Get Mystery Box with random crypto!

ግንቦት 27 እንኳን ለበዓለ ጰራቅሊጦስ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡ ቃሉ የግሪክ ሲሆን ትርጓሜው | ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች

ግንቦት 27 እንኳን ለበዓለ ጰራቅሊጦስ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡

ቃሉ የግሪክ ሲሆን ትርጓሜውም አፅናኝ መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው፡፡
☞ይህ በዓል ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተነሣ በሃምሳኛው
በዐረገ በአሥራኛው ቀን በድምቀት ይከበራል፡፡
☞ለሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ የወረደው ከጠዎቱ ሦስት ላይ ነበር፡፡

☞ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱሳን ሐዋርያት በተናገረው
አምላካዊ ቃል መሠረት"ኃይልን እስክትለብሱ በኢየሩሳሌም ቆዩ" ብሏቸው ነበር
ሰዓቱ ሲደርስ የሚያጽናኑበት ብርታት የሚሆናቸው የዕውቀት፤ የኃይል መንፈስ
ቅዱስ ሰደደላቸው፡፡
☞"በዓለ ሃምሳም የተባለው ቀን በደረሰ ጊዜ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው አብረው
ሳሉ ድንገት እንደሚቃጠል ዐውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምጽ መጣ በሁሉም መንፈስ

ቅዱስ ሞላባቸው መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደ ሠጣቸው በሌላ ልሣኖች ይናገሩ
ጀመር"(የሐዋርያት ሥራ 2፥1-11)
☞ይህችንም ዕለት ሊቃውንት የቤተ ክርስቲያን የልደት ቀን በማለት ይጠሯታል፡፡
☞ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ "መንፈስ ቅዱስ በበዓለ ሃምሳ ባይወርድ ኖሮ
ቤተክርስቲያን በኮሰሰች ነበር"በማለት የበዓሉን ታላቅነት መስክሯል፡፡

☞" እግዚአብሔር ይላል በመጨረሻም ቀን እንዲህ ይሆናል እንዲህ ይሆናል
ሥጋ በለበሱ ሁሉ ላይ ከመንፈሴ አፈሳለሁ ወንዶችና ሴቶች ልጆችሁም ትንቢት
ይናገራሉ ጎበዞቻችሁም ራእይ ያያሉ ሽማግሌዎቻችሁ ሕልም ያልማሉ ደግሞም
በዚያች ወራት በወንዶችና በሴቶች ባሪያዎቼ ላይ ከመንፈሴ አፈሳለለሁ የሚል

ትንቢት ይናገራሉ"(ትንቢተ ኢዮኤልምዕራፍ 2ከቁጥር 28)
☞መንፈስ ቅዱስ ለምን ይወርዳል?
☞መንፈስ ቅዱስ ሊያጽናና ሊረጋጋ እንደሚወርድ በወንጌል ተነግሯል፡፡
☞"አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነ አጽናኝ እርሱ ሁሉን
ያስተምራቸው እኔም እኔ የነገረሸኅችሁን ሁሉ ያሳስባችኃል፡፡(ዮሐ 14፥25)
☞ - - - እኔ ግን እውነት እነግራችኀለሁ፤ እኔ እንድሔድ ይሻላችኅል፡፡

እኔ
ባልሔድ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣም፤እኔ ብሔድ ግን አርሱን እልክላችኀለሁ፡፡
(ዮሐ 16፥7)
☞ከዐረገ በኃላ መንፈስ ቅዱስ ሊያጽናናቸው እንሚመጣ ተናገረ፡፡
☞መንፈስ ቅዱስ ምሥጢር ሊገልጥ ይወርዳል፡፡
☞"የምነግራችሁ ገና ብዙ አለኝ ነገር ግን አሁን ልትሸከሙት አትችሉም ግን
እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኅል፡፡(ዮሐ
16፥12-13)

☞"እንዲህ አላቸው ወደ ዓለሙ ሁሉ ሒዱ ወንጌልን ለፍጥረት ስበኩ(ማር
16፥15)ብሎ በዓለም ሁሉ ያለውን ቋንቋ እንዲያውቁ አድርጎ ወንጌልን ለአለም
እንዲሰብኩ ልኳቸዋል፡፡
☞ለሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ በወረደበት እለት የተለያዩ ቋንቋ ተገልጦላቸዋል፡፡
(ሐዋ 2፥3)
☞እኛም ጰራቅሊጦስ ለዋርያት መንፈስ ቅዱስ የወረደበት፤ የቤተክርስቲያን
ልጆች መሠረት የተጣለበት ቀን በመሆኑ መንፈስ ቅዱስ ያጸናን፤ ይቀድሰን፤
ምሥጢሩን ይገልጥልን ዘንድ በማሰብና በመማፀን በዓሉን እናከብራለን፡፡

(ከመድበለ ታሪክ መጽሐፍ የተወሰደ)
☞ጰራቅሊጦስ የወርቅ ሐር ግምጃ የቅዱሳን የጌጣቸው ልብስ ነው፡፡
☞ጰራቅሊጦስ የጻድቃን የባለሟል ነታቸው የራስ ወርቅ ነው፡፡
☞ጰራቅሊጦስ ሐዋርያትን በሀገሩ ሁሉ ቋንቋ ያናገረ ነው፡፡
☞ጰራቅሊጦስ ሐዲስ ወንጌልን ያስተማረ ዘንድ ጳውሎስን የጠቀሰ የሕይወት
መብረቅ ነው፡፡
☞ጰራቅሊጦስ ሐዋርያትን የወይን ጠጅ ሳይጠጡ ያሰከረ ነው፡፡

☞ጰራቅሊጦስ በጽዮን አደባባይ በቶማስ ላይ በቅዱስ ነቢይ ፊት የበራ ነው፡፡
☞ጰራቅሊጦስ ፍጹም የከበረ የአብና የወልድ የባሕርይ ሕይወት ነው፡፡
☞ጰራቅሊጦስ የማይዳሰስ የእሳት ነበልባል ነው፡፡
☞ጰራቅሊጦስ መጉደል ወይም መጨመር ሳይኖርበት በህልውናው አምላክ
ነው፡፡
☞ጰራቅሊጦስ እንደ አብና እንደ ወልድ በሰማያትና በምድር ሁሉ ላይ መንግሥቱ
የመላ ነው፡፡

☞ጰራቅሊጦስ አሸናፊ ነው ለሰማዕታት መመኪያ የተሰበሩትን የሚጠግን ነው፡፡
☞ቅድመ ዓለም ለነበረ ፍጹም አንድነቱ ለሱ ስግደት ይገባል ዛሬም ዘወትርም
ለዘላለሙ አሜን፡፡(የሀሙስ ሰይፈ ስላሴ)
☞ለእኛም ወደ አንተ የሚወሰደውን ቀናውን መንገድና የሀይማኖት ጽናቱን እና
ማስተዋል ግለጽልን፡፡መልካም በዓል ይሁንላችሁ፡፡