Get Mystery Box with random crypto!

#ነሀሴ 26 በዓለ ፅንሰቱ ለወላዴ አእላፍ አቡነ ኢየሱስ ሞአ ዘ ሃይቅ እስጢፋኖስ ወ አቡነ ሀብተ | ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ

#ነሀሴ 26 በዓለ ፅንሰቱ ለወላዴ አእላፍ አቡነ ኢየሱስ ሞአ ዘ ሃይቅ እስጢፋኖስ ወ አቡነ ሀብተ ማርያም ጻድቅ

"+ እግዚአብሔር ፍርድን ይወድዳልና:: ቅዱሳኑንም አይጥላቸውምና:: ለዘለዓለምም ይጠብቃቸዋል . . .
ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ:: በእርስዋም ለዘላለም ይኖራሉ:: የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል::
አንደበቱም ፍርድን ይናገራል:: የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው:: በእርምጃውም አይሰናከልም:: +"+

(መዝ. 36:28-31)

"+ ለመንጋው ምሳሌ ሁኑ እንጂ ማሕበሮቻችሁን በኃይል አትግዙ:: የእረኞችም አለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማያልፈውን የክብርን አክሊል ትቀበላላችሁ:: እንዲሁም ጐበዞች ሆይ! ለሽማግሌዎች ተገዙ:: ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ:: እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና:: ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል::

+ (1ዼጥ. 5:3)

#ስንክሳር ዘወርሃ ሐምሌ

ሰው ሁሉ ለመናገር የዘገየ ለመስማት የፈጠነ ይሁን !

   (ያዕቆብ 1፥19)

   < ወስብሐት ለእግዚአብሔር >

     #መልካም ቀን

  #ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል  
@ortodoxtewahedo