ፣ ምክንያቱም ነገሩን በሰከነ ልቦና ስታዩት የሆነ ትልቅ ነገር እስካላረጋችሁ ድረስ ያስባችሁት ለውጥ እይመጣም፣ እግዚአብሔር ያውቃል ብላችሁ ነገሩን ልትተውት ስትሉ ደግሞ ፣ የናንተ ፍቃድ እስከምን ድረስ እንደሆነ ጥያቄ ይሆንባችኋል ።

እየተማራችሁት ያላችሁት degree የሂደቱ አንድ አካል እንጂ ብቸኛ አካል እንዳልሆነ ስታውቁ ፣ የተለያዩ ስልጠናዎች ላይ ተጨማሪ ወጪ ማውጣት እንዳለባችሁ ሲገባችሁ ፣ እድሎችን ለመፍጠር ከመስሪያ ቤት መስሪያ ቤት መንቃቃት ሊኖርባችሁ እንደሆነ ስትረዱ ፣ እንቅልፋችሁን ሰውታችሁ ተጨማሪ ሰዓት በስራ እና በንባብ ማሳለፍ እንዳለባችሁ ውስጣችሁ ሲያምንበት ፣ የተለያዩ እድሎችን እና ማስታወቂያዎችን አንፍንፋችሁ መፈለግ እንዳለባችሁ ስትረዱ ፣ የጀመራችሁት ጉዞ ከብዙ ብጥቂቱ እንደሆነ ይገባችኋል። ከዚህም በላይ ሌላ ትልቅ ነገር ማድረግ ይኖርብኝ ይሆን ብላችሁ ራሳችሁን በየቀኑ ትጠይቃላችሁ! ምክንያቱም አሁን Law of attraction በሚባል የሃሳብ ፈንጠዚያ ውስጥ አደለም ያላችሁት ፣ ከናንተ በሚከፈል ጥረት ፣ በፈጣሪም ፍቃድ ፣ ማድረግ ያለባችሁን ነገር ሁሉ በተሻላችሁ መጠን እያረጋችሁ እንደሆነ ስታስቡ ፣ ሁል ጊዜም ለለውጥ ቦታ ሰው መሆን ትጅምራላችሁ ፣ ምክንያቱም አሁን ከሃጋራችሁ መሰደድ ብቸኛ አማራጫችሁ አይሆንም ፣ ሃገራችሁ ላይ ያሉ እድሎችን በሙሉ ለማግኘት ተወዳዳሪ ሰው ሆናችኋል እና። ለእንዲህ እያረጋችሁ ላላችሁ ወጣቶች በሙሉ አክብሮቴን እና አድናቆቴን ለመግለፅ ወዳለሁ።

ቻLu - በ ኢትዮጵያ የሳይኮሎጂ ባለሞያዎች ማህበር እና በ American Psychological Association በተለያዩ የስልጠና ፕሮግራሞች Certified የሆነ እጩ የስነ- ልቦና ባለሙያ

ለማት | ሁሉም ሰው የራሱ የሆነ መድመቂያ ቀለም አለው!

JJOIN US NOW : @qelemaat |  @qelemaat