Get Mystery Box with random crypto!

Osman Ethiopia

የቴሌግራም ቻናል አርማ osmanethio — Osman Ethiopia O
የቴሌግራም ቻናል አርማ osmanethio — Osman Ethiopia
የሰርጥ አድራሻ: @osmanethio
ምድቦች: ቪዲዮዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 25
የሰርጥ መግለጫ

Osman ethiopia

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-07 22:04:25 ማስታዎሻ
=========
ነገ ዕለተ ጁሙዓህ ዙል ሒጃህ 9, 1443 ዓመተ ሂጅራ ነው። ይህ የዙል ሒጃህ ዘጠነኛ ቀን የዐረፋህ ቀን ነው።

①) ይህ ቀን ከአመቱ ቀናት ሁሉ በላጩ ቀን ለመሆኑ በዕውቀት ባለቤቶች ዘንድ ቅንጣትም ውዝግብ የለም።
°
②) በዚህ ቀን የሚሠሩ መልካም ሥራዎች ከሌላው በላጭ ናቸው።
°
③) በዕለቱ ከሚሠሩ መልካም ሥራዎች መካከል አንዱና ዋናው ደግሞ ዱዓእ ነው።
°
④) እርሳቸው ይሁኑ ከርሳቸው በፊት ያሉ ነቢያት በዚህ ቀን ካደረጓቸው ዱዓዎች ሁሉ በላጩ «ላ ኢላሃ ኢለ-ል'ሏህ ወሕደሁ ላሸሪከ ለሁ ለሁ-ል-ሙልኩ ወለሁ-ል-ሐምዱ ወሁወ ዓላ ኩሊ ሸይኢን ቀድር» የሚለው መሆኑን ተናግረዋል – ረሱሉ-ል-ሁዳ ﷺ!
ያልሐፈዛችሁ ሐፍዙት!
°
⑤) ይህን ቀን ሐጅ ላይ ካሉ ሰዎች ውጭ ሌላው በጾም ማሳለፉ የሁለት አመታትን (ከኋላውና ከፊቱ ያሉ አመታትን) ወንጀል ያስምራል ብለዋል ውዱ ነቢይ ﷺ።
°
⑥) በዚህ ቀን በተለይም ከዐስር እስከ መጝሪብ ባለችው ወቅት የሚደረግ ዱዓእ እጅግ በጣም ተቀባይነት አለው።
°
⑦) በተጨማሪም ይህ ቀን የዋለው ነገ ጁሙዓህ እንደመሆኑ መጠን፤ በሌላ ሐዲሥ እንደተዘገበው በዕለተ ጁሙዓህ ከዐስር እስከ መጝሪብ ባለው ወቅት የሚደረግ ዱዓእ ተቀባይነት አለው። Imagine ሁለቱ ተቀባይነት ያለባቸው ወቅቶች አንድ ላይ ሲገጣጠሙ → ተቀባይነት² በሉት።
°
⑧) አላህ ይወፍቀንና፤ ሰሑር ላይ ቢነጋብን እንኳ ጹመን ለመዋል ለአንድት ቀን ብንነይት፣ ይህቺን ከዐስር እስከ መጝሪብ ያለች ወቅትም በኸይር ነገር ብናሳልፋት መልካም ነው። መቼም ሁላችንም ይብዛ/ይነስ እንጂ ከወንጀል የጠራን አይደለንምና እንዲህ አይነት ጌታችን እኛን ለመማር ብሎ ያመቻቸልንን የወንጀል ማበሻ ሰበቦችን በአግባቡ እንጠቀምባቸው።
°
⑨) ተክቢራ ማለት የሚጀመረው ከነገ ጠዋት የፈጅር ሶላት ጀምሮ እስከ ዙል ሒጃህ 13ኛ ቀን ዐስር ድረስ ነው።

አላህ እኔንም እናንተንም ለሚወደው ንግግርና ተግባር ይወፍቀን። ወደ መልካም ያመላከተ የሠሪውን ያክል ምንዳ ያገኛልና ቤተሰቦቻችሁን፣ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ለማስታወስ ሞክሩ።
298 viewsAmer, 19:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 19:37:44
አሏሁ አክበር፣ አሏሁ አክበር፣ አሏሁ አክበር
ላ ኢላሀ ኢለሏህ፣ አሏሁ አክበር፣ አሏሁ አክበር
ወሊላሂል ሀምድ!

ተክቢራ አብዙ!ዱአ እናድርግ ለሀገራችንም
383 viewsAmer, 16:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 19:37:44
لبيك الله وإن لم أكن بين الحجاج ملبياً
368 viewsAmer, 16:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 10:06:10
በቃ! ሙስሊሙ ወገኔ በየጊዜው እንዲህ ሆኖ ቀስ በቀስ እንዲያልቅ ተፈረደበት?


ላ ሐውለ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላህ!
ኢንና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!
388 viewsAmer, 07:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 19:44:46
አሕመዲን ጀበል እንደጻፈው
=====================
«ሽፋኑ «አማራ» በሚል ይሁን «ሙስሊሞች» ላለፉት ዓመታት በጅምላ
ሲጨፈጨፊ እንደነበረው ሁሉ የወሎ ሙስሊሞች በዚሁ በሰኔ ወር እንኳ
ለሁለተኛ ጊዜ ዛሬ ደግሞ በተመሳሳይ መንገድ በቄለም ወለጋ በኦነግ ሸኔ
በጅምላ እንደተገደሉ ሰማን።እጅግ የሚያሳዝንና የሚወገዝ እኩይ ተግባር!
ሰላማዊ ዜጎችን በማንነታቸው ኢላማ አድርጎ ግድያ ሲፈጸም ጉዳዩ ግድያ ብቻ
አይሆንም። ኢሰብኣዊነትና በሰው ህይወት ቁማር መጫወት ነው! ጀግና ነኝ ያለ
ኃይሉን መሳሪያ ባልታጠቁ ንጹኻን ላይ ሳይሆን ከታጠቀ ወታደር ጋር ይግጠምና
ያሳይ!
ላለፉት ዓመታት በተደጋጋሚ ንጹኋን ሲጨፈጨፉ በተመሳሳይ መንገድ
ጮህን፣አወገዝን።«እርምጃ እየተወሰደ ነው» ተባለ።ከፖለቲካ ሸፍጥ በራቀ ሁኔታ
መፍትሄው ላይ በማተኮር የእውነት ከልብ መነጋገር ባለመቻሉ ንጹኻንን መታደግ
አልተቻለም!
በተመሳሳይ መንገድ የንጹኻን ጭፍጨፋ ለስንተኛ ጊዜ መሆኑ ነው? አሁንም
እንደከዚህ ቀደሙ በዚያው መንገድ ቀጣዩ ግድያ እስኪፈጸምና ይህኛውን
እስኪያስረሳ ድረስ የዛሬውን ግድያ በማውገዝና በመጮህ ብቻ መፍትሄ ይመጣ
ይሆን? ባለፉት ዓመታት ከተጓዝንበት በተለየ መንገድና ዓይን ጉዳዩን ለመረዳት
ሞክረን የተለየ መፍትሄ ካልፈለግን በሀገራችን የንጹኻን ዜጎች እንዳይቀጥል
ያሰጋል! ሁሉን የምታውቀው አምላኬ ሆይ! ሰላምና ምህረትህን! '»
443 viewsAmer, 16:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 21:42:16 የማያባራ እልቂት። የማይገደብ የደም ጅረት። ሰሚ ያጣ ዋይታ። ለመሆኑ ደካሞችን፣ ጨቅላዎችን በጅምላ በመፍጀት የሚገኘው ትርፍ ምን ይሆን? ግን እስከ መቼ? ጌታዬ ሆይ! ከሰው ያለን ተስፋ ተሟጧል። ሽሽታችን፣ ለቅሷችን፣ ጩኸታችን ወዳንተ ብቻ ነው። አንተው መላ በለን። አንተው ወገኖቻችንን ፈርጅልን። ለርካሽ አላፊ ትርፍ ሲሉ የደካሞችን ነፍስ በማጥፋት ላይ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ድርሻ ያላቸውን ሁሉ የሚገባቸውን ስጣቸው።
472 viewsAmer, 18:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 17:30:35 ወለጋ ላይ ዛሬም ገደሏቸው።

ኢ-ን'ና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን

እንግዲህ ምን ይባላል
490 viewsAmer, 14:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 14:02:33
የአዲስ አበባ መጅሊስን ለመቆጣጠር ተደራጅቶ የመጣው የአህባሽ ቡድን የፈጸመው ውድመት ይህንን ይመስላል። ውድመቱን የፈጸሙት አብዛኛዎቹ በህግ ቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን የህንፃውን ክፍሎች በዚህ መልኩ አውድመዋቸዋል።
..
ሀሩን ሚዲያ
__________
755 viewsAmer, 11:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 14:01:40
ከነውጠኛው አካል ጋር ተናበው የሚሰሩት ጽንፈኛ ስብስቦች
..
በአዲስ አበባ ከተማ የእለት ጉርሳቸውን በመጅሊሱ ክፍያ ላይ ያደረጉ ጥቂት የአህባሽ ወጣቶች ነውጥ ለመፍጠር በከፍተኛ ደረጃ ጥረት ማድረጋቸው ይታወቃል። የእነዚህ አካላት ጥብቅ ትስስር ደግሞ ከነማን ጋር እንደሆነ የአደባባይ ሚስጥር ነው። በግልጽ በሚዲያዎቻቸው በመቅረብ ኢንተርቪው ከማድረግ ጀምሮ ግጭት ሊፈጥሩ የሚችሉ ተልዕኮዎችን በመቀበል ወደ ሙስሊሙ ማኅበረሰብ አስርጎ እስከ ማስገባት ድረስ የተለያዩ አደረጃጀቶችን ተጠቅመውና የመጅሊሱን ካዝና የፋይናንስ ምንጭ አድርገው ሲሰሩ ቆይተዋል።
..
ለስሙ የአዲስ አበባ ወጣቶች የሚል ማኅበር መስርተናል ቢሉም ማኅበሩ ህጋዊ ፍቃድ የሌለው ከመሆኑ በተጨማሪ ዋና ተልዕኮውም በሙስሊሙ መካከል ልዩነትና ጠብን በመፍጠር ከግጭቱ የማትረፍ አላማን ያነገበ ነው። ይህ ቡድን ሰዎችን ከመደብደብ አጋጣሚውን ካገኘም ከመግደል ወደኃላ የማይል አደገኛ ስብስብ ነው። ከዚህ በታች ባለው ቪዲዮ ከማን ጋር አጀንዳ እንደሚጋሩና እነማን የተግባራቸው ተባባሪዎች እንደሆኑ መረዳት ይቻላል።
..
ሀሩን ሚዲያ
___________
603 viewsAmer, 11:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 14:01:18
የአንድነቱ ጋሬጣ ማን ነበር? ከሙፍቲ ጀርባ በመሆን አደገኛ ቅስቀሳዎችን የሚያደርገው የአህባሽ ቡድን አላማውስ ምንድን ነው?
..
በዚህ ቪዲዮ ኡመር ይማም (በተለምዶ ኡመር ኮንቦልቻ) የተሰኘው ግለሰብ መንግስት ሙስሊሙ አንድ እንዲሆን በማሰብ ሙፍቲን ጨምሮ የተዋቀረውን ቡድን ይተቻል። በፍጹም አንድነት የሚባል ነገር የለም ሲልም ይገልጻል። መንግስት "አንድ ሁኑ" ማለቱ የማይመለከተው ጉዳይ ነው ሲልም ይወርፋል። ህዝበ ሙስሊሙ አንድ ከሆነ ጥቅማቸውን የሚያሳጣበቸው እሱና መሠል የቀድሞ የመጅሊስ አስገራፊና አስገዳዮች ዛሬም ችላ መባላቸውን እንደ ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም ግጭትን እየጠመቁ ይገኛል። ሀሩን ሚዲያም ይህንን ነውጠኛ ቡድን አስመልክቶ በተከታታይ መረጃዎችን ወደናንተ የሚያደርስ ይሆናል።
..
ሀሩን ሚዲያ
434 viewsAmer, 11:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ