Get Mystery Box with random crypto!

' የዝንጀሮ ፈንጣጣ / መንኪፖክስ / ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ደረጃ ይደርሳል ብለን አንጠብቅም ' - | Our World

" የዝንጀሮ ፈንጣጣ / መንኪፖክስ / ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ደረጃ ይደርሳል ብለን አንጠብቅም " - የዓለም የጤና ድርጅት

እስካሁን በመቶዎች የተቆጠሩ ሰዎች መያዙ የታወቀው መንኪፖክስ ወይም የዝንጀሮ ፈንጣጣ ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ደረጃ ይደርሳል ብለው እንደማይጠብቁ የዓለም የጤና ድርጅት ከፍተኛዋ የበሽታው ኤክስፐርት ተናገሩ።

ያን ይበሉ እንጂ በሽታው እንዴት እንደሚስፋፋ ሆነ ከአያሌ አሰርት በፊት የፈንጣጣ መከላከያ ክትባት ዘመቻ መቋረጡ ያስከተለው አንድምታ ይኖር እንደሆን ጨምሮ ብዙ የማይታወቁ ነገሮች መኖራቸውን አልደበቁም።

ዶክተር ሮዛሙንድ ሉዊስ በሰጡት ማብራሪያ ድርጅታቸው መንኪፖክስ በግብረ ስጋ ግንኙነት ወይም በአየር በትንፋሽ ይተላለፍ እንደሆን በተጨማሪም የህመም ምልክት የሌላቸው ሰዎች በሽታውን ያስተላልፋሉ ወይ የሚሉትን ጨምሮ በርካታ ጥያቄዎችን ይዞ እየመረመረ መሆኑን አመልክተዋል።

ካሁን ቀደም በሽታው በተቀሰቀሰባቸው ጊዜያት በቀላሉ የሚዛመት እንዳልሆነ ታይቷል ያሉት የዓለም የጤና ድርጅቱ ባለሙያ አሁንም ሥርጭቱን ለመቆጣጠር ጊዜ እንዳለ መግለፃቸውን ቪኦኤ /VOA ዘግቧል።

#VOA