Get Mystery Box with random crypto!

ማስታዎሻ ========= ነገ ዕለተ ጁሙዓህ ዙል ሒጃህ 9, 1443 ዓመተ ሂጅራ ነው። ይህ የ | Osman Ethiopia

ማስታዎሻ
=========
ነገ ዕለተ ጁሙዓህ ዙል ሒጃህ 9, 1443 ዓመተ ሂጅራ ነው። ይህ የዙል ሒጃህ ዘጠነኛ ቀን የዐረፋህ ቀን ነው።

①) ይህ ቀን ከአመቱ ቀናት ሁሉ በላጩ ቀን ለመሆኑ በዕውቀት ባለቤቶች ዘንድ ቅንጣትም ውዝግብ የለም።
°
②) በዚህ ቀን የሚሠሩ መልካም ሥራዎች ከሌላው በላጭ ናቸው።
°
③) በዕለቱ ከሚሠሩ መልካም ሥራዎች መካከል አንዱና ዋናው ደግሞ ዱዓእ ነው።
°
④) እርሳቸው ይሁኑ ከርሳቸው በፊት ያሉ ነቢያት በዚህ ቀን ካደረጓቸው ዱዓዎች ሁሉ በላጩ «ላ ኢላሃ ኢለ-ል'ሏህ ወሕደሁ ላሸሪከ ለሁ ለሁ-ል-ሙልኩ ወለሁ-ል-ሐምዱ ወሁወ ዓላ ኩሊ ሸይኢን ቀድር» የሚለው መሆኑን ተናግረዋል – ረሱሉ-ል-ሁዳ ﷺ!
ያልሐፈዛችሁ ሐፍዙት!
°
⑤) ይህን ቀን ሐጅ ላይ ካሉ ሰዎች ውጭ ሌላው በጾም ማሳለፉ የሁለት አመታትን (ከኋላውና ከፊቱ ያሉ አመታትን) ወንጀል ያስምራል ብለዋል ውዱ ነቢይ ﷺ።
°
⑥) በዚህ ቀን በተለይም ከዐስር እስከ መጝሪብ ባለችው ወቅት የሚደረግ ዱዓእ እጅግ በጣም ተቀባይነት አለው።
°
⑦) በተጨማሪም ይህ ቀን የዋለው ነገ ጁሙዓህ እንደመሆኑ መጠን፤ በሌላ ሐዲሥ እንደተዘገበው በዕለተ ጁሙዓህ ከዐስር እስከ መጝሪብ ባለው ወቅት የሚደረግ ዱዓእ ተቀባይነት አለው። Imagine ሁለቱ ተቀባይነት ያለባቸው ወቅቶች አንድ ላይ ሲገጣጠሙ → ተቀባይነት² በሉት።
°
⑧) አላህ ይወፍቀንና፤ ሰሑር ላይ ቢነጋብን እንኳ ጹመን ለመዋል ለአንድት ቀን ብንነይት፣ ይህቺን ከዐስር እስከ መጝሪብ ያለች ወቅትም በኸይር ነገር ብናሳልፋት መልካም ነው። መቼም ሁላችንም ይብዛ/ይነስ እንጂ ከወንጀል የጠራን አይደለንምና እንዲህ አይነት ጌታችን እኛን ለመማር ብሎ ያመቻቸልንን የወንጀል ማበሻ ሰበቦችን በአግባቡ እንጠቀምባቸው።
°
⑨) ተክቢራ ማለት የሚጀመረው ከነገ ጠዋት የፈጅር ሶላት ጀምሮ እስከ ዙል ሒጃህ 13ኛ ቀን ዐስር ድረስ ነው።

አላህ እኔንም እናንተንም ለሚወደው ንግግርና ተግባር ይወፍቀን። ወደ መልካም ያመላከተ የሠሪውን ያክል ምንዳ ያገኛልና ቤተሰቦቻችሁን፣ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ለማስታወስ ሞክሩ።