Get Mystery Box with random crypto!

መርጌታ የባህል ህክምና

የቴሌግራም ቻናል አርማ orthodox_channl — መርጌታ የባህል ህክምና
የቴሌግራም ቻናል አርማ orthodox_channl — መርጌታ የባህል ህክምና
የሰርጥ አድራሻ: @orthodox_channl
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.13K

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-04-10 08:49:56 የወደመውን የደብረ መድኃኒት ሰብሸንጎ መድኃኒአለም ቤተ ክርስቲያንን መልሶ ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ ተጣለ።
           የወደመውን የደብረ መድኃኒት ሰብሸንጎ መድኃኒአለም ቤተ ክርስቲያንን መልሶ ለመገንባት ዛሬ በ27/7/2015 ዓ/ም በዕለተ ቀኑ በብፁ አቡነ ዲዮናስዮስ የምስራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፀሎተ ቡራኬ የመሠረት ድንጋይ ተጣለ።
በእለቱ በዓሉንም ለማክበርና የአባታችንን ቡራኬ ለመቀበል ጭምር እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝበ ምእመን ተገኝቷል።
ዕለቱ የአመቱ መድኃኔ ዓለም ስለነበር ታቦቱ ወጥቶ ህዝበ ምእመኑን ባርኳል።
በእለቱ ስለክብረ በዓሉ ከሀገረ ስብከት በመጡ ሰባክያንና በብፅዑ አባታችን የምእመኑን መንፈስ የሚያፀናና ከሀዘኑ የሚያረጋጋ ጥዑም ትምህርት ተሰጥቷል።
በመርሀ ግብሩም መሰረት አጭር የሥራና ግልፅ የገቢ አሰባሰብ ሪፖርት ቀርቧል።
ብፅዑ አባታችንና ሰባክያን ከቀረበው ሪፖርት አንፃር የወደመው ቤተ ክርስቲያን በቅርብ ተገንብቶ እንደሚጠናቀቅ ያሳያል ብለዋል።መልሰን የማንገነባውና ድጋሚ የማናገኘው በህይወት ያጣነው ቅዱሱን ልጃችንን ነው በማለት ነፍሱን ከቅዱሳን እግር ስር እንዲያሳርፈው ተማፅነዋል። አያይዘውም መሰራት ያለበት ህንፃ ቤተክርስቲያን ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሔር ህንፃ የሆነው የሰው ልጅ ላይ ጭምር ነው።ስለዚህ ከቤተክርስቲያኑ ሥራ በተጓዳኝ ጠንካራ ጉባኤ ቤት ማቋቋምንም የፕሮጀክቱ አካል እንዲሆን አባታዊ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
በመቀጠልም ታቦተ ህጉን አስገብተን አጠር ያለ የገቢ ማሰባሰብ መርሀ ግብር ተከናውኗል።
በመርሀ ግብሩም አባታችን ለሥራ ጉዳይ ወደጀርመን ተንቀሳቅሰው በነበረበት ጊዜ የመንፈስ ልጆቻቸውን ጠይቀው አሰባስበው የመጡት 100,000.00 ከእኔ ታገኛላችሁ ብለዋል ህዝበ ምእመኑም እንዳቅሙ ድጋፍ በማድረግ በእለቱ ጥሬ ብር 180,542.50 የተሰባሰበ ሲሆን በእህልም ከፍተኛ ገቢ ማሰባሰብ ተችሏል።
ያሰባሰብነው አጠቃላይ ጥሬ ብር 4,500,000.00 ተሻግሯል በቅርብ 5,000,000.00 እንደምንገባ ተስፋ አለኝ።
125 views05:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-09 17:37:54
"አህያይቱንና ውርንጫዋንም አመጡለት፥ ልብሳቸውንም በእነርሱ ላይ ጫኑ፥ ተቀመጠባቸውም . . . የዘንባባ ዛፍ ዝንጣፊ ይዘው ሊቀበሉት ወጡ፦ ሆሣዕና፤ በጌታ ስም የሚመጣ የእስራኤል ንጉሥ የተባረከ ነው እያሉ ጮኹ።" ማቴ፦21፥7፤ ዮሐ፦12፥13
149 views14:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-09 16:04:42 ጥያቃ ሰላም  እድሜ  16 ነው በጣም ግዴለሽ ነኝ  በተጨማሪ ለውበቴ በጣም እጨነቃለሁ።

መልስ ተጻፈ፣ በስነ-ልቦና ባለሙያ

          . . . Bini Girmachew


ይሄን በመጫን 


https://t.me/+-E61ZVXcb0ExODRk
https://t.me/+-E61ZVXcb0ExODRk
https://t.me/+-E61ZVXcb0ExODRk  ያንብቡ
151 views13:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-09 10:36:28 ጥያቃ ሰላም  እድሜ  16 ነው በጣም ግዴለሽ ነኝ  በተጨማሪ ለውበቴ በጣም እጨነቃለሁ።

መልስ ተጻፈ፣ በስነ-ልቦና ባለሙያ

          . . . Bini Girmachew


ይሄን በመጫን 


https://t.me/+-E61ZVXcb0ExODRk
https://t.me/+-E61ZVXcb0ExODRk
https://t.me/+-E61ZVXcb0ExODRk  ያንብቡ
172 views07:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-09 08:14:02 ✞የዘመን ፍፃሜ✞

የዘመን ፍፃሜ  እስከዚህ  የሌለህ
ዘላለም የምትኖር (፫)ፍጹም አምላክነህ
           
   ሆሳዕና (፫) በአርያም

ቡሩክ  ሆሳዕና  አምላከ እስራኤል
ተቀምጦ መጣ (፫) በአህያ ግልገል
       አዝ= = = = =        
ትንሹም ትልቁም  በአንድነት ዘመሩ
አመሰገኑት (፫) ሆሳዕና እያሉ
      አዝ= = = = =
በጣም  ደስ  ይበልሽ  እልል  በይጽዮን
ንጉሥሽ መጣልሽ (፫) ሊሆንሽ መድኅን
                      
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
   https://t.me/Orthodoxss_Tewahdo
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ══╯
177 views05:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-08 21:16:39 ​​​​ሆሳዕና

በዕለተ ሆሳዕና እስራኤላውያን ለምን የዘንባባ ዝንጣፊ፤ የቴምር ዛፍ ዝንጣፊ እና የወይራ ዛፍ ዝንጣፊ ይዘው  ዘመሩ? (ማቴ. 21÷1-17፣ ማር. 11÷ 1-10፣ ሉቃ. 19÷29-38፣ ዮሐ. 12÷12-15)

                           የዘንባባ ዝንጣፊ፦
ይስሃቅ በተወለደ ጊዜ አብርሃም ደስ ብሎት ዘንባባ ይዞ እግዚአብሄርን አመስግኖበታል የደስታ መግለጫ በመሆኑ አነተ ደሰታ የምታስገኝ ሃዘናችንንም የምታርቅ አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡

ዘንባባ ደርቆ እንደገና ህይወት ይዘራል የደረቀ ሕይወታችንን የምታለመልም አምላክ ነህ ሲሉ ነው(
ዘንባባ የሰላም ምልክት ነው የሰላም አምልክ ነህ ሲሉ ነው
ዘንባባ እሾሃማ ነው አንተ ህያው አሸናፊ አምላክ ነህ ሲሉ ነው

ዘንባባ እሳት አይበላውም ለብልቦ ይተወዋል እንጅ ጌታም አንተ ባህርይህ የማይመረመር ነው ሲሉ ነው
ዘንባባ የነፃነት ምልክት ነው ከባርነት ነፃ የምታወጣን አንተነህ ሲሉ ነው አኛም ይህን በማሰብ ዘንባባ ይዘን ሆሳእና በአርያም እያልን እለቱን እናስባለን፡፡

                      የቴምር ዛፍ ዝንጣፊ፦
☞ የቴምር ዛፍ ፍሬ ጣፋጭ ነው፦ በሃጥያት የመረረውን ሂወታችን የምታጣፍጥልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው።

የቴምር ፍሬ የሚገኘው ከዛፉ ከፍታ ላይ ነው አንተ አምላካችን ልዑለ ባህሪ ነህ ከፍ ከፍ ያልክ አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
የቴምር ዛፍ ፍሬ በውስጡ ያለው ፍሬ አንድ ነው አንድ ባህሪ ነህ ሲሉ ነው።
የቴምር ፍሬ በእሾህ የተከበበ ነው ይህም የአንት ባህሪ የማይመረመር በእሳት የተከበበ ነው ሲሉ ነው።

                የወይራ ዛፍ ዝንጣፊ፦
የወይራ ቅጠል የሰላም ማብሰሪያ ነው ሰላማችንን የምታበስርልን የምታስገኝልን አንተ ነህ ሲሉ ነው፡፡
የወይራ ቅጠል ከእንጨት ሁሉ ጽኑ ነው አንተም ጽኑ ሃያል አምላክ ነህ ሲሉ ነው።

ወይራ ለመብራት ያገለግላል ፍሬው ዘይት ያወጣል ከወይራ የሚገኝ ዘይት ጨለማን አሸንፎ ብርሃን እንደሚሰጥ ሁሉ አንተም ጨለማ ህይወታችንን የምታስወግድልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
በኦሪት ግዜ የወይራ ዘይት ለመስዋአትነት ይቀርብ ነበር አንተም እንደ ዘይቱ ለመተላለፋችን መስዋዕት ሆነህ የምትቀርብ አምላክ ነህ ሲሉ ነው። በመስቀል ላይ መስዋዕት ሆኗልና።

በዓሉን በዓለ ክብር በዓለ ፍስሐ ያድርግልን፡፡ ከመጣብን መቅሰፍት መከራ እሱ በሀይል በስልጣኑ ይሰውረን ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን።

አቅራቢ ፦ ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት

➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
      𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆  
@Orthodox_Addis_mezmur
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
      𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 ‌‌
206 views18:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-08 19:05:35
213 views16:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ