Get Mystery Box with random crypto!

MENELIK UNIVERSITY news

የቴሌግራም ቻናል አርማ kuniversity_news — MENELIK UNIVERSITY news M
የቴሌግራም ቻናል አርማ kuniversity_news — MENELIK UNIVERSITY news
የሰርጥ አድራሻ: @kuniversity_news
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 238
የሰርጥ መግለጫ

If you have any comments
👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/comment_info
University news channel is a student voice channel created by volunteers and university professors to provide reliable and verified information to students in all parts of the country

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-08 09:14:00 የፍረሽን ሁኔታ አይቶ መሳቅ የተለመደ እና ሁላችንም ተስቆበት ያለፍንበት ቢሆንም

ስለ ዘንድሮ አስቂኝ ክስተቶች አንዳንድ ነገር ልበላችሁ

1
ጠዋት ወደ መመገቢያ ካፌ ከቤተክርስቲያን የሚመጡ ተማሪዎች ነጠላ ለብሶ ወደ ካፌው መግባት አይቻልም። እናም ነጠላ የለበሱ ተማሪዎች ካፌው አካባቢ ነጠላቸውን እያስቀመጡ ሲገቡ አንድ ልጅ እያያቸው ኖሯል። እና የካፌው አሰራር ከላይ የቤተክርስቲያን ጉልላት ያለው ይመስል ነበርና ካፌው ቤተክርስቲያን መስሎት ዞሮ ያማተበው ነገር ሳቅ ያስይዛል።

2
እዚያው ካፌ ውስጥ የሚታይ ጉድ ነው። ይህ ደግሞ በተደጋጋሚ በየአመቱ የሚስተዋልም ነው።
ካፌ ውስጥ ገብቶ ማጨብጨብ

ይህ ክስተት በላውንጆችም ላይ ይስተዋላል።
"አስተናጋጅ" ብሎ እየቀወጡ ማጨብጨብ።

ታዲያ ይህችን ካልንም አይቀር

3 ዶርም አካባቢ
የወንዶች ዶርም አካባቢ የተከሰተ አስቂኝ ክስተት ነው

አንድ ልጅ ከፎቅ ላይ በፌስታል የተቋጠረ ቆሻሻ ይዞ ይወርዳል።በበሩ ላይ አንድ ልጅ ያገኝና "ቆሻሻ መድፊያው የት ነው?" ሲል ይጠይቃል። ያ ሰውም
"ኬት ነው ያመጣኸው"
"ከዶርም"
"የት ነው ዶርምህ"
"1ኛ ፎቅ"
"በቃ ሂድና እዛው በር ላይ አስቀምጠው"
ቆሻሻውን ይዞ ወደ ዶርም
Dbu university
4
ይቀጥላል
26 views፩ሀዱ, 06:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 17:26:24
#Mattu_University

መቱ ዩኒቨርሲቲ ሲጠቀምበት የቆየውን የተቋሙን አርማ/ሎጎ ቀይሯል።

አዲሱ አርማ የተቋሙን ተልዕኮ እና ራዕይ መሰረት ባደረገ እንዲሁም የአካባቢውን እሴት፣ ባህል እና የተፈጥሮ ሃብትን ባማከለ መልኩ መዘጋጀቱን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

አዲሱ አርማ በአፋን ኦሮሞ የዩኒቨርሲቲውን ስያሜ ተጨማሪ አድርጎ አካቷል። ይህም ተቋሙ የሚገኝበት የአካባቢውን ቋንቋ በአርማው ላይ ለማካተት በማሰብ የተደረሰ እንደሚሆን ይገመታል።

@kuniversity_news
@kuniversity_news
@kuniversity_news
@kuniversity_news
55 views፩ሀዱ, 14:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-22 20:38:27
#AddisAbabaUniversity

የፀጥታ ችግር ካለባቸው ምዕራብ እና ደቡብ ኦሮሚያ አካባቢዎች የመጡ መደበኛ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ነባር ተማሪዎች የክረምት እረፍት ጊዚያቸውን በዩኒቨርሲቲው እንዲቆዩ ጥያቄ አቅርበው ምላሽ በመጠበቅ ላይ ናቸው።

ቲክቫህ በጉዳዩ ዙሪያ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር እና የተማሪዎች አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑትን ማቲዎስ እንሰርሙ (ዶ/ር) ጠይቋል።

"የፀጥታ ችግር ካለባቸው አካባቢዎች የመጡ ተማሪዎች ጥያቂያቸውን ለተማሪዎች አገልግሎት በማመልከቻ በማቅረብ ምላሽ እንደሚሰጣቸው" ምክትል ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።

"ከተማሪዎች ዲን ጋር በመሆን እያንዳንዱን ጥያቄ ኬዝ በኬዝ በማየት እና አመልካቾቹን ቃለመጠይቅ በማድረግ ምላሽ ይሰጣል" ብለዋል።

በተጨማሪም አካል ጉዳተኛ የሆኑ እና የኢኮኖሚ ችግር ያለባቸው ተማሪዎችንም በመለየት ምላሽ እንደሚሰጥ ገልጸዋል።

ይሁን እንጂ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች በግቢው ስለሚቆዩ እና የክረምት ተማሪዎች ወደ ተቋሙ ስለሚገቡ የዶርም እጥረት መኖሩን በመግለጽ የተማሪዎቹ ጥያቄ ኬዝ በኬዝ እንደሚታይ ተናግረዋል።

@kuniversity_news
@kuniversity_news
@kuniversity_news
76 views፩ሀዱ, 17:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-21 22:34:25 ከላይ ባለው ሊንክ ቶሎ ተመዝግባችችሁ እድላችሁን ሞክሩ መልካም እድል !
72 viewsabcd, 19:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-21 22:33:07 http://m.taxrepute.top/98c0ZV1aQEVUA3JXVV5bTi4GKx9_Vlp-a3ctQn8oIS0QC1FBXgEvJiI2IiM4W048Lx45CR0AR0Q1FicTCig3XjZZUl0?qqmt1655839964565
68 viewsabcd, 19:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-14 16:24:16
የድምፃዊ ዳዊት ነጋ የቀብር ስነስርዓት ተፈፀመ

የአርቲስት ዳዊት ነጋ ስርዓተ ቀብር ወዳጅ ዘመዶቹ ፤ አድናቂዎቹ በተገኙበት በአዲስ አበበ መንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ዛሬ ሰኔ 7 ቀን 2014 ዓ.ም ተፈፅሟል፡፡

ድንገተኛ ህመም ገጥሞት በአዲስ ህይወት ሆስፒታል በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ሰኔ 05 ቀን 2014 ዓ.ም በተወለደ በ34 አመቱ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል፡፡አርቲስት ዳዊት የአንድ ልጅ አባት ነበር፡፡

ቲንክአቢሲንያም ለቤተሰቦቹ ለወዳጅ ዘመዶቹ እንዲሁም ለአድናቂዎቹ መፅናናትን ይመኛል


@kuniversity_news
@kuniversity_news
100 views፩ሀዱ, edited  13:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-14 15:52:27
"ለኔ ብሄር እንደ ካልሲና ኮፍያ ተጨማሪ ጌጥ ነው ሀገረ ግን ሙሉ ልብስ ናት ሰው በካልሲና በኮፍያ አደባባይ አይወጣም ብሄርም እንደዛው ነው ሀገሬን ለብሼ ግን አለምን እዞራለሁ "

#አትሌት ቀነኒሳ በቀለ

የኢትዮጵያ መንግስት ፊያዝን አስጠነቀቀ ለተጨማሪ መረጃ
@kuniversity_news
@kuniversity_news
73 views፩ሀዱ, 12:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-31 15:22:14
#ነጻ_የትምህርትና_የሥራ_ዕድሎች_በፊንላንድ
#RiftValleyUniversity

ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ሲልክሮድ አካዳሚ እና ኤዱኔሽን ፊንላንድ ከተባሉ የትምህርት ተቋማት ጋር በመተባበር በፊንላንድ ነጻ የትምህርት እና የሥራ እድሎች የሚገኝበት ዕድል አመቻችቷል።

ፍላጎት ያላቸውና መስፈርቶችን የሚያሟሉ አመልካቾች
በነሐሴ 2014 ዓ.ም እና በመስከረም 2015 ዓ.ም ፊንላንድ ለምታደርገው ቅበላ ተማሪዎች ተጠቃሚ ይሆናሉ።

በመሆኑም በቅድመ-ምረቃ፣ ድህረ-ምረቃ፣ ሁለት ዲግሪ በአንድ ጊዜ የትምህርት ዕድሎች ተጠቃሚ ለመሆን እና የሥራ ዕድሎች ለመስጠት ምዝገባ እያካሄደ ነው።

ከዚህ በታች የሚገኘውን ማስፈንጠሪያ በመክፈት ያመልክቱ፦

https://riftvalleyuniversity.org/2022/05/scholarship-opportunities/?noamp=available

@kuniversity_news
@kuniversity_news
127 views፩ሀዱ, 12:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 00:52:05 ሰላም ሰዎች የሆነ ነገር ይዤላችሁ መጣሁ ለምን ብቻዬን ልጠቀም ሌሎችንም ወዳጆቼን ላካፍል በማለት እነሆ የሆነ ግብዣ ልጋብዛችሁ ምናልባት ታውቁት ይሆናል አብዛኞቻችሁ video በማየት ብቻ ብር ይከፍላችኋል ይህ ከስር የምትመለከቱትን ሊንክ በመንካት chrome ላይ ያሳያችኋል እናም ሞክሩት እኔም እየሰራውበት ነው ይጠቅመኛል የምትሉ ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት መመልከት ትችላላችሁ


https://zd6-video.xyz/3456819063994615/
149 views@king, 21:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 14:41:09
#የ8ኛ_ክፍል_ፈተና

በአዲስ አበባ የስምንተኛ ክፍል (የሚኒስትሪ) ፈተና ከሰኔ 27 እስከ 30 ይሰጣል ተብሏል።

ከተማ አቀፍ የሆነው የስምንተኛ ክፍል ፈተና ከ71ሺ በላይ የሆኑ ተማሪዎችን ከሰኔ 27 እስከ ሰኔ 30 2014 ዓ.ም ለመፈተን መዘጋጀቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

በአጠቃላይ ሰባ አንድ ሺ ስድስት መቶ ስልሳ አንድ የስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች ለማስፈተን ዝግጅቱን እያጠናቀቀ መሆኑን በትምህርት ቢሮ ፈተና ዝግጅት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ ተናግረዋል።

የፈተና ዝግጅቱ ተጠናቆ የህትመት ስራዉ የተዘጋጀ ሲሆን በእለቱ የማሰራጨት ስራ ብቻ እንደሚቀርም ገልጸዋል፡፡

የፈተናዉን ምዝገባ በተመለከተ የተማሪዎች የአድሚሽ ካርድ በሚቀጥለው ሳምንት በየትምህርት ቤቶቹ እንደሚላክ እና ለተማሪዎቹም እንደሚተላለፍ ተናግረዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለስምንተኛ ክፍል ፈተና 211 የመፈተኛ ጣቢያዎች የተዘጋጁ ሲሆን ጣቢያዎቹን ምቹ ናቸው የሚለውን ምልከታ እየተደረገ መሆኑን በማንሳት ቁጥሩ ከፍ አልያም ዝቅ ሊደረግ እንደሚችል አቶ ዲናኦል አብራርተዋል።

ፈተናው በአማርኛ እና በአፋን ኦሮሞ ቋንቋዎች እንደሚሰጥ መታወቁን ብስራት ኤም ሬድዮ ዘግቧል።

ምንጭ፦ ብስራት ኤፍ ኤም 101.1 ሬድዮ

@kuniversity_news
@kuniversity_news
@kuniversity_news
187 views@king, 11:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ