Get Mystery Box with random crypto!

ከቁጥጥር ውጭ የሆነችው የቻይና ‘Long March-5B’ ሮኬት አካል በከፍተኛ ፍጥነት ወደ ምድር | Our World

ከቁጥጥር ውጭ የሆነችው የቻይና ‘Long March-5B’ ሮኬት አካል በከፍተኛ ፍጥነት ወደ ምድር እየተምዘገዘገች መሆኑ በረካቶች ዘንድ ስጋትን ፈጥሯል።

የሮኬቱ ስባሪ በመጪዎቹ ሶስት ቀናት ውስጥ ምድር ላይ ሊወድቅ ይችላል የተባለ ሲሆን፤ በተለይም ሰኞ እለት ምድር ለይ ሊደርስ እንደሚችል ተነግሯል።

አሁን ላይ ባለው ሁኔታ ሮኬቱ በየትኛው ስፍራ ላይ ሊወድቅ እንደሚችል መገመት አዳጋች ቢሆንም፤ ሰዎች በብዛት የሚኖሩበት ስፍራ ላይ ሊወድቅ ይችላል የሚል ስጋትም ቀስቅሷል።
መቀመጫውን አሜሪካ ካሊፎርኒያ ያደረገው ለትርፍ ያልተቋቋመው ኤሮስፔስ ኮርፖሬሽን እንዳስታወቀው፤ ወደ ምድር እየተምዘገዘገ ያለው የሮኬቱ ስባሪ 25 ቶን አሊያም 25 ሺህ ኪሎ ግራም እንደመሚዝን አስታውቋል።
ሮኬቱ መቼ ምድር ላይ ይወድቃል የሚለውን ሙሉ በሙሉ መገመት ባይቻልም ሰኞ ማለዳ ላይ ሊሆን እንደሚችል ግን ተቋሙ ግምቱን አስቀምጧል።
ስብርባሪው የሚወድቅበትን ስፍራ ለማወቅ ገና ነው ያለው ከቋሙ፤ አሜሪካ፣ አፍሪካ፣ ብራዚል፣ ህንድ ወይም ደቡብ እሲያ ላይ ሊወድቅ ይችላል ብሏል።
ቻይና ሎንግ ማርች 5 የተባለ ሮኬቷን ባሳለፍነው እሁድ ወደ ጠፈር ማምጠቋን ማስታወቋ ይታወሳል።

የቻይና መንግስት ባሳለፍነው ረቡዕ እንዳስታወቀው፤ የሮኬቱ ስብርባሪ በምድር ላይ ለሚገኝ ማንኛውም አካል መጠነኛ ስጋት ሊፈጥር እንደሚችል በመግለፅ፤ ነገር ግን ስባሪው ውሃ ላይ የመውደቅ እድሉ ሰፊ መሆኑን አስታውቋል።
ሆኖም ግን የሮኬቱ ስብርባሪ አካል ሰው በብዛት ወደሚኖርበት አካባቢ ላይ የመውደቅ እድል እንዳለው ተነግሯል።

በፈረንጆቹ 2020 ላይ ከቁጥጥር ውጪ የሆነ የሮኬት አከል በአይቮሪኮስት ወድቆ በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱ ይታወሰል።

#አልዓይን