Get Mystery Box with random crypto!

ዲግሪ በ20ሺ ብር ! በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ዲግሪ በ20 ሺሕ ብር እየተሸጠ መሆኑ ተነገረ።በወልቂጤ | አገልግል

ዲግሪ በ20ሺ ብር !
በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ዲግሪ በ20 ሺሕ ብር እየተሸጠ መሆኑ ተነገረ።በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አንድ ዲግሪ በ20 ሺሕ ብር እየተሸጠ መሆኑን አዲስ ማለዳ ዘግቧል!!

በዩኒቨርሲቲው ያሉ ሠራተኞች፤ ሰዎች በሚገዙት ዲግሪ ዙሪያ ሳይማሩ መደበኛ ተማሪ እንደሆኑ አስመስለው በ20 ሺሕ ብር ሐሰተኛ ዲግሪ እየሸጡ መሆኑን ማወቅ ተችሏል። ከኹለት ወር በፊት የዩኒቨርሲቲውን ዲግሪ የገዙ ሰዎች መረጃውን ሲለዋወጡ እንዲሁ ተሰምቶ የነበረ ሲሆን፤ ከዚያን ወቅት ጀምሮ በማጣራት ሂደት ላይ መቆየቷን አዲስ ማለዳ ገልጿል። በመሆኑም፣ ዲግሪ ከገዙ ሰዎች በተደረገ ማጣራት የዩኒቨርሲቲው ሠራተኞች በምስጢራዊ አካሄድ ዲግሪ እየሸጡ መሆኑ ተደርሶበታል።

መረጃው የተገኘው በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በአካል ተገኝተው ሳይማሩ ግን በመደበኛ የትምህርት መርሀ ግብር እንደተማሩ ተደርገው ዲግሪ ከገዙት ሰዎች አንደበት ነው። መረጃ አቀባዮቹ ዲግሪውን ለመግዛት ያለውን ሂደት ሲጠየቁ ‹‹ምንም ፕሮሰስ (process) የለውም። ሙሉ ሥም፤ ፎቶ እና ብሩን መላክ ብቻ ነው።›› ሲሉ መስክረዋል።የከፍተኛ ትምህርት ተቋሙ ሠራተኞች አንድ ዲግሪ ለመሸጥ የሚጠይቁትም 20 ሺሕ ብር መሆኑ ተነግሯል። መረጃ አቀባዮቹ ሐሰተኛ ዲግሪ ገዝተው በተለያዩ ተቋማት ሥራ የያዙም ጭምር ናቸው።

በመሆኑም፤ አዲሱ የትምህርት ፎኖተ ካርታ ከመጽደቁ በፊት ለሦስት ዓመት፤ ከጸደቀ በኋላ ደግሞ ለአራት ዓመት መማርና ጥልቅ ጥናትን የሚጠይቀውን የማኔጅመንት ዲግሪ በቀናት ውስጥ እየተሸጠ መሆኑን የዐይን እማኞች ገልጸዋል።