Get Mystery Box with random crypto!

ኦርቶዶክሳዊት ሴት

የቴሌግራም ቻናል አርማ orthodoxawit — ኦርቶዶክሳዊት ሴት
የቴሌግራም ቻናል አርማ orthodoxawit — ኦርቶዶክሳዊት ሴት
የሰርጥ አድራሻ: @orthodoxawit
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 868
የሰርጥ መግለጫ

ይህ መንፈሳዊ ቻነል በእግዚአብሔር ፈቃድ የወላዲተአምላክን ምልጃ ተገን በማድረግ አገልግሎትን ለማገዝ እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሴቶችን ኅብረት እና መንፈሳዊ ህይወት ለማጠንከር ታስቦ የተከፈተ ነው።ፃታ አይለይም።ዓላማውን የሚደግፉና ቤተክርስቲያንን ለመጥቀምና ለማወቅ የሚወዱ ሁሉ እንዲገቡ ክፍት ነው።

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-04-01 23:24:49
1.0K views20:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-30 17:42:26
1.0K views14:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-06 22:10:27
1.4K views19:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-03 20:40:21
1.2K views17:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-03 20:40:20
1.0K views17:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-03 20:40:06 እቴጌ ጣይቱ በአድዋ
እንኳን ለ126ኛው የአድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ!

የእቴጌ ጣይቱን ሃይማኖተኝነት ከሚገልፁ ጉዳዮች መካከል አንዱ በአድዋ ጦርነት ወቅት ለጣልያኖች አድረው የነበሩት ባሻ አውአሎም በመጨረሻ ለኢትዮጵያ መሰለል እንደሚፈልጉ ተናዘዙ። እናም የጣልያኖችን የጦር አሰላለፍ አስረዱ። ወደ ጣልያኖችም ዘንድ ሄጄ ስለ ኢትዮጰያ አሰላለፍ የተዛባ መረጃ እሰጣቸዋለሁ አሉ።ታዲያ እቴጌይቱ ይህንን አባባል እንዴት ይመኑት? ዋሽቷቸው ቢሆንስ? እናም የባሻ ቃል እውነት መሆኑን ለማረጋገጥ እቴጌ ጣይቱ ምግብ አቀረቡ እንዲህም አሏቸው።“እኔ አሁን የማቀርብልህ ምግብ የእግዚአብሔርን ስም ጠርቼ ነው።አንተም የእግዚአብሔርን ስም ጠርተህ ስጋወደሙ እንደምትቀበል አርገህ ቁጠረው፣የተናገርከውን ሁሉ የምትፈጽም መሆንህን ማልና የቀረበልህን ምግብ ብላ!” ባሻ አውአሎምም ምለው በሉ እንዳሉትም በመሀላቸው መሠረት ለሀገራቸው መረጃ ሰጡ።

እቴጌ ጣይቱ በጊዜው ሴቶች ሊያገኙት በሚችሉት ትምህርት አንፃር እጅግ የላቀ መንፈሳዊ ትምህርት አግኝተው ነበር፡፡እቴጌ ጣይቱ ምንም እንኳን መፃፍ ባይችሉም አዘውትረው ያነቡ ነበር፡፡ ስንክሳር በሚነበብበት ግዜ ሁሉ ሳይቀር ስህተቶችን በመጠቆም የሚጠብቀውንና የሚላላውን በማስገንዘብ በንባቡ ስልት ላይ አስፈላጊውን ማስተካከያ ይነግሩ እንደነበር ድርሳናት ያስረዳሉ፡፡

ታዋቂው ታሪክ ጸሐፊ ተክለ ጻድቅ መኩሪያ፣ “አፄ ምኒልክና የኢትዮጵያ አንድነት” በሚለው መጽሐፋቸው “እቴጌ ጣይቱ በተፋፋመው የአድዋ ጦርነት ውስጥ ጥላ አስይዘው፣ ዓይነ ርግባቸውን ገልጠው፣ በእግር እየተራመዱ በንጉሠ ነገሥቱ ልጅ በወ/ሮ ዘውዲቱና በደንገጡሮች ታጅበው በጦርነቱ መካከል መገኘታቸውን፣… አቡነ ማቴዎስም የማርያምን ታቦት አስይዘው፣ ከቀሳውስትና ከመነኮሳት ጋር ሆነው፣ የጊዮርጊስን ስብሐተ ፍቁርን እያዜሙ ሲከተሉ ዜማው ሳያልቅ በፊት ጦርነቱ በኢትዮጵያ አሸናፊነት መደምደሙን” ጽፈዋል።

“…..9 ሰዓት ግድም ሲሆን የአጤ ምንሊክ ጦር ቁስለኛ እና ምርኮ እየያዘ ከጦርነቱ ቦታ መመለስ መጀመሩን ባዩ ግዜ እቴጌይቱ “ንጉሱ ሳይመለሱ ወዴት ነው የምትመለሱት? አሁንም ቁስለኞቹን እና ምርኮኞቹን ለእኔ እየሰጣችሁኝ እናንተ ወደዚያው ተመለሱ!” ብለው ጮሁባቸው፡፡ከእሳቸው ጋር ያለች እህታቸው ወ/ሮ አዛለች ምርኮ ይዞ የሚመለሰውን ሰው ባየች ግዜ “ንጉሥህን፣ጮማና ጠጅህን ትትህ የምትመለሰው በዓድዋ ቤት አለህን ?”ብላ ለፈፈች፡፡ የአጤ ምንሊክ ደግነት ወንዱን ብቻ ሳይሆን ሴቱንም መነኮሳቱንም አጀገነው፡፡

በጸሐፌ ትእዛዝ ገብረሥላሴ ጽሑፍ ላይም የኋለኛው ሰልፍ እንደመወዝወዝ (መወላወል) ሲል በዩት ግዜ እቴጌ ጮኸው “አይዞህ አንተ ምን ሆነሃል? ድሉ የእኛ ነው!” ብለው አሉት ሰውም የተናገሩትን ቃልና እቴጌን ባየ ግዜ ሴት ሲያበረታ ወንድ መሸሽ አይሆንለትምና ጸጥ አለ፤ወደኋላ ሊመለስ የነበረው ወታደርም ወደፊት ገሰገሰ፡፡
ስለዚህ በዚህ ጦርነት ከጦር ሰራዊቱ እኩል ተሰማርተው ዘመቻውን የተካፈሉትን ሁሉ ሳናደነንቅ እና ሳናመሰግን አናልፍም!
849 views17:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-15 11:54:01
የካቲት ፰ በዚህም ዕለት ከአሴር ወገን የሆነች የፋኑኤል ልጅ ነቢዪት ሐና አረፈች፡፡ የእርሷም ዘመኗ አልፎ ነበር በድንግልና ከኖረች በኋላ ከባሏ ጋር ሰባት ዓመት ኖረች። ሰማንያ አራት ዓመት ፈት ሁና ኖረች በጾምና በጸሎትም እያገለገለች ቀንም ሌትም ከምኲራብ አትወጣም ነበር።

ጌታችን ኢየሱስን ከተወለደ በኋላ በአርባ ቀን ወደ ቤተ መቅደስ በአስገቡት ጊዜ በዚያን ሰዓት ተነሥታ አመነች እግዚአብሔርንም አመሰገነችው። የኢየሩሳሌምን ድኅነት ተስፋ ለሚያደርጉ ሁሉ ስለርሱ ነገረች። ከዚህም በኋላ በሰላም አረፈች።
በረከቷ ይደርብን!
850 views08:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-13 23:07:05 ከሊቀሊቃውንት ሥሙር አላምረው የፌስቡክ ገጽ የተገኘ
794 views20:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-13 23:06:32 "ቦኑ ዘሞተ እምእለ ያፈቅሩኪ፤
ከሚዎዱሽ ወንዶች የሞተ አለ?"

ጊዜው፥ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
ማስተማር የጀመረበት፣ሐዋርያት በምልዓት ያልተጠሩበት፣ የዮሐንስ መጥምቅ ትምህርት የተፈጸመበት ወቅት ነው።
በዚያ ዘመን በገሊላ ናይን(Nain) ከተማ ይኽ ከዚኽ ቀረሽ የማትባል 'የደም ገምቦ' መልከ መልካም ሴት ነበረች። ውበቷ የኀጢኣትም የገንዘብም 'ትርፍ' ኾኗት ብዙ ጊዜ ቆይታለች።
ከዕለታት አንድ ቀን እንደልማዷ በመስታዎት ፊት ቆማ ከእግር ጥፍሯ እስከ ራስ ጠጕሯ ውበቷን ተመለከተች።
ነገር ግን የመስታወቱ ምልሰት ላይ ከፊት ያለው ውበቷን ያይደለ ሞቷንና ኀጢኣቷን የነፍሷንም ድካም ተመለከተች።
ይኽም ራስን በጥልቀት የማየት ጉዳይ በሥጋ ዐይን አይኾንም።
መጽሐፍ "ወብነ ክልኤቲ አዕይንት ውሳጣውያት ህየንተ አዕይንት ሥጋውያት" ብሎ በነገረን በነፍስ ዐይን እንጂ።
በመስታዎቷ ፊት ቆማ በዘመን ፀሓይ ለሚረግፈው አበባነቷ እንዲኽ አለች፦
"ዘወትር ወደ ዝሙት የምትሮጡ እግሮቼ ኾይ ሞት በሚያሥራችኹ ጊዜ እንደምን ትኾናላችኹ? ልታመልጡ ትወዳላችኹ አይቻላችኹም...
ባንተ ብዙ ያጣኹ አንደበቴ ኾይ፦ ትመልስለት ዘንድ የማይቻልኽ የዐለም ኹሉ ገዥ የሚኾን ሞት ዝም ባሰኘኽ ጊዜ እንደምን ትኾናለኽ?"
ከድምፅ አልባው ምስሏ ጋር እንዲኽ ስታለቅስ ቆይታ
ከኀጢኣት ወደ ጽድቅ የሚመልሳትን ጌታ ልትፈልግ ወጣች። ግን ደገሞ ባዶ እጇን መኼድ አልወደደችም።
ሃድኖክ ወደሚባል ነጋዴ ኼዳ ውድ ሽቱ ለመግዛት ጠየቀችው።
የዘወትር ፈገግታዋን በፊቷ ላይ ያጣው ነጋዴም
"ማርያም! ምን ኾነሽ አዝነሻል?
ከሚወዱሽ ወንዶች የሞተ አለን?" ብሎ ጠየቃት።
እንዲኽ ስትል መለሰችለት
"እዎ ብዙኅ ኀጢኣትየ ሞተ ወእፈቅድ እቅብሮ፤ ብዙ ኀጢኣቴ ሞተ እቀብረው ዘንድ እወዳለኹ፡፡"

ዛሬ የካቲት ስድስት የዚች ባለሽቱ ማርያም ዘናይን ዕረፍት ነው::
[ማስታወሻ፦ ይቺ ብፅዕት ማርያም የአልዓዛር እኅት ማርያም ወይም መግደላዊት ማርያም አይደለችም]

ጸሎታ ወበረከታ የሀሉ ምስሌነ።
የካቲት /2013
861 views20:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-13 23:06:29
672 views20:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ