Get Mystery Box with random crypto!

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ በጎ አድራጎት ማዕከል(ቻሪቲ)

የቴሌግራም ቻናል አርማ amubegoaderagotmahkele — የአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ በጎ አድራጎት ማዕከል(ቻሪቲ)
የቴሌግራም ቻናል አርማ amubegoaderagotmahkele — የአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ በጎ አድራጎት ማዕከል(ቻሪቲ)
የሰርጥ አድራሻ: @amubegoaderagotmahkele
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 238
የሰርጥ መግለጫ

#የማዕከሉ አላማ
♣እናትና አባት የሌላቸው ወይም ወላጅ አልባ ህፃናትን መርዳት።
♣ጧሪ የሌላቸው አረጋውያንን መርዳት።
♣ በዩኒቨርስቲው ውስጥ የሚገኙ ችግረኛ ተማሪዎችን ይረዳል።
♣ ፈቃደኛ ከሆኑ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች የተለያዩ አልባሳት በማሰባሰብ
በተለየዩ ምክኒያቶች የተቸገሩ ሰወችን መርዳት።

#ስራችን ለማገዝ እና ለመሳተፍ ከፈለጉ
251926940304

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-02 04:33:26
የኔ ጀግኖች
እንኳን በተስፋ ለጠበቃችኋት የምርቃት ቀናችሁ አደረሳችሁ

ይህ ጅማሬያችሁ እንጂ ማለቂያው አይደለምና ገና በብዙ ይጠብቃችኋለሁ


ስም እንዳልጠራ ፈራሁ መርሳት እንዳይሆንብኝ ብዬ
ከግቢ ቆይታቸው ላይ ለሌሎች እራሳቸውን ላካፈሉ ለሌሎች እህት ወንድም ለሆኑ ለቻሪቲ ምርጥ ቤተሠቦች እንኳን ደስ አላቹ በምትሰማሩበት የስራ መስክ ሁሏ መልካም ነገር ይግጠማችሁ ቤታችሁን እንዳትረሱ አደራ እላለሁ መልካም በዓል በድጋሚ
47 views01:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-03 20:58:04
ልብ ጠጋኟ ጋዜጠኛ ህይወት ታደሰ
(በ የኋላእሸት ዘሪሁን)
የኢትዮጵያ የልብ ህሙማን መርጃ ማዕከል በጎ አድራጊ ጋዜጠኛ ህይወት ታደሰ ፤ ማህበራዊ ሚድያን ለሰብዓዊነት በመጠቀም ያሰባሰበችው 1.2 ሚሊዬን ብር የገንዘብ ድጋፍ ርክክብ አተደረገ።

የኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህፃናት መርጃ የልብ ቀዶ ጥገናን ጨምሮ ሁሉንም የህክምና አገልግሎቶች ያለምንም ክፍያ በነፃ እንደመስጠቱ አላቂ እቃዎችን ለማሟሟላት ያለበትን ችግር ለመቅረፍ ከማሕበረሰቡ በሚሰበሰብ እርዳታ፣ ከሀገር በቀል እና የውጪ ድርጅቶች በሚደረግ ድጋፍ እና ሌሎችም እገዛዎች ወጪዎሽን በመሸፈን ማሕበረሰቡን እያገለገለ ይገኛል፡፡
ኗሪነቷን በሰሜን አሜሪካ ያደረገችው እና ላለፉት ሦስት ዓመታት ማህበራዊ ሚድያን ለሰበዓዊነት በመጠቀም እና በመርዳት የምትታወቀው በጎ አድራጊ ጋዜጠኛ ህይዎት ታደሰ ከማህበራዊ ሚድያ ያሰባሰባቸውን 1.2 ሚሊዬን ብር የገንዘብ ድጋፍ ለማዕከሉ አስረክባለች ፡፡
ሂወት ታደሰ ባለፉት ሶስት አመታት 30 የልብ ሙማን ህፃናት ያሳከመች ሲሆን። በመላው ኢትዮጵያ 7000 የሚሆኑ ህፃናት ወረፋ በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ።
የበጎ አድራጊዋ ጋዜጠኛ ህይዎት ታደሰ ወኪሎች፣ የማዕከሉ አመራሮች እንዲሁም ታካሚ ህጻናት በተገኙበት ፣ ዛሬ ግንቦት 26 ቀን 2014ዓ/ም ፤ጥቁር አንበሳ ግቢ ውስጥ በሚገኘው የማዕከሉ ውስጥ ርክክቡ ተደርጓል፡፡
112 views17:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-09 09:51:17
163 views06:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-09 09:51:17
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በጎ አድራጎት ማእከል (Charity) በቀን 29/08/2014 ዓ.ም በ ቁጥረ 3እና 4 ካፌ ውስጥ በ ምሳ ሰዓት (5:30-7:00) ላይ የማስተናገድ ስራን ሰርቷል።
136 views06:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-08 12:08:46 በአርባ ምንጭ ዮኒቨርስቲ በዋናው ግቢ እየተከናወነ በሚገኘው የቴክኖ ካፕ የእግር ኳስ ውድድር በትላንትናው እለት የ mechanical vs irrigation ጨዋታ ከመጀመሩ በፊት ሁሉም ከመቀመጫው በመነሳት ለተማሪ ዳዊት ጥላሁን የአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት ተደርጓል::

ነብስ ይማር
109 views09:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-07 22:52:47
የክብር ዶክተር ወ/ሮ አበበች ጎበና ታሪክ

አበበች ጎበና ኢትዮጵያ ውስጥ አገር በቀል የእርዳታ ሰጪ ድርጅት ያቇቇሙ ሴት ሲሆኑ "የአፍሪካዋ ማዘር ተሬዛ" በመባል ይጠራሉ። "የኢትዮጵያ ሴቶች እንቅሥቃሤ በ20ኛው ክፍለ ዘመን" በሚለው መፅሃፍ እንደተገለፀው በ1938 ሸዋ ውሥጥ በበፊቱ አጠራር ሠላሌ አውራጃ ልዩ ሥሙ ሸበል በሚባል ቦታ ነው የተወለዱት። አበበች ጎበና ያደጉት ከአያታቸው ጋር ነው። ይህም የሆነበት ምክንያት አባታቸው ሕፃን እያሉ በጣልያኖች ሥለተገደሉ ነው። አበበች ጎበና የመጀመሪያ ባላቸውን ገና ትንሽ ልጅ እያሉ በቤተሠብ እና በዘመድ ግፊት ቢዳሩም ዘመዶቻቸው እንዳሠቡት ትዳራቸው ሣይሠምር ወዲያው አገራቸውን ጥለው ወደ አዲስ አበባ መጡ። አዲስ አበባም ትዳር ይዘው መልካም ትዳርን ለመምሥረት በቁ።

የክብር ዶክተር ወ/ሮ አበበች ጎበና ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ያቀኑት ግሸን ማርያም ለንግሥ በዐል ነበር በሄዱበት ጊዜም በወቅቱ በኢትዮጵያ ደርሶ በነበረው ድርቅ ምክንያት በሀገሪቱ የረሃብ አደጋ ያጠላበት ጊዜ ነበርና አንዲት ሕፃን የእናቷ አስክሬን እቅፍ ስር ሆና ጡት ለመጥባት ትሞክራለች። ይህ ትዕይንት እጅግ ከፍተኛ ሐዘን ውስጥ ይከታቸዋል። ሕፃኗን ከሌላ አንዲት ሕፃን ጋር ይዘውም ለማሳደግ ይወስዳሉ። አበበች ጎበና እንደዚህ እያሉ ነው የበጎ አድራጎት ድርጅታቸውን ለመክፈት ያበቃቸውን ጉዞ የጀመሩት። 21 ሕፃናትን ለመርዳት ያሰባስባሉ ሆኖም ባለቤታቸው እና የሥራ አለቃቸው ከሕፃናቱ ወይ ከእኔ አለያም ከሥራዎ የሚል ከባድ አጣብቂን ውስጥ ይከቷቸዋል። ሆኖም
እሳቸው ለሕፃናቱ ይወስናሉ በዚህም የተነሣ ትዳራቸው እንደፈረሠ ይነገራል ።

በአሁኑ ወቅት የክብር ዶክተር ወ/ሮ አበበች ጎበና በኢትዮጵያ የተለያዩ ቦታዎች ከ12 ሺህ በላይ ሕፃናትን ይረዳሉ። በእሳቸው የርዳታ ድርጅት ሥር ከ1,5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ተጠቃሚ መሆናቸው ይነገራል። በሰብአዊ ርዳታ ለጋሽ ድርጅታቸው 265 ቋሚ እንዲሁም 400 ሌሎች ሠራተኞችን ቀጥረው የሰራሉ ።

ወይዘሮ አበበች ጎበና ፥ የክብር ዶክተር አበበች ጎበና የኢትዮጵያ ማዘር ቴሬዛ ፥ ወዘተ በሚሉ መጠሪያዎች ይታወቃሉ። በእንግሊዝኛ አህጽሮቱ ሲድ ተብሎ የሚታወቀው መሠረቱን ዩናይትድ ስቴትስ ያደረገ የኢትዮጲያውያን የሽልማት ድርጅት ማህበረ ግዩራን ዘረ ኢትዮጲያ ዘንድሮ ካከበራቸውና ከሸለማቸው ለማህበረሰባቸው ታላላቅ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ኢትዮጲውያን መካከል አንዱዋ ነበሩ ። በሺህ ዘጠኝ መቶ ሰባዎቹ በኢትዮጲያ በደረሰው ድርቅና ረሃብ ወቅት ወደግሸን በሄዱበት ጉዞአቸው በረሃቡ ህይወቱዋ ያለፈ እናቱዋን ጡት ስትጠባ ያገኙዋትን ህጻን አንስተው ወደቤታቸው ይዘው ከሄዱ ወዲህ ህይወታቸውን ወላጅ ለሌላቸው ህጻናት ባጠቃላይ ለችግረኞች የሰጡ የሺዎች እናት ናቸው
እዳዬ (እማዬ) እናመሰግናለን
እንወድሻለን



@MGK art
115 views19:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ