Get Mystery Box with random crypto!

የጻድቅ ሰው ህይወት ምን ይመስላል? በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለ ጻድቅ ሰው ህይወት በተመለከተ መጽ | የእግዚአብሔር ጸጋ ወንጌል\ The Gospel of the grace of God\

የጻድቅ ሰው ህይወት ምን ይመስላል?

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለ ጻድቅ ሰው ህይወት በተመለከተ መጽሐፍ ምን ይላል፦

“ጻድቅ በእምነት ይኖራል ተብሎ እንደ ተጻፈ የእግዚአብሔር ጽድቅ ከእምነት ወደ እምነት በእርሱ ይገለጣልና።”
— ሮሜ 1፥17


ጻድቅ በእምነት ይኖራል ማለት የጻድቅ ሰው መኖሪያ እምነት እያለን ነው። ጻድቅ ከእምነት ውጭ ምንም አይነት የህይወት ስርዓት የለም።

እምነት የጻድቅ ሰው መተንፈሻ ኦክስጅን ነው፤ ማንም የሰው ልጅ በምድር ላይ ያለ ኦክስጅን መኖር እንደማይችል ሁሉ፣ ልክ እንደዚያ ደግሞ ጻድቅ ሰው ያለ እምነት መኖር እንደማይችል ግልጽ ነው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ በተደጋጋሚ ተጽፎ የምታገኘው ቃል ቢሆን "ጻድቅ በእምነት ይኖራል" የሚል ሀሳብ ታገኛለህ። ይህ የሆነበት ምክንያት ደግሞ ጻድቅ ሰው የህይወቱ ስርዓት በሙሉ በእምነት ስለሆነ ነው።

ጻድቅ መኖሪያው ገንዘቡ ወይም ደሞዙ ወይም ስራው ሳይሆን ጻድቅ መኖሪያው እምነት ነው።

“ዓለማት በእግዚአብሔር ቃል እንደ ተፈጠሩ በእምነት እንረዳለን፤ ስለዚህ የሚታየው ነገር የተፈጠረው ከሚታየው እንዳልሆነ እንገነዘባለን።”
— ዕብራውያን 11፥3 (አዲሱ መ.ት)

ስለዚህ ከመንፈሳዊ ዓለም ያለውን መልካም ነገር ወደ ስጋዊ ዓለም የምንቀበለው በእጃችን ሳይሆን በእምነታችን ነው።

ይቀጥላል
የእግዚአብሔር ሰው ኤፍሬም ገ/ኢየሱስ


https://t.me/PRAISE_TO_OUR_GOD