Get Mystery Box with random crypto!

አደይ የሳይኮሎጂ ምክሮች 🌼

የቴሌግራም ቻናል አርማ psycologye — አደይ የሳይኮሎጂ ምክሮች 🌼
የቴሌግራም ቻናል አርማ psycologye — አደይ የሳይኮሎጂ ምክሮች 🌼
የሰርጥ አድራሻ: @psycologye
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.51K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል የተለያዩ የሳይኮሎጂ ምክሮች እና ሀሳቦች ይነሳሉ። እራስን መለወጥ ከዛሬ ይጀምራል።
በዚህ ቻናል ላይ ከምናወራባቸው ሀሳቦች ውስጥ፦
👉ስለ ፖርኖግራፊ ሱስ
👉የአደንዛዝ ዕፅ ሡስ
👉ድብርት እና ጭንቀት
👉ከሠው ጋር መጋጨት
👉ብቸኝነት
👉ጓደኛ ማጣት
👉የአስተሳሰብ ለውጥ
👉ፍርሀት እና የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ይነሳሉ። በግል ማማከር ለምትፈልጉም ሚስጥራችሁ እንደተጠበቀ እናማክራለን

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

3

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-24 19:50:36
አንተ ጠቃሚ ነህ። ለአላማ በአላማ ተፈጥረሀል። ደግሞም በጣም ነው የምታምረው። አንተ የስህተት ውጤት አይደለህም። ስህተትን ለማስተካከል እንደውም ተፈጥረሀል። አንተ ባለፀጋ ነህ። እራስህን በመስታወት እየው ልዩ እኮ ነህ።
533 views16:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 19:56:56
የአንዱ የደስታ ምንጭ...

ዝናብ ብዙውን ጊዜ ፍቅረኛሞች ለፍቅራቸው መግለጫ ይጠቀሙበታል። በዝናብ ይበሰብሳሉ። ይሯሯጣሉ። አሉ ደግሞ በዝናብ ምክንያት ሳይተኙ የሚያድሩ ሰዎች።
አየህ አንዳንድ ጊዜ ዝናብ የፍቅር መግለጫ ብቻ ሳይሆን የሀዘን ማስነሻም ይሆናል።

ዛሬ አንተን እያስደሰተክ ያለው ነገር ሌላውን ደግሞ እያስለቀሰው ይሆናል። ለዚህ ነው ፈላስፋው የአንዱ የገነት መግቢያ በር ለሌላው የገሀነም ደጅ ነው ያለው። ስለዚህ ሁሉም አንተን ባስደሰተክ ነገር እንዲደሰት አትጠብቅ። አንተ ልደትህን በምታከብርባት ቀን እናቱን ወይም አባቱን የቀበረበትን ቀን እሚያስታውስ ስንት ሰው አለ መሰለህ።

እናም ዛሬህን ተደስተክ አሳልፈህ ከሆነ ተመስገን በል። አዝነህም ከሆነ ካንተ የባሰ ያዙ ስላሉ ሀዘንህን ስላላከፋብህ ተመስገን በለው።


Its Me Jonah
1.2K views16:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 21:28:41
ዛሬ የምርቃት ቀኔ ነበር። እኔ ግን ቢሮዬ ላይ በስራ ተጠምጄ ነው ያሳለፍኩት። ብዙ ሰው የጅል ስራ እንደሰራው ነገረኝ። እና የምራቸውን ነው ? ይሄ እኮ ልዩ ቀንህ ነው ማክበር አለብህ አሉኝ። ለምን አከብረዋለው ? ስራዬን በመስራቴ ዛሬ ብዙ ብር እሚያተርፍ ውሎ አሳልፌያለው። ማታ እቤት ስገባ እናቴ አባቴ እና አጎቴ ከሁለት ጉዋደኞቼ ጋር ሆነው ዳቦ ደፍተው ቡና አፍልተው ስጋ ተሰርቶ ጠበቀኝ። ዛሬ ጠዋት 12 ሰአት ስልጠና ገብቻለው ጠዋት 2 ሰአት ስልጠናችንን ስንጨርስ በኔ ምክንያት በስልጠና የተቀየሩ 5 ጠንካራ ልጆች ጋር ቆንጆ የቁርስ ሰአት አሳለፍኩ። ከሰአት ደግሞ ጉዋደኛዬ በስጦታ አንበሻበሸችኝ።
ሁሌም ቢሆን ጊዜህን በአግባቡ እና በክብር ከተጠቀምክበት ልደሰት ባትል እንኳን ሚያስደስቱክ ሰዎች በዙሪያህ ይኖራሉ። እናም ሁሌም ቢሆን ዛሬ ላይ የምትሰሩዋት እያንዳንዱዋ ነገር ነገ ላይ ዋጋ እንዳላት ማወቅ ያስፈልጋል። ትምህርት ተምረህ ከምትመረቀው በላይ ህይወት አስተምራህ ብታስመርቅህ ስኬታማ ትሆናለህ ብዬ አምናለው። መልካም አዳር እወዳችሁዋለው


Its Me Jonah
1.7K views18:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 10:13:57
አሁን ስልጠናችንን ጨረስን እናም ኬክ ቆረሳ አደረግን። በጣም አሪፋ ጊዜ ነበር። ሁሉም በሰለጠነው ስልጠና መሰረት ቤተሰቡ ጋር በመደወል የይቅርታ እና የምስጋና ጥያቄ አቀረበ። በእንባ ተራጩ። በጣም ደስ አላቸው። እውነት እኔም በጣም ደስተኛ ሆኛለው። መልካም ቀን እወዳችሁዋለው

Its Me Jonah
2.0K views07:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 07:59:55
አሁን
በዚህ ሰአት የምስጋና እና የይቅርታ ጊዜ ስልጠና ልጆቼን እያሰለጠንኩ ነው። አሁን በሚባለው ጊዜ ውስጥ ሰው የፈለገውን የማድረግ ሀይል እና አቅም አለው። በጣም ደስ ይላል።
1.8K views04:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 09:59:13 ለውጥ
ለውጥ ከህይወት ጋር የማይነጣጠል ነገር ነው፤አንዳንዱ ለውጥ እድገትና ብልፅግና ሊያመጣ ሌላው ደግሞ ላያመጣ ይችላል፤ ነገር ግን ለውጥን የሚያቆም ሀይል የለም። ( አኑራግ ፓራካሽ ሬይ)
1.8K views06:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 11:59:43
እውነት ትውልድ አፍርቶ እንደማየት ምን እሚያስደስት ነገር አለ? ትላንት በነበረን የስልጠና ድግሳችን ላይ አዳዲስ ልጆቻችን ሲያሰለጥኑ እኛ ቁጭ ብለን ሰለጠንን። እውነት በጣም በደስታ ያሳለፍኩበት ቀን ነበር። በቃ አንድ ሰው አንድ መሪ አንድ አሰልጣኝ ማፍራት መቻል እራሱ እኮ መታደል ነው። በጣም ደስተኛ ነኝ በጣም። ለውጥ ማለት ይሄ ነው

Its Me Jonah
1.8K views08:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 14:14:33
ወዳጆቼ አባቴ ምን ሲል ይመክረኛል መሰላችሁ ፦ ዮኒ ሁሌም ቢሆን ልክ እንደ ጀልባ ሁን። ጀልባ በውሀ ላይ ሲጓዝ ማዕበል ሲነሳበት መሪው ሁሌም ማዕበሉን ተጠቅሞ ወደሚፈልግበት ይደርሳል። ማዕበል የጀልባዋን ፍጥነት ይጨምረዋል። ነገር ግን ከደነገጠች ሰብሮ ይጥላታል። እናም ሁሌም ጀልባ ለማዕበል ቀለል ማለት አለባት አለኝ።
እናም አንተም በህይወትህ ላይ የቱንም ያህል ችግር እና ፈተና ቢመጣ አትደንግጥ ቀለል በል። የትኛውም ፈተና እና ችግር ወደፊት እንድትስፈነጠር ይሆኑሀል አለኝ። እውነት በህይወቴ ከማረሳቸው የአባቴ ምክሮች ውስጥ አንዱ ነው። እናም ችግር ሲመጣ ቀለል ማለትን እወዳለው። ብዙ ሰው ችግር እና ሀዘን ሰበረኝ የሚለው ሰባሪ ችግር ስላለ ሳይሆን እኛ እኛ ለችግሩ የቀረብንለት አቀራረብ ነው። ስለዚህ የኔም አባት ለእናንተ አባታችሁ ይሁንና ምክሩን ተቀበሉት። ልክ እንደ ጀልባ ሁኑ። ውሀ ላይ ያለች ጀልባ ማዕበል መቼ እንደሚመጣ አታውቅም ግን አንድ ነገር ታውቃለች ማዕበል እሚባል ነገር እንዳለ። እናንተም በህይወት እስካላችሁ ድረስ ችግር መቼ እንደሚመጣ አታውቁም ነገር ግን አንድ ነገር ታውቃላችሁ ችግር እሚባል ነገር እንዳለ። ስለዚህ በየትኛውም ችግር ለመውደቅ አትዘጋጁ። አሻግራችሁ ለማለፍ እንጂ። መልካም ቀን እወዳችሁዋለው


Its Me Jonah
1.9K views11:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-21 09:29:13
መኖርን ለምን መረጥክ ?
የሰው ልጅ የመሞቱን ያህል መኖሩን አይፈራውም። እውነት ሳስው ያስገርመኛል። መንግስተ ሰማይ እንደሚገቡ እርግጠኛ እንደሆኑ የሚሰማቸው ሰዎች እንኩዋን ሞትን አብዝተው ይፈሩታል። መኖር እኮ እንደውም ያስፈራል። ምክንያቱም መሞታችን አንዴ እኛነታችን የሚቋረጥበት ሲሆን መኖራችን ግን ሁሌም በኛነት ጥያቄ ውስጥ የምንያዝበት ነው። ትልቁ ጥያቄ ታድያ ይሄ ነው፦ ከመሞት ይልቅ መኖርህን ለምን መረጥከው? ጠዋት ከእንቅልፍክ ስትነሳ ምንድነው ያስነሳህ? ምንድነው እንድትኖር ያደረገህ ?ለምንስ መኖርክ ይሄን ያህል ዋጋ ተሰጠው? አየህ ይሄንን ነው መመለስ ያለብህ። ለምን ? ስለዚህ መኖርን መርጠህ እየኖርክ እስካለህ ድረስ የተሻለውን ምርጡን እና ትልቁን ህይወት ኑር። አለበለዚያ ግን መኖርህም መሞትህም ዋጋ የለውም። የምትኖረው ኖረህ ለማለፍ ነው ወይስ ሌሎችን ለማኗኗር ነው? አብዛኛው ሰው ኗሪ ሳይሆን አኗኗሪ ነው። የህዝብ ቁጥርን ሚጨምር ብቻ አለ። ስለዚህ ስትኖር ለምን? እድሜ ሲጨመርልህ ለምን ? አለዚያ ብዙ አበርክተው መሞት ሚፈልጉ አሉ ለነሱ ቦታ መልቀቅም ፅድቅ ነው። ስለዚህ የዘመንህ ጥያቄ ይሁን። ለምን እኖራለው ? ምን ልሰራ ? ምን ላበረክት? ምን ልሰጥ ነው የምኖረው ? ብለህ እራስህን ጠይቅ። አለበለዚያ ግን ህይወት ላንተ ትርጉም የላትም ስለዚህ ሞትን አትፍራው። ምክንያቱም ለመኖር ሚያጓጓ ነገር የለህም። መልካም ጊዜ እወዳችሁዋለው
@Jonahhhhhhh

Its Me Jonah
2.2K views06:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-19 18:15:30 ማባበል
ማባበል ምንድነው ? ማባበል ማለት አንድ ነገር እንዲደረግላችሁ ወይም ሰዎች ለእናንተ የሆነ ነገር እንዲያደርግላችሁ በስሜት በእንቅስቃሴ እና በተግባር የሚገለጥ ነገር ነው። የራሳችሁ አይምሮ እነደሚያባብላችሁ ታውቃላችሁ ? እራሳችሁን በራሳችሁስ እንደምታባብሉት ታውቃላችሁ?
አንድን ነገር ለማድረግ ባልፈለጋችሁት ጊዜ እና በድካማችሁ ጊዜ የሆነ መከናወን ያለበትን ነገር እንዳታከናውኑ የምትሆኑት እራሳችሁን ስለምታባብሉት ነው። ማባበላችሁ መድረስ የምትፈልጉበት ቦታ ላይ እንዳትደርሱ ገደል ይሰራባችሁዋል። ይሄን ብታደርገውም ባታደርገውም እኮ ችግር የለውም። ለምን ቀስ እያልክ አትሞክርም። ከምትጨናነቅ እኮ ቢቀርብህ የተሻለ ነው። ለምን ሰዎች ሰርተውት የማያውቁትን ነገር ለመስራት ትለፋለህ። በቃ ከሁሉም ጋር አንድ ሆነክ ኑር። የተለየ ነገር ላትፈጥር እራስህን አታድክመው ይልሀል አይምሮህ። እና አይምሮህን ድፍረት አስለምደው። ቆራጥ አድርገው። ወደፊት የሚራመድ እንጂ በሆነው ባልሆነው የሚያባብልህ የስኬትህ ጠላት አታድርገው። ስለዚህ ዛሬ ላይ ወስንበት። እራስህን እያባበልክ ከስኬት አትራቅ።
የሚያባብሉ ጉዋደኞች ካሉህም እራቃቸው አይጠቅሙህም ይገድሉሀል። በቁምህ ነው የሚቀብሩህ። ወደፊት የሚያራምድ እና የሚገፋ አንድ ጉዋደኛ ካለህ ከብዙ ሺህ አባባይ ጉዋደኞች ይበልጣል። መልካም ምሽት እወዳችሁዋለው

Its Me Jonah
1.7K views15:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ