Get Mystery Box with random crypto!

ጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የ5.5 ቢሊዮን ብር የብድር ስ | Our World

ጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የ5.5 ቢሊዮን ብር የብድር ስምምነት ተፈረመ።

በዛሬው ዕለት አዋሽ ባንክ መካከለኛ፣ አነስተኛና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች የፋይናንስ አቅርቦት እንዲያገኙ ከዘጠኝ አነስተኛ ፋይናንስ ተቋማት ጋር የ5.5 ቢሊዮን ብር የብድር አቅርቦት ስምምነት አድርጓል።

ከባንኩ ጋር ይህን ስምምነት ያከናወኑት ዘጠኙ አነስተኛ ፋይናንስ ተቋማት ቪዥን ፈንድ፣ ንስር፣ ቀንዲል፣ መተማመን፣ መክሊት፣ ዳይናሚክ፣ ዋሳሳ፣ ሃርቡ እና ፒስ አነስተኛ ፋይናንስ ተቋም ናቸው።

ማይክሮ ፋይናንስ እና ባንኩን በማስተሳሰር ትልቅ ሚና የተጫወቱት ማስተርካርድ ፋውንዴሽን እና ፈርስት ኮንሰልት ብሪጅ ፕሮገራም መሆናቸው በዕለቱ ተጠቅሷል።

ፈርስት ኮንሰልት ባቀረበው ማብራሪያ መሰረትም የ5.5 ቢሊዮን ብር ብድሩ 110ሺህ ኢንተርፕራይዞችን ተደራሽ የሚያደርግ ሲሆን በዚህም እስከ 330 ሺህ ወጣቶች እና ቤተሰቦቻቸው ተጠቃሚ የሆናሉ፡፡

የአዋሽ ባንክ ሥራ አስኪያ አቶ ፀሐይ ሽፈራው ባንኩ ከ2016ዓ.ም ጀምሮ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የተለያዩ የብድር አቅርቦቶችን ማድረጉን በማስታወስ በቅርቡ ይፋ ባደረገው “ታታሪዎቹ” የተሰኘ የወጣት ሥራ ፈጣሪዎችን የሚያበረታታ ውድድር 8ሺህ አመልካቾችን ተቀብሎ እያወዳደረ መሆኑንም አንስተዋል።