2023-03-08 17:00:24
#እዉነተኛ_ታሪክ
በሶሪያ ጦርነት ጊዜ ነዉ፥ በምድረ በዳ የተገኘዉ እዉነተኛ ወዳጅ።
በሃገረ ሶሪያ አንድ ሙስሊም ሴት ከባሏ እና ከ አራት ልጇቿ ጋር የቤታቸዉ በረንዳ ላይ ቁርስ ይበላሉ፤ በድንገትም እየተጫወቱ ምግባቸዉን እየተመገቡ ሳሉ:- ወደ አይር መንገዱ የተወረወረ ሚሳኤል የእነሱ ቤት ላይ ያርፋል ሚሳኤሉም በወደቀ ቅጽበት የዛች ሴት [ስሟን ካልተሳሳትኩ አሊማ] ሁለት ወንድ ልጇቿ እና ባለቤቷ ይሞታሉ፣ አሊማ ላይ ከባድ ጉዳት በእግሯ ላይ ሲደርስ ሁለት ሴቶች ልጆቿ መጠነኛ ጉዳት ያገኛቸዋል።
ለተወሰነ ቀን ሕክምና ካደረገች በሗላ አሊማ ያላትን ንብረት ሁሉ ትሸጥና እጇ ላይ ያለዉን ሁሉ ብር ድንበር ለሚያሻግር ደላላ ሰጥታ ወደ ሌላ ሃገር ከባህር ማዶ ለመሰደድ ትሄዳለች፤ ጉዞዉ ለሊት ስልነበር በጣም የሚያሳዝነዉ አሊማ ከደረሰባት ጉዳት የተነሳ በክራንች ስለምትሄድ ያዉም ሁለት ሕጻናት ሴቶች ልጆች ይዛ እርመጃዉ በጣም የተገታ ነበር። በዚህ ጊዜ ከፊት ከፊት የሚመራቸዉ ደላላ ወደ አሊማ ይመጣና በጣም ተቆጥቶ:- [ስሚ አንቺ ሴትዮ ለሊቱ ከነጋ ሰዎቹ ደርሰዉ ይገድሉናል አንቺ በደንብ አልራመድ ብለሽ እኛን ልታሲዥን ነዉ የራስሽ ጉዳይ] ብሎ ክራንቹን በእግሩ መጥቶ ይጥልባታል አንዴ ብሩን ሰልተቀበለ የአልሚና ጉዳይ ትቶ በሩጫ ያመልጣል። አሊማ ከሁለት ሕጻናት ልጆቿ ጋር በለሊት በጫካ ዉስጥ ወድቃ ታለቅሳለች። እያለቀሰችም እያለ በድንገት ሰዉነቱ የፈረጠመ ረጅም ጎልማሳ ሰዉ ይመጣና:- [አይዞሽ በሶሪየሎ እንባዋን በእጁ ያብሳል፣ በእጁም ደግፎ ያስነሳትና በአንድ እጁ እሷን በሌላኛዉ እጁ ሁለት ሴት ልጆቿን ይዞ በጣም በፍጥነት እየተራመደ ከነበሩበት አገር ያወጣቸዋል]፤ የሚፈለግቡት ሃገር ካደረሳቸዉ በሗላ [ሰለም ሁኑ] ብሎ ሊሄድ ሲል አሊማ [አንተ መልካም ሰዉ አላህ ዉለታህን ይክፈልህ ስምህንና አድራሽን ንገረኝ ደዉዬ ላገኝህ እፈልጋለሁ ትለዋለች]
እሱም:- ስምሽን አዉቀዋለሁ አሊማ ነዉ የሁለት ልጆቿንም ስም ይጠራና አድራሻዬን በቅርቡ ታዉቂዋለሽ ባለሽበት ቦታ እመጠላሁ እስከዛዉ ግን ስሜ አልመሲ ኢሳ ነዉ ብሏት ተሰወረ።
ከቀናት በሗላ አሊማ የሄደችበት ሃገር ያሉ ባልና ሚስት የወንጌል አገልጋዮች ጌታ ስለ አሊማ ይነግራቸዋል፤ ከዛም ሄደዉ ወንጌል እንዲሰብኩላት አዘዛቸዉ። እነሱም ጌታን ታዘዉ ወደ አሊማ ቤት ሄዱ በሯን ሲንኳኩም አሊማም በሯን ከፍታ ተቀበለቻቸዉ፣ መልዕክቱንም ይነግሯት ጀመር:- [99 በጉቹን ትቶ አንዷን የጠፋችዉን በግ ሊፈልግ ስለሄደዉ ሲያገኛትም ተሸክሟት በደስታ ስለተመለሰዉ እረኛ ገና እያወሩላት እያሉ አሊማ በመሃል አቋረገጠቻቸዉ እና ጮህች ይሄ የእኔ ታሪክ ነዉ ከቀናት በፊት ጠፍቼ ወድቄ በሞት አፋፍ ላይ ተሸክሞ አተረፈኝ በፈርጣማ እጆቹ የታደገኝ አልመሲ ኢሳ ነዉ] አለች በጉልበቷ ተንበረከከች፥ አድራሻዉ የጠፋባትን ደጉን እረኛ አልመሲ ኢሳ እዉነተኛዉን አዳኙን በቃሉ በኩል አገኘችዉ!
የኢየሱስ አድራሻዉ ቃሉ ዉስጥ ነዉ፤ አልመሲ ኢሳ ያድናል!
#ምንጭ:- ከአንድ ሚሽነሪ የተገኘ እዉነተኛ ታሪክ
መልካም ቀን፤ ሐምሌ 26/11/2013ዓ.ም። “የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።”
— 2ኛ ቆሮንቶስ 13፥14
የመረጃ ምንጭ የእግዚአብሔር አገልጋይ ማስረሻ በላይ Facebook page የተወሰደ መልዕክት ነው።https://t.me/PRAISE_TO_OUR_GOD/3296
2.2K viewsEphraim Grace, edited 14:00