Get Mystery Box with random crypto!

የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሳሙኤል በ2015 ዓ.ም መጨረሻ ጀምሮ እን | Our World

የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሳሙኤል በ2015 ዓ.ም መጨረሻ ጀምሮ እንደሚተገበር በሚጠበቀው የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና ዙሪያ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ከሰጡት ማብራሪያ የተወሰደ

የዩኒቨርስቲ መዉጫ ፈተና ምንድነዉ?

ብቁ የሰው ሃይል በማዘጋጀት ወደ ኢኮኖሚ መግባቱን ማረጋገጫው አንደኛው መንገድ ነዉ::

ተመራቂዎች በተማሩበት ሙያ፤ ዘመኑ የሚጠይቀውን እውቀት፣ክህሎትና አመለካከት ገንብተው ስለመውጣታቸው የሚመዝን ነዉ፡፡

ዲግሪ በያዙ ተመራቂዎች መካከል በብቃት የሙያውን ምሉዕነት ተላብሶ የተመረቀው የትኛው እንደሆነ ይመዝናል

ምዘናዉ ለማን ይሰጣል?

ምዘናው የሚሰጠው በመጀመሪያ ዲግሪ ላይ ብቻ ነዉ

ትግበራው አገራዊ ፖሊሲ እንደመሆኑ በግል፣ በመንግስትም በየትኛውም ተቋም የሚማር ዲግሪውን የሚያገኘው ምዘናውን ካለፈ ነዉ፡፡

ምዘናዉ ለምን እና በማን ይሰጣል?

ተማሪዎች ሲገቡ እንጂ ለምን ወውጫ ላይ ይፈተናሉ የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ቢሆንም ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡት የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ተፈትነው መሆኑን መዘንጋት አይገባም

የከፍተኛ ትምህርት አዋጅ 1152/2011 የመውጫ ፈተና ሊሰጥ እንደሚችል በግልጽ አስቀምጧል፡፡ የሪፎም አካል ነው፣

የሪፎም አጀንዳን መንግስት የሚመራው እንደመሆኑ ሂደቱን ትምህርት ሚኒስቴር መንግስትን ወክሎ የሚሰራዉ ነዉ፡፡

ምዘናዉን ለማካሄድ ምን እየተሰራ ነዉ ?

ትምህርቶቹን የሚያዘጋጁ ተቋማትና መምህራን የዝግጅት ስራዎች እስከ ግንቦት 2015 ዓ.ም ይሰራሉ