Get Mystery Box with random crypto!

Prosperity Party - ብልፅግና

የቴሌግራም ቻናል አርማ prosperity2022 — Prosperity Party - ብልፅግና P
የቴሌግራም ቻናል አርማ prosperity2022 — Prosperity Party - ብልፅግና
የሰርጥ አድራሻ: @prosperity2022
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.08K
የሰርጥ መግለጫ

This is an official telegram channel of prosperity party.

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-26 08:33:19
የመኖርያ ቤት ኪራይ መጨመርም ይሁን ተከራይን ማስወጣት የሚከለክለው ደንብ ለቀጣይ ስድስት ወራት ተራዘመ
*******************
የመኖርያ ቤት ኪራይ መጨመርም ይሁን ተከራይን ማስወጣት የሚከለክለው ደንብ ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት መራዘሙን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዜጎች ላይ የሚደርሰውን የኑሮ ጫናን ለመቀነስ በመኖርያ ቤት ተከራዮች ላይ የኪራይ ዋጋ ጭማሪ እና ተከራይን ማስለቀቅን የሚከለክል ደንብ አውጥቶ ተግባራዊ ማድረጉ ይታወቃል፡፡

ይህም ደንብ በተለያየ ጊዜ እየተራዘመ ላለፈው አንድ አመት ተግባራዊ ተደርጎ ቆይቷል፡፡

ስለሆነም የከተማ አስተዳደሩ አሁን ያለውን አጠቃላይ ነባራዊ ሁኔታ እና የህብረተሰቡን የኑሮ ጫና ከግምት ባስገባ ወቅቱን በአብሮነትና በመተሳሰብ ለማለፍ ይረዳ ዘንድ ይህ ደንብ ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት እንዲራዘም ወስኗል፡፡

በመሆኑም ይህንን ክልከላ በመተላለፍ ተከራዮችን የሚያስወጡ እና የኪራይ ዋጋን የሚጨምሩ አካላት ላይ ማህበረሰቡ በሚከተሉት የስልክ ቁጥሮች ጥቆማውን ለከተማ አስተዳደሩ ማድረስ እንደሚችል ያስታውቃል፡፡

አጭር ቁጥር ፡- 9977

የሞባይል ስልኮች

09-00640830
09-00640789
960 views05:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 11:49:05
በፓርቲያችን 1ኛ ጉባኤ ላይ ከዚህ በታች በዝርዝር የተጠቀሱ ነጥቦች ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎቻችን ሆነው በከፍተኛ ትኩረት እንድንፈፅማቸው የተቀመጡ አቅጣጫዎች ናቸው፡፡
#prosperity
1.8K views08:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 12:25:10
ወጣቶች በሥራ ላይ የሚያተኩሩ፤ ሀገራቸውን ለማወቅ የሚተጉ፣ የሀገራቸውን ጸጋ የሚያለሙ፣ ፈጣሪያቸውን አመስጋኝ መሆን አለባቸው። ሀገራቸው ኢትዮጵያ ትልቅ እንደ ነበረች አስታውሰው ወደ ቀደሞ ከፍታዋ እንድትመለስ በኅብረ ብሔራዊ አንድነት ማጽናት የዚህች ድንቅ ሀገር ልጆች ግዴታ ነው። ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ
የኢፊዴሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር
2.1K views09:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 11:06:14
የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ 2ኛው ተርባይን የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ጀመረ
******** በአፍሪካ ግዙፉ የኃይል ማመንጫ የሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በሁለተኛ ተርባይኑ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ጀምሯል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በቤንሻንጉል ጉሙዝ ጉባ ወረዳ በታደሙበት ዝግጅት ነው በዛሬው ዕለት ሁለተኛው ተርባይን ኃይል ማመንጨት የጀመረው።
የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ካሉት 13 ተርባይኖች መካከል ዩኒት 9 የሚባለው ሁለተኛው ተርባይን የተሳካ ተከላ እና ሙከራ ከተደረገ በኋላ ኃይል የማመንጨት ስራው እውን ሆኗል።
ዛሬ በይፋ ሥራ የጀመረው ሁለተኛው ዩኒት 375 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም እንዳለው ተገልጿል።
2.8K views08:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 09:16:33 ቃላችንን አላጓደልንም!!
በማራኪ አያሌው

ከአራት ዓመታት በፊት ሀገራዊ ለውጡ ሲበሰር የህዝባችን የለውጡን ፍሬዎች የማጣጣም ተስፋ ላቅ ያለ ነበር፡፡ የለውጥ አመራሩም ይህን የሕዝቡን ፍላጎት ለማርካት ሲረባረብ ቆይቷል፡፡ ህዝባችን በለውጡ ዘመን የእንጦጦ ከፍታ ከጫካነት ወደ ውብ ተፈጥሯዊ መዝናኛነት ሲቀየር ተመልክቷል፡፡ የቤተ መንግስት ቅጥር ጊቢ ለምቶና ተውቦ ሲበረከትለት፤ ጎርጎራና ወንጪ የልማቱ ተቋዳሽ ሰሆኑ አይቷል፡፡

የተቋማትና የምጣኔ ሃብት ሪፎርምን፣ የዜጎችና የሀገር ክብርና ፍቅር ከፍ ማለትን፣ ሳይፈልግ የተጫነበት የልዩነት ትርክት በአዲስ የአብሮነትና የወንድማማችነት ትርክት መቀየርን ሲመለከት ለሀገር አንድነት መሰረት እየተጣለ በመሆኑ ተስፋው ያልለመለመ ኢትዮጵያዊና የኢትዮጵያ ወዳጅ የለም፡፡ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም በለውጡ ላደረጉት አበርክቶ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የሰላም ኖቤል ሽልማትን በማበርከት አድናቆቱን ቸሯል፡፡

ከለውጡ በተቃራኒ የነበሩት አካላት ግን እጃቸውን አጣጥፈው አልተቀመጡም፡፡ የሕዝቡን ፍላጎትና ውሳኔ አሜን ብለው መቀበል አልፈለጉም፡፡ አንድም በፍርሃት፤ ሁለትም እኔ ከሞትኩ … እንደሚሉት ሆኖባቸው ከውጪ ሃይሎች ጋር ጭምር ተቀናጅተው በሚለኩሱት እሳት ብዙ መከራ አስተናግደናል፡፡ የዜጎች ሞት፤ መፈናቀል፤ ግጭት፤ የመሰረተ ልማት ውድመት፣ ወዘተ ... ጉዟችንን አድካሚ፤ ድላችንንም በፈተና የታጀበ እንዲሆን አድርገውታል፡፡

አንዳንድ የውጪ ሃይሎች እነሱ በቀየሱልን መንገድ ብቻ እንድንራመድ በየምዕራፉ የነበረው ጉተታ አይዘነጋም፡፡ በታላቁ የሕዳሴ ግድብ፤ በምርጫና በተለያዩ ጉዳዮች "እኛ ካልወሰንላችሁ" የሚለው መረን የለቀቀ ጣልቃ ገብነታቸው ከምኞት ባያልፍም ዋጋ አስፍሎናል፡፡ እኛ ግን በየግንባሩ የተከፈተብንን ዘመቻ በጋራ በመመከት እጣ ፈንታችን እንደ ሀገር በአንድ ላይ የተሰናሰለ በቀላሉ የማንሰበርና የማንበታተን ጠንካራ ሕዝብ መሆናችንን በዓለም አደባባይ አስመስክረናል፡፡

በነዚህ ዓመታት በአንድ በኩል ችግሮችን በመቀልበስና የሀገር አንድነትን በማስጠበቅ በሌላ በኩል ልማትን በማፋጠን የለውጥ አመራሩ ቃሉን ሳያጓድል ቀጥሏል፡፡ እንደ ሀገር ያነገብነው ራዕይ እና ሕዝቡ የሰጠን አደራ ከሚፈታተኑን ችግሮች በላይ ናቸውና የብልፅግና ጉዟችን ከስኬት ማማ ሳይደርስ አይቆምም፡፡ የሰፊውን ሕዝብና የሀገርን ተስፋ ያለመለሙትን የለውጡን መልካም ወረቶች እያካበትን የፍርሃት ቆፈን ለብሶ ከፊታችን የቆመውን ፀረ ለውጥ ሃይል አልፈንው እንሄዳለን፡፡
#Prosperityparty #prosperity
2.7K views06:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 09:16:33
1.8K views06:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 11:43:22
የተጠና እርምጃ በመውሰድ በአሸባሪው ሸኔ ላይ ኪሳራ ማድረስ ተችሏል - የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

የተጠና እርምጃ በመውሰድ በአሸባሪው ሸኔ ላይ ኪሳራ ማድረስ መቻሉን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ፡፡

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫቸውም፥ የአሸባሪው ሸኔን ጥቃትን የመከላከልና ቡድኑን የማስወገድ ዘመቻዎች ሲካሄዱ መቆየታቸውን አንስተዋል፡፡

በተለይ በኦሮሚያ ክልልና አዋሳኝ አካባቢዎች የሽብር ቡድኑ እየረበሸ እንደሚገኝ አንስተው፥ በፌዴራልና ኦሮሚያ ክልል የጸጥታ ሃይሉ ጥምረት ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ዘመቻው ሲካሄድ መቆየቱን ገልጸዋል፡፡

በዘመቻውም ትልልቅ ስኬቶች ተመዝግበዋልም ነው ያሉት፡፡

ሲወሰዱ የነበሩ ዘመቻዎች በተጠኑ ቦታዎች ላይና የተወሰኑ ቦታዎች ዒላማ በማድረግ የሽብር ቡድኑን እንቅስቃሴ ከግምት ውስጥ በማስገባት ሲካሄድ መቆየታቸውን አመልክተዋል፡፡

እንደአብነት ከጥቂት ቀናት በፊት የተወሰደውን እርምጃ አስመልክቶ እንዳሉት ፥ በሆሮጉድሩ ወለጋ ዞን የሱሉላ ፊንጫ ወረዳ ላይ በተፈጸመው እርምጃ በርካታ የሸኔ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ ተወስዷል ነው ያሉት፡፡

በአካባቢው የፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ይዞታ የሸንኮራ አገዳ ማሳ ውስጥ በመሸሸግ የተከፈተባቸውን እርምጃ ለመሸሽ ሲሞክሩ እንደነበር አንስተዋል፡፡

በዚህም የተጠና እርምጃ በመውሰድ በአሸባሪው ሸኔ ላይ ኪሳራ ማድረስ ተችሏል ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ፡፡
2.0K viewsedited  08:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 17:20:06
አገራችን ኢትዮጵያ በታሪክ መዝገብ ውስጥ በደማቅ ቀለም ተጽፋ የምትገኝ፤ ከአለም ስልጣኔ በፊት የስልጣኔ ባለቤት የነበረች የመቻቻል እና የብዝሃነት አገር ናት፡፡ ኢትዮጵያ ታላቅ አገር ናት ሲባልም እንደው በቃል ብቻ ለማለት ሳይሆን በተጨባጭ ታላቅነቷን የሚመሰክሩ በርካታ መገለጫዎች ስላሏት ጭምር ነው።

ኢትዮጵያን በማንም ሃይል ፍላጎትም ሆነ ንግግር ዝቅ ማድረግ እንዳይቻል አድርገው ከፍ ያደረጓት አባቶቻችንን ስብዕና ተላብሰን እና አገር ከፍ ስትል ከፍ የሚለው የዜጎቿ ክብር መሆኑን በመገንዘብ ሁሌም ቢሆን እንደታሪካችን ንግግራችንም ተግባራችንም ኢትዮጵያን የሚመጥን ሊሆን ይገባል፡፡

ኢትዮጵያን ለማሻገር በሚደረገው የትግል ምዕራፍ የሚገጥሙ ችግሮች ሁሉ በጽናታችን ልክ የምንሻገራቸው እንጂ ወደፊት ከመገስገስ የሚያቆሙን ሊሆኑ አይገባም፡፡ የትናንት ታሪካችን የሚያስተምረን ይሄንኑ ነውና፡፡ በመሆኑም ዛሬም፣ ነገም፣ ወደፊትም በጽናት በመቆም ትኩረታችን ችግሮቻችንን ከስር ከስር እየነቀሉ ኢትዮጵያን ማጽናት ላይ ሊሆን ይገባል፡፡

የኢትዮጵያን ብልጽግና ማረጋገጥ የሚቻለውም ችግር የማይበግረውና በአገራዊ ጥቅሙ የማይደራደር ጽኑ ትውልድ በመገንባት ብቻ ነው፡፡
2.4K views14:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 15:11:57
የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ በብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅ/ቤት ቅጥር ጊቢ ውስጥ እየተሰሩ ያሉ የአረንጓዴ አሻራ እንቅስቃሴዎችን ጎብኝተዋል፡፡
አቶ አደም በጉብኝቱ ወቅት የተተከሉ ችግኞች ለምግብነት የሚውሉ እና በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚደርሱ መሆናቸው በበጎ የሚታይ እንደሆነ ገልፀው የተጀመሩ እንቅስቃሴዎች አበረታች እንደሆኑ እና ይበልጥ ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
ፅ/ቤቱም ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት በመስጠት ተጨማሪ ባለሙያዎችን ጭምር በመመደብ የተጀመሩ እንቅስቃሴዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡
በጅምር ላይ ያሉ ተግባራትም በሳይንሳዊ መንገድ እየዳበሩ መቀጠል እንደሚገባቸውና የዋና ፅ/ቤቱ ተሞክሮዎች በሁሉም ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች ውስጥ መስፋፋት እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡
1.9K views12:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ