Get Mystery Box with random crypto!

አንዴ ከሄዱ ብትለምኗቸው የማይመለሱ አራት ነገሮች! በሕይወታችሁ እንደገና ለመመለስ የሚያስቸግሯ | Our World

አንዴ ከሄዱ ብትለምኗቸው የማይመለሱ አራት ነገሮች!


በሕይወታችሁ እንደገና ለመመለስ የሚያስቸግሯችሁ አራት ነገሮች፡-

“እድል” - አንዴ ካመለጣችሁ በኋላ!

“ቃል” - አንዴ ከአንደበታችሁ ከወጣ በኋላ!

“ጊዜ” - አንዴ ሳትጠቀሙበት ካለፈ በኋላ!

“አመኔታ” አንዴ ከጎደለ በኋላ ለመመለስ አስቸጋሪ ነው፡፡

1. “እድል” - በአጋጣሚም ሆነ ጠንክራችሁ በመስራታችሁ የመጣን እድል መለየት፣ ማክበርና በተገቢው ሁኔታ መጠቀም፡፡

2. “ቃል” - ሁኔታዎች ሲገፋፏችሁም ሆነ እንዲሁ ስለለመደባችሁ በቀላሉ የምትናገሯቸውን ሰው ጎጂ ንግግሮች በሚገባ ማሰብና ራስን መግታት፡፡

3. “ጊዜ” - በሆነ ባልሆነ የምታባክኑትና አሁን ባላችሁ እድሜ ማድረግ የሚገባችሁን ነገር ባለማድረግ የምታባክኑትን ጊዜ በጥንቃቄ መያዝ

4. “አመኔታ” - ሰዎች ሲያምኗችሁና ራሳቸውንም ሆነ ነገሮቻቸው በእናንተ ላይ ሲጥሉ እምነት ከማጉደል መጠበቅ፡፡

፣ ያለፈው አልፏል፣ የባከነው ባክኗል፡፡ የተራረፈውን እንሰባስበውና ሕይወትን እንደገና በአዲስ መልክ እንጀምር፡፡

ከዶ/ር እዮብ ማሞ የተወሰደ

***