Get Mystery Box with random crypto!

እግዚአብሔር እንዲህ አስተማረኝ... ዛሬ እረፍቴ ስለነበር በማለዳ ራሴን በዋና ለማነቃቃት ወደ አ | ጵራቅሊጦስ

እግዚአብሔር እንዲህ አስተማረኝ...
ዛሬ እረፍቴ ስለነበር በማለዳ ራሴን በዋና ለማነቃቃት ወደ አንድ ቦታ ሄድኩ።አንድ አባት ትንሽ ልጁን ውሐ ውስጥ ይዞ ዋና ሊያስለምደው ይሞክራል።ጥልቀት ወዳለበት ቦታ እየቀረቡ ሲሄዱ ልጁ በፍርሀት ውስጥ ሆኖ እያለቀሰ ካልወጣሁ ማለት ጀመረ።ያኔ አባቱ እንዲህ ሲለው ሰማሁ"አይዞህ አለቅህም"!

ልጁ የያዘውን እጅ ሳይሆን የውሀውን ስምጠት ባየ ጊዜ ፈራ።የእኛም ህይወት እንዲህ ነው።የእግዚአብሔር እጅን ሳይሆን ሁኔታዎቻችንን ስናይ እንጨነቃለን።እግዚአብሔር ግን በማንኛውም ከባድ በሚመስል ህይወት ውስጥ እንድናልፍ የሚፈቅደው በያዘን እጁ ስለሚተማመን ነው።ወዳጆቼ አትፍሩ አትጨነቁ።አንጠፋም ደግሞም አንወድቅም።ምክንያቱም እርሱ እንዲህ ብሎናል"አልለቅህም ከቶም አልተውህም"ዕብ 13:5

ጌታዬ ኢየሱስ ስለ እኔ የቆሰለው እጅህ ይዞኛልና አመሰግንሀለው።ይሄ እጅ እንደ ሰው ይዞ የማይለቅ መሆኑን አስተውል ዘንድ በየቀኑ አይኔን ክፈት።