Get Mystery Box with random crypto!

የክብር ዶክተር ወ/ሮ አበበች ጎበና ታሪክ አበበች ጎበና ኢትዮጵያ ውስጥ አገር በቀል የእርዳታ | የአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ በጎ አድራጎት ማዕከል(ቻሪቲ)


የክብር ዶክተር ወ/ሮ አበበች ጎበና ታሪክ

አበበች ጎበና ኢትዮጵያ ውስጥ አገር በቀል የእርዳታ ሰጪ ድርጅት ያቇቇሙ ሴት ሲሆኑ "የአፍሪካዋ ማዘር ተሬዛ" በመባል ይጠራሉ። "የኢትዮጵያ ሴቶች እንቅሥቃሤ በ20ኛው ክፍለ ዘመን" በሚለው መፅሃፍ እንደተገለፀው በ1938 ሸዋ ውሥጥ በበፊቱ አጠራር ሠላሌ አውራጃ ልዩ ሥሙ ሸበል በሚባል ቦታ ነው የተወለዱት። አበበች ጎበና ያደጉት ከአያታቸው ጋር ነው። ይህም የሆነበት ምክንያት አባታቸው ሕፃን እያሉ በጣልያኖች ሥለተገደሉ ነው። አበበች ጎበና የመጀመሪያ ባላቸውን ገና ትንሽ ልጅ እያሉ በቤተሠብ እና በዘመድ ግፊት ቢዳሩም ዘመዶቻቸው እንዳሠቡት ትዳራቸው ሣይሠምር ወዲያው አገራቸውን ጥለው ወደ አዲስ አበባ መጡ። አዲስ አበባም ትዳር ይዘው መልካም ትዳርን ለመምሥረት በቁ።

የክብር ዶክተር ወ/ሮ አበበች ጎበና ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ያቀኑት ግሸን ማርያም ለንግሥ በዐል ነበር በሄዱበት ጊዜም በወቅቱ በኢትዮጵያ ደርሶ በነበረው ድርቅ ምክንያት በሀገሪቱ የረሃብ አደጋ ያጠላበት ጊዜ ነበርና አንዲት ሕፃን የእናቷ አስክሬን እቅፍ ስር ሆና ጡት ለመጥባት ትሞክራለች። ይህ ትዕይንት እጅግ ከፍተኛ ሐዘን ውስጥ ይከታቸዋል። ሕፃኗን ከሌላ አንዲት ሕፃን ጋር ይዘውም ለማሳደግ ይወስዳሉ። አበበች ጎበና እንደዚህ እያሉ ነው የበጎ አድራጎት ድርጅታቸውን ለመክፈት ያበቃቸውን ጉዞ የጀመሩት። 21 ሕፃናትን ለመርዳት ያሰባስባሉ ሆኖም ባለቤታቸው እና የሥራ አለቃቸው ከሕፃናቱ ወይ ከእኔ አለያም ከሥራዎ የሚል ከባድ አጣብቂን ውስጥ ይከቷቸዋል። ሆኖም
እሳቸው ለሕፃናቱ ይወስናሉ በዚህም የተነሣ ትዳራቸው እንደፈረሠ ይነገራል ።

በአሁኑ ወቅት የክብር ዶክተር ወ/ሮ አበበች ጎበና በኢትዮጵያ የተለያዩ ቦታዎች ከ12 ሺህ በላይ ሕፃናትን ይረዳሉ። በእሳቸው የርዳታ ድርጅት ሥር ከ1,5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ተጠቃሚ መሆናቸው ይነገራል። በሰብአዊ ርዳታ ለጋሽ ድርጅታቸው 265 ቋሚ እንዲሁም 400 ሌሎች ሠራተኞችን ቀጥረው የሰራሉ ።

ወይዘሮ አበበች ጎበና ፥ የክብር ዶክተር አበበች ጎበና የኢትዮጵያ ማዘር ቴሬዛ ፥ ወዘተ በሚሉ መጠሪያዎች ይታወቃሉ። በእንግሊዝኛ አህጽሮቱ ሲድ ተብሎ የሚታወቀው መሠረቱን ዩናይትድ ስቴትስ ያደረገ የኢትዮጲያውያን የሽልማት ድርጅት ማህበረ ግዩራን ዘረ ኢትዮጲያ ዘንድሮ ካከበራቸውና ከሸለማቸው ለማህበረሰባቸው ታላላቅ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ኢትዮጲውያን መካከል አንዱዋ ነበሩ ። በሺህ ዘጠኝ መቶ ሰባዎቹ በኢትዮጲያ በደረሰው ድርቅና ረሃብ ወቅት ወደግሸን በሄዱበት ጉዞአቸው በረሃቡ ህይወቱዋ ያለፈ እናቱዋን ጡት ስትጠባ ያገኙዋትን ህጻን አንስተው ወደቤታቸው ይዘው ከሄዱ ወዲህ ህይወታቸውን ወላጅ ለሌላቸው ህጻናት ባጠቃላይ ለችግረኞች የሰጡ የሺዎች እናት ናቸው
እዳዬ (እማዬ) እናመሰግናለን
እንወድሻለን



@MGK art