Get Mystery Box with random crypto!

ይህ ነው የትግራይ ሙስሊም ~ copy | Osman Ethiopia

ይህ ነው የትግራይ ሙስሊም
~
<<የትግራይ ሙስሊሞችን ልዩ ደግነት አስታወስከኝ፣ ዩኒቨርሲቲ እያለኝ በምግብ መበከል ምክንያት አምፀን ወጣን፣ ሙስሊም ተማሪዎችን መቐለ አንዋር መስጅድ ድንኳን ጥለው ከሁሉም መስጂዶች ገንዘብ ተሰብስቦ፣ በየቀኑ ብዙ በጎች ታርደው፣ ሁልጊዜ ድግስ ነበር። ፀብ የሚፈጠረው ማታ ላይ ነው፣ ምክንያቱም ሁሉም እቤቱ ወስዶ ማሳደር የሚፈልገውን ያህን የሙስሊም ተማሪዎች ቁጥር አይሞላም ነበር፣ ስለዚህ እኔ እንደት 2 ብቻ፣ 3 ብቻ እያሉ ለኸይር ስራ ይጣሉ ነበር። ሌላው ነገር ደግሞ በመስጂዱ ድግስ ሆዳችን ተወጥሮ እያለ፣ ማታ ለማሳደር በሽሚያ ከተከፋፈሉን በኋላ በየቤቱ ሌላ ድግስ ይጠብቀን እና በግድ ብሉ እኛ በቃን ሌላው ጉዳይ ነው፣ አምፀን ወጥተን ወፍረን ተመለስን።
ይህን ልዩ ህዝብ እንደት ትረሳዋለህ፣ እንደት ልትጠላ ትችላለህ፣ ፖለቲካ ያስጠላል። ስንቱን አሳጣን፣ ስንቱ በህሊናዬ መጡ በአላህ።
አላህ ከዚህ ሁሉ ችግር አውጥቷቸው፣ አንድ ያድርገን።>>

copy