Get Mystery Box with random crypto!

"መምህር ምህረተአብ አሰፋ ምን አስተማሩ"

የቴሌግራም ቻናል አርማ ortoteach — "መምህር ምህረተአብ አሰፋ ምን አስተማሩ"
የቴሌግራም ቻናል አርማ ortoteach — "መምህር ምህረተአብ አሰፋ ምን አስተማሩ"
የሰርጥ አድራሻ: @ortoteach
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.95K
የሰርጥ መግለጫ

ኑ መልካሙን መልካሙን እናውጋ፣እናውራ

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

3

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-14 00:17:28
679 views21:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 10:18:47 ꔰ ሰኔ ፳፩ = ሰኔ ጎለጎታ ወሕንፀተ ቤተክርስቲያን
እንኳን ለእናታችን ለእመቤታችን ለቅድስተ ቅዱሳን ለድንግል ማርያም ሰኔ ጎለጎታና ሕንፀተ ቤተ ክርስቲያን (ለመጀመሪያ ጊዜ ቤተ ክርስቲያን ለታነጸበት) ክብረ በዓል በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ፡፡
‹‹ሰኔ ጐልጐታ፤ ችግር የምትፈታ፤
ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያም በዚህ ቀን ሰኔ ፳፩ ልጇን ወዳጇን ጎለጎታ በሚባል ቦታ ላይ እንበዋ እንደ ጅረት እስኪፈስ ድረስ ለኃጥአን ምሕረትን ለምናዋለች:: ጌታችንም ‹‹ስምሽን የጠራውን፤ በቃል ኪዳንሽ ያመነውን ሁሉ እምርልሻለሁ፡፡›› ብሎ ቃል ኪዳን ሰጥቷታል፡፡
ህንጸተ ቤተክርስቲያን (የቤተ ክርስቲያን መታነጽ)
ታላቅ በዓል ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውኃ ፈሻሽ የመጣችና ሩቅ ብእሲ የመሠረታት ሳትሆን እራሱ ጌታችን አምላካችን በገዛ ደሙ የመሠረታት ናት፡፡ ሐዋ 20፡28፡፡ በዕለተ ዐርብ በዕፀ መስቀል ላይ ከጌታችን የፈሰሰውን ቅዱስ ደም ቅዱሳን መላእክት በብርሃን ፅዋ ቀድተው በዓለም ሁሉ
ረጭተውታል፡፡ ስለሆነም የጌታችን ወርቀ ደም በነጠበባቸው ቦታዎች ሁሉ ላይ ዛሬም ድረስ ቤተ ክርስቲያን ይሠራባቸዋል፡፡
የብርሃን እናቱ ንግሥተ ሰማይ ወምድር
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ረድኤት በረከቷ ይደርብን፣ በጸሎቷ: በምልጃዋ: ከኃጥያትና ከበደል : ከመከራ ሥጋና ከመከራ ነፍስ ትጠብቀን: አሜን።
984 views07:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-24 20:20:28 ፤ አቤቱ፥ አንተን ታመንሁ፤ ለዘላለም አልፈር።
፤ በጽድቅህ አስጥለኝ ታደገኝም፤ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል አድነኝም።
፤ በጠንካራ ቦታ ታድነኝ ዘንድ አምላክና መሸሸጊያ ሁነኝ፤ ኃይሌ መጠጊያዬ አንተ ነህና።
፤ አምላኬ፥ ከኃጢአተኛ እጅ፥ ከዓመፀኛና ከግፈኛም እጅ አድነኝ።
፤ አቤቱ፥ አንተ ተስፋዬ ነህና፥ እግዚአብሔር ሆይ፥ ከታናሽነቴ ጀምረህ መታመኛዬ ነህና።
፤ ከማኅፀን ጀምሮ በአንተ ተደገፍሁ፥ ከእናቴም ሆድ ጀምሮ አንተ መሸሸጊያዬ ነህ፤ ሁልጊዜም ዝማሬዬ ለአንተ ነው።
፤ ለብዙዎች መደነቂያ ሆንሁ፤ አንተ ግን ብርቱ መጠጊያዬ ነህ።
፤ አፌን ምስጋና ምላ ሁልጊዜ ክብርህንና ግርማህን እዘምር ዘንድ።
፤ በእርጅናዬ ዘመን አትጣለኝ፥ ጕልበቴም ባለቀ ጊዜ አትተወኝ።
፤ ጠላቶቹ በላዬ ተናግረዋልና፤ ነፍሴንም የሚሹአት በአንድነት ተማክረዋልና፥ እንዲህም አሉ።
፤ እግዚአብሔር ትቶታል፤ የሚያድነው የለምና ተከትላችሁ ያዙት።
፤ አምላክ ሆይ፥ ከእኔ አትራቅ፤ አምላኬ ሆይ፥ እኔን ለመርዳት ፍጠን።
መዝሙረ ዳዊት ምዕ. 71 ቁ1-12
963 views17:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 12:55:35
በሀገረ እግዚአብሔር / በቅድስት ምድር /
በእመቤታችን ርስተ ምድር በሆነችው በኢትዮጵያ የሰው ልጅ ደም እየፈሰሰ ነው ፡፡
ኢትዮጵያ ሹሙ እንደ ጠፋበት ንብ ህዝቡ ከተበታተነ ሰነበተ። የሰው ሕይወት የውሻ ሕይወት ያክል ተቆጥሮባታል ፡፡
አምላክ ከ 22ቱ ፍጥረታት ለይቶ አምላካዊ ክብሩን
የሰጠው የሰው ፍጡር እየሞተም እየገደለም ነው ፡፡ ሰው ሠውን እያደነ ነው ፡፡
ከሰው ሕይወት ይልቅ ስንዝር መሬት ትልቅ ከበሬታ አግንታለች። ሁሉም ነገ ጥሎት ለሚሄድ መሬት እየተስገበገበ ነው። በዚች ሀገር የጥይት
ባሩድ እየሸተተ ነው ፡፡ ህዝቡ ደስታውን ሳያጣጥም ጥቁር ደመና እየመጣበት ነው ፡፡ በዚች ሀገር ፈሪሀ እግዚአብሔር ያለው አስታራቂ ሽማግሌ ይፈለጋል፡፡
ቅዱሳን የመነኑበት ምድር በእግዚአብሔር ቁጣ እንደ እስራኤላውያን ቤተ መቅደስ እንዳትሆን እንፈራለን፣የሙሴ ጽላት ያለባት ምድር የሶረያን እጣ እንዳታገኝ እንፈራለን። ምንግዜም ሰው ሲያጠፋ ሀገር ባድማ ትሆናለች፡፡
በፈረሱ የተማመነ ይጠፋል ይላል ነብዩ ዳዊት።
የፈርዖን ታሪክ እንዳይደገም እንፈራለን ፡፡ የሰው ደም ከባድ ነው። ትልቅ መከራ ያስከፍላል ፡፡ ሳጥናኤል ክፉ
ነው። ከላይ ከትዕቢት ተራራ ላይ ሰቅሎ ወደ ውርደት ሸለቆ ይፈጠፍጣል፡፡
ምን ይሁን ኢትዮጲያውያን እርስ
በርስ አዳኝና ታዳኝ ሆነው በደማቸው ይራጫሉ ፡፡
አንደበቱ ቅባ ቅዱስ የተቀባ መሪ እቺ ሃገር ትፈልጋለች።
936 views09:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-20 11:12:34
አማላጃችን ሚካኤል ሆይ ፈጥኖ ደራሻችን ሚካኤል ሆይ የጌታን ዙፋን ከሚያጥኑ ሱራፌል ካህናት አንዱ ሰማያዊ ካህን አንተ ነህ ። የሰማያውያን ሊቃነ መላእክት ሁሉ አንተ አለቃቸው ነህ ። ይልቁንም የልዑላንም ልዑል አንተ ነህና በጠራሁህ ጊዜ ሁሉ በይቅርታና በቸርነት ድረስልኝ አትራቀኝ።"
(መልክአ ሚካኤል)
778 views08:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 12:17:43
አንተን ታምኛለሁና በማለዳ ምሕረትህን አሰማኝ፤ አቤቱ፥ ነፍሴን ወደ አንተ አንሥቻለሁና የምሄድበትን መንገድ አስታውቀኝ።
፤ አቤቱ፥ ወደ አንተ ተማፅኛለሁና ከጠላቶቼ አድነኝ።
፤ አንተ አምላኬ ነህና ፈቃድህን ለማድረግ አስተምረኝ፤ ቅዱስ መንፈስህም በጽድቅ ምድር ይምራኝ።
፤ አቤቱ፥ ስለ ስምህ ሕያው አድርገኝ፤ በጽድቅህም ነፍሴን ከመከራዋ አውጣት።
፤ በምሕረትህ ጠላቶቼን ደምስሳቸው፥ እኔ ባሪያህ ነኝና ነፍሴን የሚያስጨንቁአትን ሁሉ አጥፋቸው።
መዝሙረ ዳዊት ምዕ. 143 ቁ 8-12
785 views09:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 08:56:09
ሰኔ ፆም ነገ ሰኞ ይጀምራል
ጾመ ሐዋርያት / የሴኔ ጾም /
ቅዱሳን ሓዋርያት ለስብከተ ወንጌል ወደ ዓለም
ከመበተናቸው በፊት አገልግሎታቸው የተቃና እንዲሆን
የጾሙት ጾም ነው ፡፡
12 ናቸው ፡፡ ግን ዓለምን አዳረሷት ፡፡ መንፈስ ቅዱስን
ተቀብለናል ብለው ይበቃናል አላሉም ፡፡ ጾም ጨመሩበት ፡፡
መንገዳቸው ተቃና ፡ አውሬው ሰገደላቸው ፡ አንደበታቸው
እንደ ማር ጣፈጠ ፡፡
ዓልጫውን ዓለም በጨው / በስብከታቸው አጣፈጡት ፡፡
ክርስቲያን የአባቶቼ ጾም የኔም ነው ሲል ይህን ጾም ይጾማል
ፆሙን የበረከት ያድርግልን
1.3K views05:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-03 19:52:10
@ortoteach
@ortoteach
@ortoteach
Share share .....lililoch endidars share share adergut wudd betsboch
974 views16:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-03 07:49:07
919 views04:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-02 22:46:38
እንኳን ለጌታችንና ለመድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአለ እርገት አደረሳችሁ
823 views19:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ