Get Mystery Box with random crypto!

ይህን ልጅ እንደግፈው ለሌሎችም መረጃውን '#ሼር_ፖስት ይሁን።  የ21 ሚሊዮን ብር ሽልማት የሚያስ | አገልግል

ይህን ልጅ እንደግፈው ለሌሎችም መረጃውን "#ሼር_ፖስት ይሁን።  የ21 ሚሊዮን ብር ሽልማት የሚያስገኘው እና 2400 ተወዳዳሪዎችን ካሳተፈው ዓለም አቀፍ የሳይንስ ውድድር ተሳትፎ ለግማሽ ፍጻሜ ያለፈው አቤል አሰፋ  በሚያሳዝን ሁኔታ በ4 ሺህ ላይክ በክሮሺያዊት ተወዳዳሪ እየተመራ ይገኛል።  የሱ ገና 10 ሺህ ላይ ነው።

ውድድሩ ውስብስብና ጥልቅ የሆኑ የሳይንስ፣ የሒሳብ እና የፊዚክስ ጽንሰ ሐሳቦችን ምንም የሳይንስ እውቀት የሌላቸው ሰዎች በቀላሉ ሊረዱት በሚችሉት መልኩ በ90 ሰከንድ ቪዲዮ ማቅረብ ነው። 
ቪዲዮው በፌስቡክ እና በዩቲዩብ ከፍተኛ የሕዝብ ድምጽ (ብዙ ላይክ) ያገኘለት ተወዳዳሪም ወደ ምርጥ 15 ተፎካካሪነት ይገባል። ለዚህ ዙር የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ እስከ ሰኞ መስከረም 09/2014 ዓ.ም. ድረስ የሚቀጥል ሲሆን በቀጣዩ ቀንም ወደ ምርጥ 15ቱ ውስጥ የተካተቱ ሥራዎች ይፋ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል።
እነዚህ ሒደቶችን አልፎ በመጨረሻ አሸናፊ የሚሆነው ተወዳዳሪ፣ የ250 ሺህ ዶላር ተሸላሚ ይሆናል።
የእርስዎ ሁለት ድምጽ ደግሞ ለመጨረሻው ዙር ከሚገቡ 16 ተወዳዳሪዎች መካከል በህዝብ ድምጽ የሚያልፍ አንድ ብቸኛ ተወዳዳሪ ሊያደርገው ይችላል፡፡ የሚከተሉትን ሁለት ቪድዮዎች  ‘Like’ አድርገው ድምጽዎን በመስጠት ይህን ኢትዮጽያዊ ወጣት ለፍጻሜ ውድድር እንዲደርስ ይተባበሩት:: አንደኛውን ቪዲዮ የምታገኙት በዚህ የፌስቡክ ሊንክ ነው፣ ሊንኩን ተከትላችሁ ቪዲዮው ሲመጣ ላይክ ማድረግ ነው።  https://www.facebook.com/watch/?v=595860615362156

ሁለተኛው ቪዲዮ የሚገኘው በድርጅቱ የዩቲዩብ ቻናልነው፣ ሊንኩን ተከትላችሁ ቪዲዮውን ላይክ ማድረግ ነው





ለጓደኞቻችሁም አጋሩለት!