Get Mystery Box with random crypto!

ታታ አፍሮ -Tata Afro

የቴሌግራም ቻናል አርማ poettataafro — ታታ አፍሮ -Tata Afro
የቴሌግራም ቻናል አርማ poettataafro — ታታ አፍሮ -Tata Afro
የሰርጥ አድራሻ: @poettataafro
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.29K
የሰርጥ መግለጫ

ታታ አፍሮ ገጣሚና ጦማሪ ነኝ። ወጎች እና መጣጥፎችን እደርሳለሁ። ፖለቲካዊ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ሀይማኖታዊ ጉዳዮች ላይ ግጥሞችን እንዲሁም ጦማሮችን አዘጋጃለሁ። አፍሪካዊ እና ዓለም አቀፋዊ ታሪኮችን በዚሁ ቻናል እንዳስሳለን..
#Instagram፦ www.instagram.com/tataafro_official

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-27 19:29:39
የአክብሮት ሰላምታዬን በማስቀደም ከሰሞኑ በምድረ አሜሪካ ኦሪገን ግዛት ተካይዶ በነበረው 18ተኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በተቀዳጀነው አንፀባራቂ ድል የተሰማኝን ደስታ ስገልፅ በተለይም በአሁኑ ወቅት ሀገራችን ካለችበት ተጨባጭ ሁኔታ አንፃር ከመቼውም ጊዜ በላቀ ብሔራዊ ስሜታችን ሊጠናከር በሚገባበት በእዚህ ታሪካዊ እና ወሳኝ ሰዓት ይህን አኩሪ ድል ላስመዘገቡ ባለውለታ ውድ ጀግኖች አትሌቶቻችን እና እንዲሁም ይህ የተቀናጀ ውጤት እንዲመጣ ከፍተኛ አስተዎፆ ላደረጉ ጀግናዋ አትሌት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉን ጨምሮ ለአሰልጣኞች እና ለመላው የሉካን ቡድኑ አባላት በሙሉ ከፍ ያለ የአክብሮት ምስጋናዬን እያቀረብኩ ነው::

በእዚህ አጋጣሚ ለመላው ኢትዮጵያዊያን ወገኖቼ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክቴን ለማስተላለፍ እወዳለሁ::

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
ፍቅር ያሸንፋል
ቴዎድሮስ ካሳሁን
(ቴዲ አፍሮ)
4.5K views16:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-23 20:01:31 https://vm.tiktok.com/ZMNQ7b7gR/?k=1
375 views17:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 23:10:08 https://vm.tiktok.com/ZMNaD8ypj/?k=1
541 views20:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 13:00:21 በቅድሚያ ጀግናው ልጃችን ቴዲ አፍሮ፦ እንኳን ለኢትዮጵያ ልጇ፥ ለልጆቿም ወንድሞቿ ሆነህ ተወለድክልን። ብዙዎች በዚህ ዓለም ላይ "ከከባድ ነገሮች ውስጥ አንዱ ከባድ ነገር የሚወዱትን ሰው በሚመጥኑ ቃላቶች ለመግለጽ መሞከር ነው" ሲሉ አውቃለሁ። በዚህ ጉዳይ በተወሰነ መልኩ ብስማማም ልቤ ግን አንደበት ከሚገልጸው በላይ ተግባር የሚገልጸው ፍቅር ይልቃል ብሎ ስለሚያምን ይኼን ሰው ለመግለጽ ቸገረኝ ብሎ ከማውራቱ ይልቅ እሱን በእውነተኛ የመውደድ ስሜት መውደዴ ብቻ በቂ ሆኖ ይሰማኛል። እንደ ቴዲ አፍሮ በጀግንነት እና በእርሱ ጽናት ልክ ባይሆንም ጥቂት ነገሮቹን በመውረስ ለአንዲትም ሰከንድ ቢሆን ሀሳቡን ሳልቋወም ከ20 አመታቶች በላይ ከርሱ ጋ ተጉዣለሁ። ይኼ እና ያልገለጽኳቸው እውነታዎች በተግባር የተገለጸውን ፍቅሬን በመጠኑም ቢሆን ይልጻሉ ብዬ አምናለሁ።

ሰውን ለመውደድ ሰው ከመሆን የላቀ ምክኒያት ባያስፈልግም የሰዎች አፍ ግን ስለምን ወደድከው ሲል ዕልፍ ጊዜ ጠይቆኛል። በመጀመሪያ ሰው በመሆኑ እንደ ሁሉ ሰው እንደወደድኩህ በኩራት ተናገርኩ። በመቀጠልም የእርሱን ስብዕናዎች እንዲ እያልኩ መጥቀስ ጀመርኩ። ቴዲ አፍሮን በጣም የወደድኩት ከሌሎቹ በተለየ መልኩ በሙዚቃዎቹ ስለ ፍቅር በጽኑ መንፈስ ስለሚያቀነቅን ነው። እኔ ደግሞ የፍቅርን ኃያልነት የማምን ሰው ነኝ። ፍቅር በእግዚአብሔር ከመወደድ እና እግዚአብሔርን ከመውደድ ይጀምራል። እግዚአብሔርን የሚወድ ሁሉ ሌሎችን ይወዳል። ይኼ የፍቅር ሉዓላዊ /ነጻ/ ህግ ነው።

ታዲያ ስለፍቅር ሌልች አላዜሙም እንዴ ብሉኝ ነጥቤ እሱ አይደለምና ሃሳቤን እንዲህ ስል እቀጥላሉ። ፍቅር ማለት መውደድ ብቻ አይደለም። መፍራት እና ማክበርም ጭምር ነው። በመፍራት የሆነ ማክበር እና አምልኮ ለእግዚአብሔር፥ በማክበር የሆነ መፍራት ደግሞ ለሰው ልጆች እና ለፍጥረት ሁሉ ይገባል። ይኼን መንፈስ የተጎናጸፈ ሰው ደግሞ ታላቁንም ታናሹንም ያከብራል፣ ይወዳል ይፈራልም። መፍራት በሃይለ ቃል ላላመናገር ነው። መፍራት ከላይም ከታችም በማሃከልም ለቆመው ለመታዘዝ መፍቀድን እንደ ሆነ ልብ ይሏል። ከዚህ አንጻር በኪነጥበቡ ዘርፍ እንዲህ ሆኖ ያገኘሁት ይኼንን ሰው ነው። ይኼንን ሰው መውደድ፣ ማክበር፣ መታዘዝ እንዲሁም እንደ ታላቅ ወንድም ማየት ፍጹም ጤናማ ከሆነ ልብ እና አዕምሮ የሚመነጭ ነው። በእግዚአብሔርም ዘንድ መውደድ ለሰው ልጆች ሁሉ የቀረበ የክርስቶስ አዋጅ ነውና ይኼን ሰው በመውደዴ ደስተኛ ነኝ እላለሁ በኩራት።

በመጨረሻም ለኢትዮጵያ አገራችን እና ለወገኖቻችን ላበረከተው አስተዋጽኦ ከፍ ያለ ምስጋናዬን ለማቅረብ እወዳለሁ። የኪነጥበብ ሙያው እንዲከበርና እንዲታፈር ጭምር የእርሱ በዚህ ደረጃ መግዘፍ ዋናውን ሚና ተጫውቷል ለዚህም ትልቅ ክብርን እሰጠዋለሁ። ቴዲ አፍሮ በሚወዱት፣ በሚጠሉት፣ በሚተቹት /በሚቀኑበት/ ባለሙያዎች ልብ ውስጥ ሳይቀር ትልቅነቱ ሊገዝፍ የቻለው እግዚአብሔርን ይዞ በመቆሙ ስለሆነ እግዚአብሔር እስከ ፍጻሜው ድረስ አብሮት ይሆን ዘንድ መልካም ምኞቴ ነው።

ትንሽ ልከትብ ፈልጌ ብዕሬን አነሳሁት ግን ትልቅ ሰው ሆነብኝ እና በትንሽ አንቀጽ ልቋጨው ተሳነኝ። አሁንም ብዙ ጠልቄ መውጫው እንዳይጠፋኝ የልቤን ሀሳብ ገትቼ ምኞቴን ገልጬ ልተው። በእውነተኛ መውደድ የምወድህ የክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ መልካም ልደት ይሁንልህ። የሚወድህ ልቤ የጸነሰውን ሀሳብ በሚያከብርህ ብዕሬ እንዲህ ከተብኩት።

✎ #ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/
9.4K views10:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 19:46:36
በክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ የህይወት ጉዞ ላይ የሚያውጠነጥን "ቴዎድሮስ እስኪነግሥ" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ ከሀምሌ 20/2014 ዓ.ም ጀምሮ ለአንባቢያን ይቀርባል።

ከመጽሐፉ...

"...ቴዲ በሥነ-ግጥሙ ዘርፍ የነበረው ሀሳብን በተመጠነ ቃል የመግለጽና ለሰዎች በድምጹ የማቅረብ ልምዱ አድጎና ጎልብቶ እዚህ ደረጃ መድረሱ እጅግ አስገርሞኛል፡፡ ስለ ኢትዮጵያ ህዝቦች በጋራ የመኖር ውበት የሚገልጽባቸው መንገዶች ልዩ ናቸው፡፡ አርቲስቱ ከፖለቲካ ነጻ መሆኑና ቀደምት ሀገሪቷን በከፍታ ላስጓዟት መሪዎች የሚሰጠው ክብር ከድምጻውያን መካከል በግንባር ቀደምትነት የሚያሰልፈው ነው፡፡"

የቴዲ አፍሮ የቀድሞ አማርኛ መምህር ስለሺ ከበደ
350 views16:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 21:09:50 Tata Afro
598 views18:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 21:09:22 አድርሱልኝ ለክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/

መቼ ነው በሉልኝ...?

በቅድሚያ ግን ይኼንን ጽሁፍ እስካጠናከርኩበት ሰዓት ድረስ "ናዕት" /የህዝብ ድምጽ/ የሆነው ሙዚቃ ከተለቀቀ 18 ቀናቶችን አስቆጥሯል። በነዚህ ቀናቶች ውስጥ ሙዚቃውን በቀን ውስጥ ደጋግሜ ሳላዳምጥ ያለፍኩበት ቀን ስለመኖሩ እጠራጠራለሁ። መኪና ስነዳም ሆነ ስራ ቦታ ቁጭብዬ፥ ስተኛም ሆነ በቡና ሰዓት ላይ፥ ከተማው ውስጥ ስዘዋወርም ሆነ ከከተማ ውጪ ለጉዳይ በወጣሁበት አጋጣሚ ሁሉ ይኼንን ሙዚቃ ከመስማት አልቦዘንኩም።

ደጋግሜ ያለ መሰልቸት ማዳመጤ ሙዚቃውን ቴዲ አፍሮ ስለዘፈነው እኔም በማይናወጥ ጽኑ መውደድ ሰውዬውን ስለምወደው ብቻ አይደለም ይኼ ሊሆን የቻለው። ይልቁንም ለልቤ የዘመናት ጽኑ ቁስል፥ ግጥም አበጃጅቶ ዜማ ደርድሮ እውነተኛ ህመሜን ስላንጎራጎረው ጭምር ነው። ናዕት እየሰማሁት እንደ አዲስ ያመኛል። እያደመጥኩት እንደ አዲስ ተስፋን ያጭርብኛል። አብሬው እያዜምኩ የወገኔ ስቃይ ይነበበኛል። እየሰማሁት ወገኔ ከህመሙ ሲያርፍ በዐይነ ህሊናዬ ይቀረጽብኛል። ግን ለክቡርነታቸው ጥያቄ ለማቅረብ ልቤ ስለወደደ ከታላቅ አክብሮት ጋ እንደሚከተለው በአደባባይ የልቤን ጥያቄ እጠይቀዋለሁ።

መቼ ነው...?

የክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን ሆይ እንዴት ነው እኛን በበደል አለንጋ ሲገርፉን አንተ መድማት የቻልክበት...? በምን ጥበብ ነው የኛ አካል ላይ ያረፈ ቁስል አጥንትህ ድረስ ዘልቆ የተሰማህ...? ምን ያህል ብትቀርበን ነው የውስጣችንን ሀዘን እያመመክ ያዜምከው...? እስከመቼስ ነው ድሆች ስንረገጥ አብረኸን የምትረገጠው...? መቼ ነው ደክሞህ የምትተወን..? መቼ ነው የኛ የወገኖችህ የገላችን ላይ ቁስል አንተን ውስጥ ውስጥህን ማቁሰሉን የሚተወው...? መቼ ነው የኛ ደም አደባባይ ላይ በፈሰሰ ቁጥር አንተ ውስጥ ውስጡን ከመድማት የምታርፈው...? መቼ ነው ልብህ ከእኛ የማያባራ ሀሳብ እርቃ እረፍት የሚኖራት...? መቼ ነው እኛ እንደ ዲዳ የተቆጠርንባቸውን ዘመናቶች አንተ ጮኸ ማስተጋባት የምታቆመው...? መቼ ነው ጎዳና ከወደቅን ጋ ትብብር አቁመኽ በብልጭልጭ ድንኳን ውስጥ የምታድረው...? መቼ ነው ድሃ ወገንህን ትተኽ እርፍ የምትለው...? መቼ ነው በግፍ መገደላችንን ችላ የምትለው...? መቼ ነው አንዴም ቢሆን እንኳን ግፈኞችን በድፍረት ከመናገር የምትቆጠበው...? መቼ ነው ግን እንደ ሌሎቹ በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ሆነን እቶን እሳት በላያችን እየዘነበብን ፀሐይ ነው እያልክ የምትፎግረን...? ቆይ እኛ ምን አድርገንልህ ነው እንዲህ በጽኑ የወደድከን...? መቼ ነው ለሁሉ እኩል ማዘን ለሁሉ እኩል መቆርቆር የሚደክምህ...? መቼ ነው እንደ ሌሎቹ አገሬን እወዳለሁ እያልክ የራስህን ጥቅም ለማስከበር የምትሰለፈው...? እኔ ወዳጅህ ልፋ ቢለኝ እንጂ ያንተን መልስ ጠንቅቄ አውቀዋለሁ። በኩራቶ ሆነኽ እንዲህ ነው የምትለው...

"...በዚህ ለጸና እውነት
የፍቅር ሀገር ከጥንት
ዘብ ያድራል ሁሉም እስከ ሞት
ዶፍ ቢዘንብ እቶን እሳት...!
ዶፍ ቢዘንብ እሳት ሀገሬን ላልረሳት
ቃል አለኝ ኖሬ ሞቼም ልክሳት..."

ምክኒያቱም ባንተ ጨዋ ነፍስ እሳቤ እኛ ነን ላንተ አገር። እኛ ነን ላንተ ዜጎች። ድሃን መውደድ ልክ ሆኖ የታየኽ፤ ከወደቁ ጋ አብሮ ወድቆ መነሳት ስህተት ያልሆነው ባንተ ልብ ውስጥ ብቻ ነው። እግዚአብሔር በኳላቸው ብሩህ ዐይኖችህ አዳፋ ልብሳችን እና በችግር የገረጣው ሰውነታችንን በመጠየፍ ስሜት ሳይሆን በመጠሪያችን /ሰው በሚለው/ የክብር ገጻችን አንጥረኽ በማየት እና አክብረኽ በመጥራት የእግዚአብሔር ወገኖች መሆናችንን በማሳሰብ በናቁን እና በተጠየፉን ሰዎች ፊት ኩራት ሆነኸናል። መንግስት ስለፈሰሰው ደማችን በግፍ ስለተነጠቀች ነፍሳችን ግድ አልሰጥ ብሎት የሀዘን ቀን እንኳን ለማወጅ ቢጠየፈንም አንተ ግን በዜማ የዕልፍ ሰዎችን ስሜት አባብተኽ ልባችን በግፍ ስለወደቁ ወገኖቻችን በሀዘን ሆኖ እንዲያስባቸው አደረከው። ከምድር ሆኖ ወደ እግዚአብሔር የሚጮኸው የንጹሃን ደም አንዲት ቀን በጋራ ሀዘን ታስቦ ብቻ መረሳት ያለበት ሳይሆን የዓለም ህዝብ ተባብሮ ለዘመናት ሲያስባቸው ሊኖር ይገባል ስትል ውስጥን የሚሰብቅ ዜማ ደረደርክላቸው።

የክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን Teddy Afro ሁሌም ከጭቁኖች ጎን በኩራት የምትቆም ጽኑ ሰው ነህና ዛሬም ድረስ በማይናወጥ ጽኑ መውደድ እንወድኃለን!

ዝንፍ በማይል እውነተኛ መውደድ እ...ወ...ድ...ኃ...ለ...ሁ...!





✎ #ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/
595 views18:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-22 16:05:20
የኢትዮጵያ ሙዚቃ በዓለም ጆሮዎች...

ድምጻችን በዓለም እየተሰማ ነው። "ናዕት" አርባ ሺ Subscribers፣ ከ90 ሺህ በላይ መውደዶች እና ከአንደ ሚሊየን በላይ ተመልካቾችን በአስራ ሰባት /17/ሰዓታት ውስጥ ብቻ አግኝቷል። ይኽ የህዝብ ድምጽ የሆነው የክቡር ዶ/ር ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ አዲስ ሙዚቃ ዓለማችን ላይ በዚህን ሰዓት በስፋት እየተደመጡ ካሉ ሙዚቃዎች ውስጥ የሁለተኛ ደረጃነትን የያዘ ሲሆን በዘመናዊ የሙዚቃ ማድመጫ ድረገጽ /You Tube/ ላይ ከእራሱ ከቴዲ አፍሮ በቀር በኢትዮጵያ በዚህ ፍጥነት የተደመጠ ሙዚቃ በፍጹም የለም።

ናዕት /እያመመው ቁ፪/ ሙዚቃ ገና 24 ሰዓት ሳይሞላው በዚህ ፍጥነት በዓለም ደረጃ መዳረስ መቻሉ እጅግ ሊደነቅ የሚገባ ክስተት ነው። የህዝብ ድምጽ ሁሌም ኃያል ነው። ናዕት የኢትዮጵያውያን ድምጽ ነው። እንደ አገር ከገባንበት ማጥ ለመውጣት እንደ ዜጋ ከተረገጥንበት ትቢያ ለመነሳት እንዲህ ያሉ አስገምጋሚ ድምጾች ያሹናል። እንደ ሰማይ ማስገምገም እንደ ነጋሪት ጉሰማ የአምባ ገነኖችን ልብ የሚያሸብር የነፍስ ጩኸት።

✎ #ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/

አሁንም ከፍ ብሎ ይደመጥ

የሚያዜም ይመስላል ሲያጣጥር ተጨንቆ
ውስጡን ሲሰብቅለት ኡ... እያለ ማሲንቆ
ኡ...ኡ...



816 viewsedited  13:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 20:08:05 @
778 views17:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 20:07:50
የክቡር ዶ/ር ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ አንተ ጽኑ እና ጀግና አባት ነህ። ከአብራኮችህ ለወጡ ልጆችህ ብቻ ሳይሆን ለብዙዎች ምርጥ አባት ሆነህ በመቆምህ ከልብ እናመሰግንኃለን።

የአገሬ ማህጸን እንዳንተ አይነት ቅን ሰዎችን ስለምታፈራ ክብር ሊሰማት ይገባል።

መልካም የአባቶች ቀን ይሁንልህ!

በጽኑ መውደድ እ...ን...ወ...ድ...ኃ...ለ...ን!
12.7K views17:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ