Get Mystery Box with random crypto!

ፍኖተ-ወራዙት ዘኦርቶዶክስ ⛪

የቴሌግራም ቻናል አርማ fenotewerazut — ፍኖተ-ወራዙት ዘኦርቶዶክስ ⛪
የቴሌግራም ቻናል አርማ fenotewerazut — ፍኖተ-ወራዙት ዘኦርቶዶክስ ⛪
የሰርጥ አድራሻ: @fenotewerazut
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.19K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ፍኖተ-ወራዙት ቻናል መንፈሳዊ ትምህርቶችን የሚያገኙበት ሃይማኖታዊ ቻናል ነው። በዚህ ቻናል በመንፈሳዊ ሕይወትዎ የሚበረቱባቸውን መንፈሳዊ ጽሑፎችና መልእክቶች ባሉበት ሆነው መከታተል ይችላሉ።
    መልእክት ወይም አስተያየትና ጥቆማ ካለዎት
https://t.me/Tadiweszefinotewerazut
https://t.me/TadiwesTeshager
✞ይላኩልን
@Fenotewerazuteotc 👈ለግሩፕ

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 09:32:52 ቅዱስነታቸው ወደ ሀገር ቤት ይመለሳሉ ሲባል የተጨነቀው አካል ቤተ ክህነቱን ይረብሸው ይዟል። አቀባበል ለማድረግ ኃላፊነት የተሰጣቸውን እነ ሊቀ ማዕምራን ፋንታሁን ሙጬን አስረዋቸዋል።

የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው እስክንድር ገ/ክርስቶስ ከታሰሩት መኻል ተፈትቷል። የፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት አገልጋዮችን ደኅንነቶች ሊያስራቸው ወደ ቤተ ክህነት ቢመላለሱም አልተሳካላቸውም።

ምክንያቱም የእስር ማዘዣ ያላመጣ አካል ወደ ግቢ እንዳይገባ ቆፍጣናው ሥራ አስኪያጅ ስላዘዙ። የእስር ማዘዣ የያዘም በቅድሚያ ኃላፊዎችን ሳያነጋግር በቀጥታ ወደ ታሳሪዎች እንዳይሔድ አዝዘዋል።

ሊታሰሩ የተፈለጉት:-

፩. መልአከ ሕይወት አባ ኃይለ ገብርኤል ነጋሽ የልዩ ጽ/ቤት ኃላፊ፣
፪. መልአገነት አባ ኪዳነ ማርያም ደስታ አቡነ ቀሲስ፣

፫. መምህር ሙሴ ኃይሉ የፓትርያርኩ ልዩ ተጠሪ ፕሮቶኮል፣

፬. መምህር ልሣነ ወርቅ ደስታ ገብረሕይወት የልዩ ጽ/ቤት ጉዳይ አስፈጻሚ፣

፭. መልአከ ሰላም አባ ኪሮስ ወልደ አብ ካሜራ ማን፣

፮. አባ ተስፋ ሥላሴ ዘርአይ ናቸው።

አቡነ አብርሃም እና አቡነ ጴጥሮስ የታሰሩትን እነ ፋንታሁን ሙጬን እና ኤልያስ ተጫነን ጣቢያ ድረስ ወርደው ጠይቀዋቸዋል። አቡነ አብርሃም ከባሕር ዳር እንደገቡ በቀጥታ ነበር ወደ ጣቢያው ያቀኑት። እንዲህ እንጅ አባትነት። እግዚአብሔር ያሰንብትልን!

የታሰሩት በአስቸኳይ ይፈቱ ዘንድ እናሳስባለን።

ሲወጡ ጭንቅ ሲመለሱ ጭንቅ።

አባይነህ ካሴ

ወደዚህ ግሩፕ ሼር ያልተደረጉ መረጃዎች እንዲደርሱዎ ገፃችን ተወዳጁ(Follow us)

ለሌችም እንዲደርስ በቅንነት
ሼር አድርጉ !
፨፨፨ #ወስብሐት_ለእግዚአብሔር ፨፨፨

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

•➢ ሼር // SHARE

ለሌሎች መረጃዎች
በቴሌ ግራም ያግኙን

On Telgram

https://t.me/Fenotewerazut

https://t.me/negerlikawunt
143 views06:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 09:32:47
105 views06:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 09:28:10
95 views06:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 09:26:50 ለቅዱስነታቸው አቀባበል እንዳይደረግ ክልከላ እየተደረገ ነው። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ቀዳማዊ ሐምሌ ፲፱ ቀን ለሕክምና ወደ ሰሜን አሜሪካ ማምራታቸው ይታወቃል። የሕክምና ክትትል እያደረጉ ያሉት ቅዱስነታቸው የጤናቸው ሁኔታ መሻሻል እያሳየ መሆኑ ተገልጿል። ይህንንም ተከትሎ ቅዱስ ፓትርያርኩ በአሜሪካ እያደረጉት ያለውን ሕክምና አጠናቅቀው ነሐሴ ፳፬ ቀን እንደሚመለሱ ተገልጾ የነበረ ቢሆንም መርሐግብሩ ተራዝሞ ጳጉሜ ፩ ቀን ፳፻፲፬ ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመለሱ የቤተክርስቲያን ምንጮች አሳውቀዋል። ይሁን እንጂ ለቅዱስነታቸው የአቀባበል ሥነ ሥርዓት እንዳይካሄድ በመንግሥት በኩል ክልከላዎች እየተደረጉ መሆኑን ምንጮቻችን አሳውቀዋል። የብልጽግና መንግሥት በተደጋጋሚ በቅዱስነታቸው ላይ ፖለቲካዊ ሴራ በመሥራት ቤተክርስቲያንን ለመከፋፈል እየሞከረ ሲሆን ቅዱስነታቸው ለሕክምና በሄዱበት ወቅትም የስም ማጥፋት ዘመቻዎችን ከፍቶ እንደነበረ የሚታወስ ነው። እንደምንጮቻችን ገለጻ ከሆነ ቅዱስነታቸው ወደ አገር ቤት ሲመለሱ ሊደረግላቸው የታሰበውን የአቀባበል ሥነ ሥርዓት ከወዲሁ እየከለከለ ይገኛል ብለዋል። ቅዱስ ፓትርያርኩ ባሉበት ሁሉ ቤተክርስቲያን መኖሯንና ቅዱስ ፓትርያርኩ ላይ የሚደረጉ እኩይ ሴራዎች ሁሉ በቤተክርስቲያን ላይ የሚደረጉ መሆናቸውን ቤተክርስቲያን በተደጋጋሚ አስታውቃለች። ይሁን እንጂ የብልጽግና መንግሥትና ጀሌዎቹ ተደጋጋሚ ሴራዎችን እየሸረቡ ነው። #መንግሥት_ሆይ #እጅህን_ከቤተክርስቲያን_ላይ አንሣ!!!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከታትለን እናደርሳችኋለን።

ሐራ ተዋህዶ

ወደዚህ ግሩፕ ሼር ያልተደረጉ መረጃዎች እንዲደርሱዎ ገፃችን ተወዳጁ(Follow us)

ለሌችም እንዲደርስ በቅንነት
ሼር አድርጉ !
፨፨፨ #ወስብሐት_ለእግዚአብሔር ፨፨፨

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

•➢ ሼር // SHARE

ለሌሎች መረጃዎች
በቴሌ ግራም ያግኙን

On Telgram

https://t.me/Fenotewerazut

https://t.me/negerlikawunt
107 views06:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 07:56:17 #የተዋሕዶ_ልጅ_ሆይ_እባክህን_ንቃ

ቆይ ግን የሰሜኑ የወንድማማቾች ጦርነት ሙስሊሞችንና ፕሮዎቹን አይመለከታቸውም እንዴ? እሳቱ አይነካቸውም ወይ? ሙጂብ አሚኖ?ከሕመዲን ጀበል?አብዱልጀሊል ሺህ አሊካሳ? አቡበክር አህመድ?ያሲን ኑር?ከሚል ሸምሱን...ወዘተ የእሳቱ ወላፈን አይነካቸውም ወዳጄ። የሚተላለቀው የቅድስት ኦርቶዶክስ ልጆች ናቸው ከሁለቱ ወገን። ከዚያ ማዶም የቅድስቲቱን የአክሱም ልጆች ግፋ በለው እያለ የእሳት እራት የሚያደርገው ሕወሀት ከዚህም የብልጽግና ጎስፕል ቅኝቶች ፉከራና ሽለላ የተዋሕዶን ልጆች አጫረሷቸው።
በአንዲት ቤተክርሲቲያን ለምስጋና የሚቆሙ!
ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን የሚቀበሉ!
ከአንድ ሰማያዊ ምንጪ ከተቀዳ የመላእክት ዝማሬ በቅዱስ ያሬድ መዝሙር የሚዘምሩ!
በአባ ሕርያቆስ ቅዳሴና በቅዱስ ኤፍሬም ውዳሴ በእንድ የሚቆሙ!
በአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ሰአታት ማህሌት የሚቆሙ!
በሰማይ ባለው አባታቸው በመንግስቱ በአንድነት ለምስጋና የተጠሩ!
አንድ አይነት ሕዝቦች እንዲህ የሚያባላቸው የጎጠኝነትና የመንደርተኝነት የእኔነት መንፈስ የሆዳምነት የስስታምነት ጠኔ ተወግዶ አንድ መሆናችንን ማን በነገረን?
አምላኬ ሆይ እባክህን ስለ እናትህ ቃል ኪዳን ስትል የኢትዮጵያን ነገር ቸል አትበል!
ቅድሰት ቅዱሳን ሆይ የአምላጅነትሽ ነገር ወዴት ነው? በእውነት የ24 ሰአታት ልመናችንና ደጅ መጥናታችን ወደ አንቺ ማንጋጠጣችን ተመልከቺ! የእኛን ኃጢያት አትመልከቺ በአንቺ ልመና ሰላሙን ላኪልን!
ቅድስት ሆይ የሚሉሽን ወገኖችሽን ልጆችሽን ስምሽን እየጠራ ለጦርነት የሚማገዱ የቃል ኪዳን ልጆችሽን ልቦና ተመልክተሽ ክፉውን መንፈስ አርቂልን!
ይኽንን ስንል ግን አብረው የሚዋደቁ የገፈታው ቀማሽ ሙስሊም ወንድሞቻችን የሉም ማለት አይደለም።
ለዚህም ማሳያ ሙሉ ሙስሊሙን አላልንም በስም የጠቀስናቸውን ብቻ ነው ያልን። በስም መጥቀሳችን ይህንኑ ያጠናክራል ።

አምላኬ ሆይ ወዴት ነህ!
309 views04:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 07:56:07
188 views04:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 16:23:55
ዛሬ አብርሆት ካፌና ሬስቶራንት ነው ያመሸነው። እጅግ ልዩና ዘመናዊ ነው። አስተናጋጆች በአለባበሳቸው ሀገርኛ ናቸው። ረጅም ቀሚስ ለብሰው የአብርሆትን ቀጣይ ርእይ የሚናገሩ ይመስላሉ።

በነገራችን ላይ ባሕር ዳር ከተማ ውስጥ ትላልቅ የቢዝነስና የትምህርት አክሲዮኖች ተቋቁመዋል።

፩- በቅርብ የተቋቋመውና ከራድዮን ካፌና ሬስቶራንትን የሚያስተዳድረው ከራድዮን ንግድ ሆቴልና ቱሪዝም አ.ማ
፪- ኹለት ከፍተኛ ገበያዎችን(ሐይፐር ማርኬት) ሥራ ያስጀመረው ቤተሰብ ምጣኔ ሀብት አ. ማ
፫- በቅርቡ አብርሆት መዝናኛን የከፈተው አብርሆተ ሰብእ የትምህርት የሥልጠናና ንግድ አ.ማ
እነዚህ አክሲዮኖች ከንግድ ባሻገር ሰው ላይ የሚሠሩና እየሠሩ ያሉ ናቸው። የቦርድና የአስተዳደር አመራሮች ዶክተሮችና የተሻለ የትምህርት ዝግጅት(የአመራር ጥበብ) እንዲሁም ኢትዮጵያዊ ሰብእና ያላቸው ናቸው። እነዚህ አክሲዮኖች ከዓመታት በኋላ ለባሕር ዳር ብቻ ሳይሆኑ ለኢትዮጵያም ተስፋ ናቸው።

(አዲሱ)
390 views13:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 11:26:07 ጸሎት

፩. ጸሎት ከክፉ ነገር ይጠብቅሃል፤

፪. ጸሎት በእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ እንድትኾን ያደርግኻል፤

፫. ጸሎት ወደ እግዚአብሔር ይበልጥ ያቀርብኻል፤

፬. ጸሎት ደስተኛ ያደርግኻል፤

፭. ጸሎት ተስፋን ይሰጥኻል፤

፮. ጸሎት የራስ ወዳድነት ስሜትኽን ይቀንስልኻል፤

፯. ጸሎት ከኹሉም ስቃዮች ይፈውስኻል፤

፰. ጸሎት ፈተናን ለማሸነፍ ይረዳኻል፤

፱. ጸሎት በመንፈሳዊ ሕይወትኽ ጠንካራ እንድትኾን ያደርግኻል፤

፲. ጸሎት ነገሮችን ይለውጣል።

ወደዚህ ግሩፕ ሼር ያልተደረጉ መረጃዎች እንዲደርሱዎ ገፃችን ተወዳጁ(Follow us)

ለሌችም እንዲደርስ በቅንነት
ሼር አድርጉ !
፨፨፨ #ወስብሐት_ለእግዚአብሔር ፨፨፨

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

•➢ ሼር // SHARE

ለሌሎች መረጃዎች
በቴሌ ግራም ያግኙን

On Telgram

https://t.me/Fenotewerazut

https://t.me/negerlikawunt
298 views08:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 08:11:16 ❖ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምን ማለት ነው ? ~

1 ኦርቶዶክስ የሚለው ስም ከየት የመጣ ነው?
2 ተዋህዶ የሚለውስ ከየት የመጣ ነው?
3 ክርስትያን ማለትስ ምን ማለት ነው???

ኦርቶዶክስ ማለት ቃሉ የግሪክ ሲሆን አማርኛው
ትርጉሙ እውነተኛ፤ቀጥተኛ መንገድ የሆነች ሃይማኖት
ማለት ነው፡፡
ቀጥተኛዋ መንገድ ጠይቁ በእርሷም ላይ ሂዱ
ለነብሳቹሁም እረፍት ታገኛላቹሁ፡፡[ኤር 6÷16]
ነብዩ ኤርምያስ እንዳለው እዚህ ላይ እንግዲህ ቀጥተኛ
ማለት ኦርቶዶክስ ማለት ሲሆን መንገድ ማለት ደግሞ
ሃይማኖት ማለት ነው፡፡
ኢየሱስም ክርስቶስም አለ እኔ መንገድ እውነት
ሕይወት ነኝ ብልዋል፡፡[ዮሐ 14÷6]
ይህ ማለቱም የሃይማኖት መሰረታ ቹሁ እኔ ነኝ ማለቱ
ነው፡፡
ከሰማያዊው ጥሪ ተከፋዮች የሆናቹሁ ቅዱሳን ወንድሞች
ሆይ የሃይማኖታችንን ሊቀ ካህን የሆነውን ኢየሱስ
ክርስቶስን ተመልከቱ፡፡[ዕብ 3÷1]
ስለዚህ ኦርቶዶክስ ማለት ይህ ነው፡፡

2 ተዋህዶ ማለትስ ከየት የመጣ ነው?

ተዋህዶ ማለት ተዋሃደ ከሚለው የግእዝ ግስ
የተወሰደ ሲሆን ትርጉሙ አንድ ሆነ መለኮትና ስጋ አንድ
ሆነ ማለት ነው፡፡ ከሁለት አካል አንድ አካል ፤ከሁለት
ባህርይ አንድ ባህርይ ሆነ ማለት ነው በሌላ አካሄድ ደግሞ
ተዋሃደ ማለት መለኮት ስጋ ለበሰ ከድንግል ማርያም
ከስጋዋ ስጋ ከነብሷ ነብስ ነሳ ማለታችን ነው፡፡
ይህም ደግሞ ግልፅ የሆነ እውነት ነው፡፡
በጀመርያ ቃል ነበረ ፤ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ
ነበረ፤ቃልም እግዚአብሔር ነበረ፡፡[ዮሐ 1÷1]
ቃልም ስጋ ሆነ፤ፀጋንና እውነትን ተመልቶ በእኛ አደረ
እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡[ዮሐ1÷14]
ስለዚህ ተዋህዶ ስንል ቃል ስጋ ለበሰ ማለታችን ነው፡፡
በበለጠ ደግሞ ብርሃናዊው የሆነ የዓለም ብርሃን
ቅዱስ ጳውሎስ ቃል በቃል ተዋህዶ የሚለው ፅፎልናል፡፡
ክርስቶስ እርሱ ሰላማችን ተውና፤ሁለቱን ያዋሐደ በአዋጅ
የተነገረለት በራሱ አዲስ ሰውን ይፈጥር ዘንድ ሰላምም
አደረገ፡፡[ኤፌ 2÷14-15]
ስለዚ ተዋህዶ ማለትም ይህን ይመስላል፡፡

3 ክርስቲያን የሚለውስ ከየት የመጣ ነው?

ክርስትያን ማለት ከክርስቶስ ስም የተወሰደ ሲሆን
ክርስቶስ ተከታዮች፤አማኞች ማለት ነው፡፡
ክርስቶስ አምላክ ነው፤ጌታ ነው፤ፈጣሪ ነው፤ፈራጅ ነው
ብለን የምናምን ክርስትያን ተብለን እንጠራለን፡፡
የክርስቶስ ሐዋርያትም በአንጾክያ ምክንያት ክርስቲያን
ተባሉ፡፡[ሐዋ 11÷26]
በትዕቢት ተነፍቶ በዲያብሎስ ፍርድ
እንዳይወድቅ፤ሰው ሁሉ አዲስ ክርስቲያን አይሁን፡፡
[1ኛ ጢሞ 3÷16]
ክርስቲያን እንደሚሆን ግን መከራን ቢቀበል ስለዚህ ስም
እግዚአብሔርን ያመስግን እንጂ አይፈር፡፡
[1ኛ ጴጥ 4÷16]
ስለዚህ ሁሉም ከመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተነሳ ነው፡፡
ኦርቶዶክስ ነው ሃይማኖቴ ስን ቀጥተኛ ናት
ሃይማኖታችን እያልን ነው፡፡
=>የተዋህዶ ልጆች ነን ስንልም የክርስቶስ ልጆች ነን
እያልን ነው፡፡
=>ክርስቲያን ነን ስንልም ክርስቶስን የምናመልክ
የምናምን ክርስቲያን ነን፡፡
ማለታችን ነው፡፡
ሌላው እምነት ፤ሃይማኖት ግን ጴንጤ ፤ፕሮቴስንት
፤ካቶሊክ፤ጆባዊስትን ክርስቲያን ነን ቢሉም እነዚህ
የመሳሰሉ ግን ከጥንትም ያልነበረ ስም አዲስ ድርጂት
ነው በመፅሐፍ ቅዱስም አንድም ቦታ ላይ የለም፡፡
ከግዜ ቡሃላ ከኦርቶዶክስ ወጥተው ወደ ምንፍቅና
የተመሩ ድርጅቶች ናቸው፡፡
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ግን ከጥንት የነበረች የነብያት
የሃዋርያት የቅዱሳን ሰማዕታት ሃይማኖት ናት ፡፡አሁን እስከ ልጅ ልጅ ለዘላለም ትኖራለች፡፡

❖አንድ ጌታ❖ እንዲት ሃይማኖት ❖አንዲት ጥምቀት

❖ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ዘላለም ትኑር አሜን

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር ይቆየን
291 views05:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 00:45:11
ስንተባበር እንሰማለን

እንደ ካሮት ማደጉን አንድ ብሎታል

Ours Café
የተከራየውን ቤት እንዲለቅ ተነግሮታል። ቀበሌ 04 የሚገኘው ዝማምነሽ ታወር አወርስ ካፌ ከገባው የውል ስምምነት ውጭ የሆነ ድርጊት በመፈፀሙና በተደጋጋሚ በተሰጠው ማስጠንቀቂያ ማስተካከል ባለመቻሉ ቤቱን አስተካክሎና ቀሪ ክፍያውን ፈፅሞ እንዲለቅ በደብዳቤ አሳውቋል። ይህ የማይሆን ከሆነ ጉዳዩን ወደ ፍርድቤት እወስዳለሁ ብሏል። በነገራችን ላይ በተፈፀመው ድርጊት ያዘነው የከተማዋ ነዋሪ ወደ ካፌው መሄድም አቁሟል።

(tadeletibebu)

ወደዚህ ግሩፕ ሼር ያልተደረጉ መረጃዎች እንዲደርሱዎ ገፃችን ተወዳጁ(Follow us)

ለሌችም እንዲደርስ በቅንነት
ሼር አድርጉ !
፨፨፨ #ወስብሐት_ለእግዚአብሔር ፨፨፨

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

•➢ ሼር // SHARE

ለሌሎች መረጃዎች
በቴሌ ግራም ያግኙን

On Telgram

https://t.me/Fenotewerazut

https://t.me/negerlikawunt
344 views21:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ