Get Mystery Box with random crypto!

ሚስጥረ ስላሴ ምስጢረ ሥላሴ፦ስለ ስላሴ ምስጢር የሚናገር ትምህርት ማለት ነው። እግዚአ | ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች

ሚስጥረ ስላሴ

ምስጢረ ሥላሴ፦ስለ ስላሴ ምስጢር የሚናገር ትምህርት ማለት ነው። እግዚአብሔር አንድነቱ ሦስትነቱን ሳይጠቀልለው፤ ሦስትነቱ አንድነቱን ሳይከፋፍለው በአንድነትና በሦስትነት የሚመሰገን አንድ ሕያው አምላክ ነው።

<= >የእግዚአብሔር ሦስትነት ስንል፦ እግዚአብሔር የማይለያይና የማይቀላቀል ፍጹም የሆነ ሦስትነት አለው ማለታችን ነው። የእግዚአብሔር ሦስትነት በስም በግብር  በአካል ነው።

<= >እግዚአብሔር በስም ሦስት ነው ስንል ሦስት የተለያዩ ስሞች አሉት ማለታችን ነው። እነዚህም፦ #አብ #ወልድ መንፈስ ቅዱስ  የሚባሉት ሲሆኑ እርስ በርሳቸው አይወራረሱም፤ አንዱ በሌላው ስም አይጠራም።  "ዘፍጥረት1፡ 2 "  "ምሳሌ30፡4" ።

>እግዚአብሔር በግብር ሦስት ነው፦ ስንል ሦስት የተለያዩ የአካል ሥራዎች አሉት ማለት ነው።  እነሱም፦
መውለድና ፤ማስረጽ የአብ
መወለድ፡ የወልድ
መስረጽ፡ የመንፈስ ቅዱስ ፤ የሚሉት ሲሆኑ የአካል ግብር ይባላሉ። "መዝሙር2፡7"
<=>እግዚአብሔር በአካል ሦስት ነው ማለት ደግሞ 
ለአብ፤ ፍፁም መልክ፤ ፍፁም ገጽ፤ ፍፁም አካል አለው። 

ለወልድ፤ ፍፁም መልክ፤ ፍፁም ገጽ፤ ፍፁም አካል አለው ።

ለመንፈስቅዱስ፤ፍፁም መልክ፤ ፍፁም ገጽ፤ ፍፁም አካል አለው ማለታችን ነው። <=>የሦስቱ የእግዚአብሔር ስሞችትርጉም

አብ፦ ማለት አባት ማለት ሲሆን የሚወልድ፤የሚያሰርጽ ወይም የሚያስገኝ ያለ እናት ወልድን የወለደ፤ መንፈስ ቅዱስን ያሰረጸነው።

ወልድ፦  ልጅ ማለት ሲሆን የሚወለድ ወይም ያለ እናት ቅድመ ዓለም፤ ያለ አባት ድህረ ዓለም  የተወለደ ነው። "መዝሙር2፡7" መንፈስቅዱስ፦ ረቂቅ፤ ልዩ፤ ንፁህ; ከፍጡራን መናፍስት ሁሉ የተለየ  ማለት ነው። "ኢዮብ26፡13"


የቅድስት ስላሴ እረድኤት
በረከታቸው አይለየን አሜን

አ       አ         አ
  ሜ        ሜ       ሜ
      ን        ን           ን

ሼር....ሼር...
              Join @ortodoxslijoch