Get Mystery Box with random crypto!

'ጥቁር_ኮት_አልብሱኝ' | Osman Ethiopia

"ጥቁር_ኮት_አልብሱኝ" ===============
(በእለተ አረፋ የተፈፀመ አሳዛኝ ታሪክ)

ወደ ሞት አደባባይ እየተነዱ ነው። ሊገደሉ። ከኃላቸው ሆኖ ወደ ሞት አደባባይ ለሚነዳቸው ሰው እንዲህ አሉት "ጥቁር ኮት አልብሱኝ"። አመጡላቸውና እየለበሱ ለምን ጥቁር ኮት መልበስ ፈለጉ? ተብለው ስጠየቁ "እንደምታዩት አከባቢው እጅግ ብርዳማ ነው። ይሄ በኔ ሞት ሊደሰት የተሰበሰበ ህዝብ ብርዱ ስያንቀጠቅጠኝ አይቶ ሞት ፈርቶ ነው የሚንቀጠቀጠው እንዳይለኝ ሰውነቴን ማሞቅ ስለፈኩ ነው" ብለው መለሱላቸው።

April 28, 1937 ተወለዱ። በ1979 የሀገሪቱ 5ኛው ፕሬዝዳንት ሆነው በመመረጥ ለ24 ዓመታት ሀገራቸውን በፕሬዝዳንትነት አገልግለዋል።

በ24 ዓመታት የስልጣን ቆይታቸው ወቅት ሀገራቸው በጦር ሃይል እና በኢኮኖሚ ምዕራባዊያን ሀገራትን የምትገዳደር ሀገር ወደ መሆን አሸጋገሯት።

እሳቸው የገነቧት አገር ምዕራባዊያንን ከመገዳደር ባሻገር ምዕራባዊያን በመካከለኛው ምስራቅ ለሚከተሉት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ እና ብሔራዊ ጥቅማቸው ጋሬጣ ልትንባቸው እንደምችል እርግጠኛ ሆነዋል።

ስለሆነም እሳቸው መወገድ ነበረባቸው። የሚያስወግዱበትን ሰበብ ፈለጉ። ቀላል ነበር ይህ ሰው "#ኒውክሌር_ቦንብ_ታጥቋል" በሚል ተራ ክስ እ.አ. አ 2003 ከስልጣን እስወገዷቸው።

በኢኮኖሚ የምዕራባዊያን ተገዳዳሪ የነበረች ሀገር በምዕራባዊያን ወረራ ተዘርፋ እንዳልነበረች ሆነች። ሞኙ ያገሬው ሕዝብም በሳቸውን ከስልጣን መውረድ ሀገራቸው ምድረ ገነት የሆነች ያልህ ጨፈሩ።

ያገረውን ህዝብ በዚህ ያህል መጨፈርና መደሰት የተገነዘቡት ምዕራባዊያን "ለምን የዚህን ህዝብ ደስታ ላይ ደስታ አንደርብላቸውም" በማለት Decmber 30, 2006 #በእለተ_አረፋ በአደባባይ በስቅላት ገደሏቸው።

እሳቸው በህዝባቸው ፊት ያውም በእለተ አረፋ በአደባባይ እንደተሰቀሉት ሁሉ ዛሬ ላይ ሀገራቸውና ህዝባቸው በዓለም ፊት የደሃ ደሃ ተብለው ከተመዘገቡት ሀገራት ተርታ ሆነዋል። በየእለቱም በአገሪቱ በተፈለፈሉ አሸባሪ አካላት በዓለም አደባባይ ይሰቀላሉ።መሪህን በስሜት አሳልፈህ አትስጥ።

እኚህ ሰው ማናቸው!?!?!?
( ሁሴን አብደላ ሁሴን)

ለመላው የእስልምና ተከታዮች መልካም የአረፋ በዓል በድጋሜ ኢድ ሙባረክ እንኳን አደረሳችሁ
M.B