Get Mystery Box with random crypto!

ስራ የሌለው እምነት የሞተ ነው። ይህ ማለት ታዲያ ደህንነትን ለማግኘት መስራት አለብህ ማለት ነው | Pure_Christianity

ስራ የሌለው እምነት የሞተ ነው። ይህ ማለት ታዲያ ደህንነትን ለማግኘት መስራት አለብህ ማለት ነው እንዴ? ያዕቆብ በፍፁም ስለ ስራ እያወራ አይደለም ይልቁኑ ስለሚሠራ እምነት እንጂ። ያዕቆብ ለማስተላለፍ የፈለገው መልዕክት ይህን ይመስላል፦ የሚያድንህ እውነተኛ እምነት ነው። እውነተኛ እምነት ማለት በስራ የሚገለጥ እምነት ነው። ለምሳሌ ፀሎት ይጠቅማል እያልክ የማትፀልይ ከሆነ ፀሎት እንደሚጠቅም አታምንም ማለት ነው ብታምን ኖሮ ትፀልይ ነበረ። አንደበትህ ይናገራል ልብህ ግን አላመነም። ስለዚህ ማድረግ ያለብህ ነገር መስራት ሳይሆን ማመን ነው ። ያዕቆብ እያለ ያለው አላመናችሁም እመኑ ነው። ያዕቆብ በስራ በኩል ለሠዎቹ ለማሳየት የፈለገው ስራን ሳይሆን እምነትን ነው። ምክንያቱም ኢየሱስ ከበሽታ እንደሚፈውስህ ታምናለህ ነገር ግን ሠዎች ሲታመሙ አትፀልይም ስለዚህ አታምንም ማለት ነው። ያዕቆብ የስራ ሳይሆን የእምነት መምህር ነው። ያዕቆብ እመን እያለህ ነው። የሚያድንህ እምነት ስለሆነ በትክክል በክርስቶስ ስራ እመን። ከዛ ይሄ እምነትህ ያራምድሀል አለቀ። ምክንያቱም አስቀድሞም ቢሆን አንተ መስራት ብትችል ማመን አይጠበቅብህም ነበረና። የተፈለገው ስራ አንተ የምትሠራው ሣይሆን ክርስቶስ ላይ ያለህ እምነትህ የሚሠራውን ስራ ነው። ፃዲቅ በእምነት በሕይወት ይኖራል።
@Pure_Christianity
@Pure_Christianity