Get Mystery Box with random crypto!

​​#ቃና_ዘገሊላ በዛሬው ዕለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማ | ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

​​#ቃና_ዘገሊላ

በዛሬው ዕለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያምና ከሐዋርያቱ ጋር የገሊላ ክፍል በሆነችው በቃና በሰርግ ቤት ተገኝቶ ውሃውን ወይን ጠጅ ያደረገበት ነው። ሰርግ ደግሶ የነበረው ዶኪማስ አዘጋጅቶት የነበረው ወይን ጠጅ አልቆ በተጨነቀ ጊዜ ችግሩን ቀርቦ ሳይነግራት ማለቁን አውቃ ልጄ ሆይ ወይን ጠጅ እኮ አልቆባቸዋል በማለት ተናግራ ውሃው ወደ ወይን ጠጅ እንዲለወጥ የማማለድ ተግባር የፈጸመችበት ዕለት ነው።

አምላካችን ጋብቻ ክቡር መሆኑን ዓለም እንዲረዳ ያደረገበት፣ ሰዎች ያዘጋጁት ነገር ተንጠፍጥፎ አልቆ በተጨነቁ ጊዜ እመቤታችን ለልጇ አሳስባ ጎደሏቸው እንዲሞላ ፣ጭንቀታቸው እንዲወገድ የምታደርግበት በዓል ነው።

ጥንቱ ዕለቱ የካቲት 23 ቀን ቢሆንም ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን የውሃን በዓል ከውሃ በዓል ጋር ማክበር ይገባል ብለው የሚጠጡት አልቆባቸው ተጨንቀው የነበሩበት ቃና ዘገሊላ የውሃ በዓል በመሆኑ ከውሃ በዓል ከሆነውና የእዳ ደብዳቤያችን ከተደመሰሰበት ከጥምቀት ጋር እንዲከበር በማድረጋቸው በዛሬው ዕለት እናከብረዋለን።

ዛሬ የዶኪማስ ጭንቀት ብቻ ሳይሆን በጋብቻ ምክንያት የሚከሠት የክርስቲያኖች ሁሉ ጭንቀት የተቃለልበት ዕለት ነው። እመቤታችን ዶኪማስ ሳይለምናት ጭንቀቱን እንዳቃለለችለት ለልጅሽ አሳስቢልን ብለን ብንማጸናት የማይፈጸምልን ነገር፣ የማይወገድልን ጭንቀት አለመሆኑን የተረዳበት ዕለት ነው። በዓሉን ማክበር የሚገባንም ይህን እያሰብን ነው። አምላካችን ከበዓሉ በረከት ይክፈለን።

@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur