Get Mystery Box with random crypto!

#አደይ በተሰኘው ድራማ ላይ የዚች ሴት ገጸ ባህሪ እጅጉን ይገርማል። ማለትም አማኝ ነች መስቀል አ | ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ

#አደይ በተሰኘው ድራማ ላይ የዚች ሴት ገጸ ባህሪ እጅጉን ይገርማል። ማለትም አማኝ ነች መስቀል አርጋለች በተቃራኒ ቆማ ከምታምነው እምነት ውጭ ግን ጠንቋይ ቤት ነው መፍትሔ ፍለጋ የምትሄደው። #ድራማ በማህበረሰብ ላይ ትልቅ ተጽኖ የመፍጠር አቅም አለው። በዚህ ገጸ ባህሪ ውስጥ የምትተውነው ሴት ኃይማኖቱ በፍጹም ሊፈቅደው በማይችል ነገር ላይ ተጠምዳ መታየቷ ለተመልካች የሚያስተላልፈው መልክት በእጅጉን ደስ የማይል ነው።

በተደጋጋሚ የሚሰሩ ድራማዎቻችን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ በማትከተለው በማትሰብከው እኩይ ተግባራት ተጠምደው አንዳንዴ የቄስ ካራክተር በመላበስ ሁላ ካህናትን ክብር በሚነካ መልኩ ይተውናሉ። ይሄ ድርጊት አለም ላይ በማህበረሰብ ላይ ተጽኖ በሚፈጥረው የቴሌቪዥን ድራማ እና ፊልም በተደጋጋሚ መሰራቱ በእጅጉ ጸያፍ የሆነ ተግባር ነው።

በዚህ አጋጣሚ ማህተም አስረህ አስረሽ ቤተክርስቲያን የማትፈቅደው ቦታ ስትገኝ ስትገኚ ስንገኝ የምናስተላልፈው መልክት የእነሱ ኃይማኖት ይፈቅዳል እኮ የሚያስብል መሆኑን እናስብ። መሃተብ አስረን መዝፈን በየጭፈራ ቤቱ መገኘት እርቃን እያሳዩ ፎቶ መነሳት እና የመሳሰሉት ድርጊቶች በጣም ልንተዋቸው ይገባል።

ከ #ፓፒዮ


ሰው ሁሉ ለመናገር የዘገየ ለመስማት የፈጠነ ይሁን !

   (ያዕቆብ 1፥19)

   < ወስብሐት ለእግዚአብሔር >

     #መልካም ቀን

  #ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል  
@ortodoxtewahedo