Get Mystery Box with random crypto!

ክፍል አራት #የእግዚአብሔር_ጽድቅ_በወንጌል_ተገልጧል። “በወንጌል የእግዚአብሔር ጽድቅ ተገልጦአ | የእግዚአብሔር ጸጋ ወንጌል\ The Gospel of the grace of God\

ክፍል አራት

#የእግዚአብሔር_ጽድቅ_በወንጌል_ተገልጧል።

“በወንጌል የእግዚአብሔር ጽድቅ ተገልጦአልና፤ ጽድቁም ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ በእምነት የሆነ ነው፣ “ጻድቅ በእምነት ይኖራል” ተብሎ እንደ ተጻፈው።”
  — ሮሜ 1፥17 (አዲሱ መ.ት)

በመጀመሪያ ደረጃ ወንጌል ምንድነው?

ወንጌል ተብሎ የተተረጎመዉ የግሪኩ ቃል Euaggelion የሚል ነው፤ ትርግሙም መልካም ዜና ማለት ነው። በዚህም፣ መልካም ዜና ያልሆነ ሁሉ ወንጌል አይባልም።

#ወንጌል_ማለት_ለማመን_የሚከብድ_የምስራች_ነው። ይህ የምስራች ደግሞ ለሰው ሁሉ የሚነገር መልካም ዜና ነው።

“በወንጌል አላፍርም፤ ምክንያቱም ለሚያምን ሁሉ ለድነት የሚሆን የእግዚአብሔር ኀይል ነው፤ ይህም በመጀመሪያ ለአይሁድ፣ ቀጥሎም ለአሕዛብ ነው።”
  — ሮሜ 1፥16 (አዲሱ መ.ት)

#_ወንጌል_ማለት_የእግዚአብሔር_ጽድቅ_የተገለጠበት_ታላቅ_የምስራች_ነው።
ሐዋርያው ጳውሎስ በወንጌል አላፍርም ያለበት ዋነኛ ምክንያት የእግዚአብሔር ጽድቅ የተገለጠበት መንገድ ስለተረዳ ነው። ወንጌል አያሳፍርም፤ ምክንያቱም ደግሞ ለሚያምን ሁሉ ድነት የሚሆን የእግዚአብሔር ሀይል ስለሆነ ነው።

#ደህንነት ኃጢአተኛው ሰው በመስቀል ሥራ የጸደቀበት ብቻ ሳይሆን ይህንን #የጽድቅ_ሕይወት_መኖር_የሚችልበትን_የእግዚአብሔር_ኃይል_ያገኘበት_ነው።

ወንጌል ለሰው ልጆች ሀጢአት አይናገርም፤ ወንጌል የሚናገረው ስለ እግዚአብሔር ጽድቅ ነው።

በወንጌል የተገለጠው የእግዚአብሔር ጽድቅ ሰዎች ሁሉ በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን የሚገኘው ጽድቅ በእምነት እንዲቀበሉ የሚያደርግ የምስራች ነው።

#ወንጌል_የተገለጠው_የእግዚአብሔር_ጽድቅ_እንጂ_ሀጢአት_አይደለም።

   ይቀጥላል
የእግዚአብሔር ሰው ኤፍሬም ገ/ኢየሱስ

https://t.me/PRAISE_TO_OUR_GOD