Get Mystery Box with random crypto!

ቅዱሳን መጽሐፍት ምን ይላሉ?

የቴሌግራም ቻናል አርማ orthodox_betie — ቅዱሳን መጽሐፍት ምን ይላሉ?
የቴሌግራም ቻናል አርማ orthodox_betie — ቅዱሳን መጽሐፍት ምን ይላሉ?
የሰርጥ አድራሻ: @orthodox_betie
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 935
የሰርጥ መግለጫ

ክርስቲያን መግደል እንጂ ሞት አይፈራም
በቻናላችን የምንሰጣቸው አገልግሎቶች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስዕለማርያም
ስብከቶች
መዝሙሮች
ሲሆኑ ቻናላችነን ለመቀላቀል
@orthodox_betie በማለት ያገኙናል

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-12 17:09:28 ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬

የማንን መጽሐፍ በpdf ይፈልጋሉ

▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬

➛█➛ ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ሕማማት
የኤፍራጥስ ወንዝ
ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ
ቃና ዘገሊላ

➛█➛ አለማየሁ ዋሴ
እመጓ
ዝጎራ
መርበብት
ሰበዝ
ሚተራሊዮን

➛█➛ ፍስሀ ያዜ
የሳጥናኤል ጎል በኢትዮጵያ ፩
የሳጥናኤል ጎል በኢትዮጵያ ፪
የሳጥናኤል ጎል በኢትዮጵያ ፫
የሳጥናኤል ጎል በኢትዮጵያ ፬

➛█➛ የዶ/ር ሮዳስ ታደሰ
ማዛሮት
አንድሮሜዳ 1
አንድሮሜዳ 2

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
█ ▒ ░✞ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ❖ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ✞░ ▒ █
█ ▒ ░✞ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ❖ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ✞░ ▒ █
█ ▒ ░✞ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ❖ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ✞░ ▒ █
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
14 viewsኦርቶዶክስ ፕሮሞሽን ❖ ፪, 14:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 07:04:09 +++ቅዱስ ጳውሎስ
በኪልቂያ አውራጃ ጠርሴስ ከተማ የተወለደው ቅዱስ ጳውሎስ ከፈሪሳውያን ወገን ነው፡፡ የዘር ሐረጉ ከነገደ ብንያም እርሱም ሮማዊ እንደሆነ ራሱ ተናግሯል፡፡ በልጅነቱ አስተዋይ እንደነበር በቅዱሳት መጻሕፍት ይገልጻል፡፡ አስተዳደጉም የአይሁድ ሥርዓት ነበር፡፡ የመምህር ገማልያል ተማሪም ስለነበር የሕግ ትምህርት ተምሯል፤ ይህ ብቻም ሳይሆን ጥበብና እድም አብሮ እንደተማረና ጳውሎስ ድንኳን መስፋት ተምሮ እንደነበር ታሪኩ ምስክር ነው፡፡ በዚህም ጊዜ ይኖር የነበረው የሕግና ፍልስፍና ትምህርት ቤቶች በብዛት ይገኝባት በነበረችው የጤርሰስ ከተማ ነው፡፡
ጳውሎስ ሐዋርያ ከመሆኑ በፊት አስቀድሞ ሳውል ተብሎ የሚጠራ ክርስቲያኖችንም እያሳደደ የሚገድል ሰው ነበር፡፡ ለዚህም ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ማስረጃ ያደረጉት የእርሱ ለአባቶቹ ሕግ ቀናተኛ መሆኑ የክርስትናን ትምህርት እንዲቃወም ማድረጉን ነው፡፡ ‹‹ሳውል ግን አብያተ ቤተ ክርስቲያናትን ይቃወም ነበር፤ የሰውንም ቤት ሁሉ ይበረብር ነበር፤ ወንዶችንም ሴቶችንም እየጎተተ ወደ ወኅኒ ቤት ያስገባቸው ነበር፡፡›› (የሐዋ.፰፥፫)
በዚህ ብቻም አላበቃም፤ የቀድሞ ሳውል የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙርትን ለመግደል በመዛት ወደ እነርሱ ሄዶ ለሊቀ ካህናቱ የሥልጣን ደብዳቤ እንደለመናቸው መጽሐፍ ቅዱስ ጠቅሷል፡፡ ይህም ምንአልባት በመንገድ የሚያገኘው ሰው የሚኖር ከሆነ ወንዶችንም ሆነ ሴቶችን እያሰረ ወደ ኢየሩሳሌም ለማምጣት በደማስቆ ያሉ ምኵራቦች እንዲፈቅዱለት ለማድረግ ነው፡፡ በደማስቆ ከተማ ሲደርስም በድንገት መብረቅ ከሰማይ ብልጭ ሲልበት መሬት ላይ ወደቀ፤ ወዲያውም ‹‹ሳውል፥ ሳውል፥ ለምን ታሳድደኛለህ?›› የሚል ድምጽ ሰማ፤ ሳውልም ‹‹አቤቱ፥ አንተ ማነህ›› አለው፤ እርሱም አንተ የምታሳድደኝ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነኝ፤ በሾላ ብረት ላይ ብትቆም ለአንተ ይብስብሃል›› አለው፤ እርሱም እየፈራና እየተንቀጠቀጠ ‹‹አቤቱ፥ ምን እንዳደርግ ትሻለህ?›› አለው፤ ጌታም፥ ‹‹ተነሣና ወደ ከተማ ግባ፤ በዚያም ልታደርግ የሚገባህን ይነግሩሃል›› አለው፡፡ ሳውልም ከምድር ተነሥቶ በሚቆምበት ጊዜ ማየት ተሳነው፤ ዓይኖቹ ቢገለጡም የሚያየው ነገር ግን አልነበረም፡፡ ለሦስት ቀናት ያህል ሳይበላና ሳይጠጣ ከቆየ በኋላም ጌታ በራእይ ለደቀ መዝሙሩ ሐናንያ ተገልጦ ባዘዘው መሠረት እጁን ጭኖ ዓይኖቹን ፈወሰለት፤ ስለመመረጡ ነገርም አስረዳው፡፡ ‹‹በአሕዛብና በነገሥታት፥ በእስራኤል ልጆችም ፊት ይሸከም ዘንድ ለእኔ የተመረጠ ዕቃ አድርጌዋለሁና፡፡›› እንዲል፤ (የሐዋ.፱፥፬-፲፭)
ሳውልም ተጠመቀ፤ ከበላና ከጠጣ በኋላ ስለበረታ ወደ በደማስቆ ከደቀ መዝሙርቱ ጋር ሰንብቶ ምኵራቦቹ በመግባት ሰብኳል፡፡ ደማስቆም ከተመለሰ በኋላ አሕዛብን በማሳመን አጥምቋቸዋል፡፡ በዚህም ጊዜ በዚያ ይኖሩ የነበሩ አይሁድ ሊገድሉት በማሰባቸው ክርስቲያኖቹ እርሱን ለመደበቅ ወደ ኢየሩሳሌም ሰደዱት፡፡
እርሱም ማስተማሩን ሳያቋርጥ በአንጾኪያ ኤፌሶን ቆሮንቶስ ሮም ከተሞች እየተዘዋወረ የእግዚአብሔርን ቃል ሰብኳል፡፡ በተአምራት ሙት አስነሥቷል፤ ድውይ ፈውሷል፡፡ ትምህርቱንም የሚያደርገው የነበረው ሰው በተሰበሰበበት በምኵራብ፣ በዐደባባይ፣ በገባያ፣ በትያትር ቦታ፣ በደስታና በኀዘን ወቅት ነው፡፡ ጳውሎስ ተብሎ የተሰየመውም በቆጵሮስ ከተማዎች ባደገረው ጎዞ እንደነበር በቅዱሳት መጻሕፍት ተገልጷል፡፡
ቅዱስ ጳውሎስ በቃል ካስተማራቸው ትምህርቶችም ይልቅ በመልክእት መልክ በጽሑፍ ያስቀመጣቸው በመጽሐፍ ቅዱስ ተመዝግበው ለትውልድ ትውልድ ተላልፈዋል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም የተለያዩ የመከራን ተቀብሏል፡፡ ስለዚህም ሲገልጽ «በሁሉ መከራ ስንቀበል አንጨነቅም፤ እንናቃለን፤ አንዋረድም፤ እንሰደዳለን አንጣልም፤ እንጨነቃለን አንጠፋም» በማለት ነው፡፡ (፪ኛቆሮ. ፬፥፰-፲፩)
በ፷፭ ዓ.ም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም በኒቆጵልዮን ከተማ ሲያስተምር በነበረበት ወቅት ንጉሥ ኔሮን ይዞ ወደ ወኅኒ አስገብቶ ጽኑ ሥቃይን አሠቃየው፤ በ፸፬ ዓመት ዕድሜው በሮም ከተማ በኦስትያ መንገድ አንገቱን በሰይፍ ተቆረጦ ሐምሌ ፭ ቀን ሰማዕትነትን ተቀበለ፡፡
ቅዱሳኑ ሐዋርያት ጴጥሮስና ጳውሎስ የእግዚአብሔርን ቃል ለዓለም የሰበኩ፣ ብዙዎችን በክርስትና ጥምቀትና በገቢረ ተአምራት ያዳኑ የቤተ ክርስቲያን አዕማዶች ናቸው፡፡
አማላጅነታቸውና ተራዳኢነታቸው አይለየን፤ አሜን!
ምንጭ፡- ፹፩ መጽሐፍ ቅዱስ፣ መጽሐፈ ስንክሳር ዘወርኃ ሐምሌ ፭፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ቁጥር ፩
28 viewsኢዮብ ባለሀገሩ, 04:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 07:03:25 ሁለቱ የቤተ ክርስቲያን አዕማዶች
ሐምሌ ፬ ቀን ፳፻፲፬ ዓ.ም

+++ቅዱስ ጴጥሮስ
የዮና ልጅ ስምዖን የተባለው ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ የተወለደው በገሊላ ባሕር ዳር በምትገኘው በቤተ ሳይዳ ነው፡፡ ከወንድሙ ከእንድርያስ ጋርም ዓሣ ያሠግር ነበር፡፡ በዚህን ወቅት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ «በኋላዬ ኑና ሰዎችን አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ» በማለት ቅዱስ ጴጥሮስን ከወንድሙ ጋር ጠራው፡፡ (ማቴ.፬፥፲፰፣ ፩ኛቆሮ.፩፥፲፯፣ሐዋ.፳፪፥፫) በዚህ ጥሪ መሠረትም መተዳደሪያው የነበረውን መረቡንና ታንኳውን እንዲሁም አባቱን ትቶ ጌታውን ተከተለ፤ ዕድሜው ፶፭ ዓመት ነበር፡፡ (ዜና ሐዋርያት ገጽ ፫-፲፭)
በዕብራይስጥ ጴጥሮስ ‹ዐለት› ማለት ነው። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ «አንተ ጴጥሮስ ነህ፤ በዚህ ዐለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፤ የገሃነም ደጆችም አይችሏትም» በማለት ተናግሯል። (ማቴ.፲፮፥፲፰) ጌታም ይህን ክብር ለሐዋርያው የሰጠው ጴጥሮስ የእርሱን ወልድ እግዚአብሔር መሆን ስለመሠከረ ነው፡፡
ጴጥሮስ ጌታ ዐለት እንደሆነ ቢመሠክርለትም አስቀድሞ ግን እናቱ ባወጣችለት ስም ‹ስምዖን› ተብሎ የሚጠራ አሳ አስጋሪ ሰው እንደነበር ታሪኩ ይገልጻል፡፡ ጌታችን ከመረጠው በኋላ የአምላኩን ትእዛዝ በመጠበቅ ሲያገለግል ኖሯል፡፡ ቃሉንም (ወንጌልን) ማወቅም ብቻም ሳይሆን በገቢረ ተአምሩ ተመልክቷል፡፡ ይህንም በማቴዎስ ወንጌል እንዲህ ተጽፎ እናገኘዋለን፤ «ደቀ መዛሙርቱ በታንኳው ገብተው ወደ ባሕር ማዶ ቀድመውት ይሄዱ ዘንድ ግድ አላቸው፡፡ ከዚያም በኋላ ሕዝቡን አሰናብቶ ሊጸልይ ብቻውን ወደ ተራራ ወጣ፤ በመሸም ጊዜ ብቻውን በዚያው ነበር፡፡ ታንኳው ግን እነሆ፥ በባሕሩን መካከል ነበር፤ ከማዕበል የተነሣ ይታወክ ነበር፤ ነፋስ ከፊቱ ነበርና፡፡ ከሌሊቱም በአራተኛዪቱ ክፍለ ሰዓት ጌታችን ኢየሱስ በባሕር ላይ እየተራመደ ወደ እነርሱ መጣ፡፡ ደቀ መዛሙርቱም በባሕሩ ላይ ሲሄድ ባዩት ጊዜ ፈሩ፤ እነርሱም፣ «ምትሐት ነው!» ብለውም ደገነገጡ፤ ከፍርሃትም የተነሣ ጮኹ፡፡ ወዲያውም ኢየሱስም፥ «አይዞአችሁ፥ እኔ ነኝ አትፍሩ» አላቸው። ጴጥሮስም መልሶ «አቤቱ አንተስ ከሆንህ በውኃው ላይ ወደ አንተ እንድመጣ እዘዘኝ» አለው። እርሱም «ና» አለው። ጴጥሮስም ከታንኳው ወርዶ ወደ ጌታችን ኢየሱስ ሊደርስ በውኃው እየተራመደ ላይ ሄደ። ነገር ግን ነፋሱ በርትቶ ባየ ጊዜ ፈራ፤ ሊስጥምም ጀምረ፥ ያንጊዜም «አቤቱ፥ አድነኝ!» ብሎ ጮኸ። ወዲያውም ጌታችን ኢየሱስ እጁን ዘርግቶ ያዘውና «አንተ እምነት የጐደለህ ለምን ተጠራጠርህ?» አለው። ወደ ታንኳው በወጣ ጊዜ ወዲያው ነፋሱ ፀጥ አለ። በታንኳው ውስጥ የነበሩት ሁሉ «በእውነት አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ» እያሉ ሰገዱለት። ባሕሩንም ተሻግረው ወደ ጌንሴሬጥ ምድር ደረሱ። ወደ አውራጃዋዎቻቸውም ሁሉ ላኩ፤ በሽተኞችንም ሁሉ አመጡለት፡፡ የልብሱንም ዘርፍ ይዳስሱ ዘንድ ለመኑት፤ የዳሰሱትም ሁሉ ይድኑ ነበር።» (ማቴ.፲፬፥፳፪-፴፮) በማቴዎስ ወንጌል ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጴጥሮስን አማት ማዳኑን የተቀሰበት ምዕራፍ በመኖሩም ቅዱስ ጴጥሮስ ባለትዳር እንደነበር እንረዳለን፡፡ (ማቴ.፰፥፲፬-፲፭)
ቅዱስ ጴጥሮስ ጌታችን ኢየሱስ በደብረ ታቦር ምሥጢረ መለኮቱን ሲገልጥ፣ በኢያኤሮስ ቤት ልጁን ሲፈውስ እና በጌቴሴማኒ ጸሎት ሲያደርግ ከሐዋርያቱ ቅዱስ ዮሐንስና ቅዱስ ያዕቆብ ጋር አብሮ አልተለየም፡፡ ሆኖም ግን ጴጥሮስ ጌታችን ክዶ እንደነበር በመጽሐፍ ቅዱስ ተመዝግቧል። ይህንንም ጌታችን እራሱ አስቀድሞ ዐውቆ እንዲህ ብሎታል፤ «ነፍስህን ስለ እኔ አሳልፈህ ትሰጣለህን? እውነት እውነት እልሃለሁ ዶሮ ሳይጮህ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ፡፡» (ዮሐ.፲፫፥፴፰) ጌታችን ለሰዎች ሁሉ ድኅነት ሲል በመስቀል ይሰቀል ዘንድ በአይሁድ ተይዞ መከራ ሲቀበል እርሱን የሚያውቁትን ደግሞ እየለዩ በተመሳሳይ መልኩ ሊያሰቃዩአቸው በሞከሩ ጊዜ ጴጥሮስ ለጌታው ከመመሥከር ይልቅ ክዶታል፡፡ በሚክድበት ጊዜም ዶሮ ስትጮህ ሰምቶ ጌታችን የነገረውን ቃል በማስታወስ መሪር ልቅሶን አለቀሰ፤ ይህም እንደ ንስሓ ተቆጠረለት፡፡ (ማር.፲፬፥፷፰-፸፪)
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሙስና መቃብርን አጥፍቶና ሞትን ድል ነሥቶ በሦስተኛው ቀን ሲነሣ ለደቀ መዝሙሩ በተገለጠበት ጊዜ ጴጥሮስን «ትወደኛለህን?» ብሎ ጠይቆታል፤ ይህን ጥያቄ የጠየቀው ደጋግሞ ሦስት ጊዜ ነበር፤ እርሱም በመጨረሻ «አንተ ሁሉን ታውቃለህ፤ እኔም እንደምወድህ አንተ ታውቃለህ» ብሎ መልሶለታል። ጌታችንም ግልገሎቹን እንዲያሠማራ፣ ጠቦቶቹን እንዲጠብቅ፣ በጐቹን እንዲያሠማራ አደራ አለው። (ዮሐ. ፳፩፥፲፭-፲፯)
ጌታችን ካረገ በኋላም በአይሁድ ሸንጐ ድውይ ፈወስክ ተብሎ በተከሰሰ ጊዜ በድፍረት ስለ መድኃኔዓለም ክርስቶስ መሥክሯል፤ ወደ ፍልስጥኤም፣ ሶርያ፣ ጳንጦን፣ ገላትያ፣ ቀጰዶቅያ፣ ቢታንያ እና ሮሜም ሀገርም በመጋዝ አሕዛብን አስተማረ፤ ድውያንን ፈወሰ፤ (ሐዋ ፭፥፲፭)
ለአንድ ዓመት ያህልም ከቅዱስ ጳውሎስ ጋር ካስተማረ በኋላ ዝናው በሮማ ባለሥልጣናት ዘንድ ተሰማ ደረሰ። የኔሮን ባለሥልጣናት የሆኑት የአልቢኖስና የአግሪጳ ሚስቶች ክርስትናን በመቀበላቸው ኔሮን ንጉሠ ሮማ ቀንቶ አሳዳጊ መምህሩን ሁለቱንም ሚስቶቹን አግታሺያንና ፓፒያን በርግጫ ገደላቸው። የሮማን ከተማ ደግሞ በእሳት አቃጠላት።
ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ከሮማ ወደ ኦፒየም ጎዳና ተጓዘ፤ በዚያም ጌታችን በሽማግሌ አምሳል ተገለጠለት፤ ሆኖም ግን ጴጥሮስ ጌታ እንደሆነ ዐውቆ በፊቱ ተደፋና «ጌታዬ ወዴት እየተጓዝክ ነው?» አለና ጠየቀው። «ዳግም በሮም ልሰቀል» አለው። ቅዱስ ጴጥሮስም ይህን ሲሰማ እጅግ አዝኖ ወደ ሮማ ተመለሰ። ሲፈልጉት ወደ ነበሩት የኔሮን ወታደሮች ሄዶ «እነሆኝ ስቀሉኝ» አላቸው፤ ቅዱስ ጴጥሮስንም ይዘው ካሠሩት በኋላ ሊቅሉት የመስቀያውን እንጨት ሲያቀርቡ «እኔ እንደ ጌታዬ ልሰቀል አይገባኝም» በማለት ቁልቁል እንዲሰቅሉት ለመናቸው። እነርሱም ቁልቁል ሰቀሉት ይህም የሆነው ሐምሌ ፭ ቀን ፷፯ ዓ.ም. ነበር፡፡
...
25 viewsኢዮብ ባለሀገሩ, 04:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 07:36:21 ቅዱስ ጴጥሮስ በባልና በሚስት መካከል ሊኖር ስለሚገባው መልካም ግንኙነትና መተሳሰብ ሲያስረዳ ሣራ፣ አብርሃምን ትታዘዘው፤ ‹‹ጌታዬ›› ትለው እንደ ነበረው፤ በበጐ ሥራ ፍጹማን የኾኑ ልጆችን ይወልዱ ዘንድ ወንዶች ሚስቶቻቸውን እንዲያከብሩ ይመክራል፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያትም በዲድስቅልያ “አእምራ አንስት ከመ ብእሲት እንተ ታፈቅር ምታ ትረክብ ክብረ በኀበ እግዚአብሔር፤ ሴቶች ሆይ፥ ባሏን የምትወድ ሚስት በእግዚአብሔር ዘንድ ክብርን እንደምታገኝ ዕወቁ” በማለት በባልና በሚስት መካከል ሊኖር ስለሚገባው መከባበርና መተጋገዝ፤ እንደዚሁም መከባበር ስለሚያስገኘው ጸጋ አስተምረዋል (ዲድስቅልያ፣ አን. ፫፣ ቍ. ፳፭)፡፡ በተአምረ ማርያምም “ከእናንተ ወገን ሚስት ያለችው ሰው ቢኖር እንደ ዓይን ብሌን ይጠብቃት፤ እግዚአብሔር ያስጠበቀው አደራ ናትና” ተብሎ ተጽፏል (፲፩ኛ ተአምር፣  ቍ. ፳፮)፡፡
በጋብቻ ሕይወት ውስጥ ሊኖር ስለሚገባው መረዳዳት ቅዱሳት መጻሕፍት የሚናገሩትን ኃይለ ቃል ጠቅለል ስናደርገው ባልና ሚስት በመካከላቸው የራስ ወዳድነትና የትዕቢት መንፈስን በማስወገድ እንደ ዓይን ብሌን ሊጠባበቁ፣ ሊከባበሩና እርስበርስ ሊከባበሩ እንደሚገባቸው እንገነዘባለን፡፡ በየትኛውም ዓይነት ሕይወት ውስጥ መረዳዳት መኖሩ ተገቢ ነው፡፡ በጋብቻ ሕይወት ግን መረዳዳት ልዩ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡ ምክንያቱም ጋብቻ ሁለት ሰዎች በአንድ ጣሪያ ሥር በአንድነት የሚኖሩበት ሕይወት ከመኾኑም ባሻገር ኑሮንም ስሜትንም በጋራ የሚመሩበት የአንድነት ተቋም ነውና፡፡ ለዚህም ነው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የጋብቻን ሕይወት፣ ‹‹በቤት ውስጥ ያለች ትንሿ ቤተ ክርስቲያን›› በማለት የሚገልጸው፡፡
ይቆየን
45 viewsኢዮብ ባለሀገሩ, 04:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 07:36:21 የጋብቻ ሕይወት እና የሩካቤ ሥርዓት – ክፍል ፫

በዲያቆን ኤፍሬም የኔሰው

ሚያዝያ ፲፫ ቀን ፳፻፲ ዓ.ም
፩.፩ የጋብቻ ክቡርነት እና ምሥጢር
እግዚአብሔር አምላካችን በብሉይ ኪዳን የአዳምንና የሔዋንን፤ የሌሎችንም አባቶች እና እናቶች ጋብቻ ባርኳል፡፡ በሐዲስ ኪዳንም በዶኪማስ ቤት ተገኝቶ፣ ውኃውን ወደ ወይን ቀይሮ ቤቱን በበረከት ሞልቶለታል፡፡ ይህም ጋብቻ በእግዚአብሔር ዘንድ የተወደደና የከበረ ምሥጢር መኾኑን አመላካች ነው፡፡ ምክንያቱም አምላካችን ያልፈቀደዉን ሕይወት ባርኮ አይሰጥምና ነው፡፡ ጌታችን አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ባልና ሚስት አንድ ሥጋ ናቸው እንጂ ሁለት አይደሉም፡፡ እግዚአብሔር ያጣመረውን እንግዲህ ሰው አይለየው” በማለት ማስተማሩም ጋብቻ የአንድነት ውጤትና ታላቅ ሥርዓት መኾኑን ያስረዳል (ማቴ. ፲፱፥፮፤ ዮሐ. ፪፥፩-፲፩)፡፡
በዚህም ሥርዓት በብሉይ ኪዳን፡- አዳምና ሔዋን፣ አብርሃምና ሣራ፣ ይስሐቅና ርብቃ፣ ያዕቆብና ራሔልን የመሰሉ፤ በሐዲስ ኪዳን፡- ኢያቄምና ሐና (የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ወላጆች)፣ ጸጋ ዘአብና እግዚእ ኀረያ (የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ወላ ጆች)፣ ኖኅና ታቦትን (የቅዱስ መርቆሬዎስ ወላጆች) የመሰሉ ደጋግ አባቶች ልጆችን አፍርተውበታል፤ ተጠቅመውበታልም፡፡ ለዚህም ነው “ጋብቻ በዂሉ ዘንድ ክቡር ነው፤ ለመኝታቸውም ርኵሰት የለበትም” ተብሎ የተነገረው (ዕብ. ፲፫፥፬)፡፡ በሥርዓት ከኖሩበት የሚያስከብር ሕይወት ነውና፡፡
ቅዱስ ኤፍሬም በውዳሴ ማርያም ድርሰቱ “… ማርያም ድንግል ከብካብ ንጹሕ ወመርዓ ቅዱስ፤ ድንግል ማርያም ሙሽራዋ ንጹሕ የኾነ የሰርግ ቤት ናት፤” በማለት እመቤታችንን አመስግኗታል፡፡ ሊቁ እመቤታችንን በሰርግ ቤት መመሰሉ ጋብቻ ንጹሕ ሥርዓት መኾኑን የሚያመለክት ነው፡፡ ይህም ምሥጢራዊ ትርጕም አለው፤ በሰርግ ቤት ደስታ፣ ጨዋታ፣ መብልና መጠጥ፣ የሙሽራውና የሙሽሪት አንድነት ይከናወንበታል፤ የሙሽራውና የሙሽሪት ዘመዶች አንድ ይኾኑበታል፡፡ መብልና መጠጡ የትምህርተ ወንጌል (የሥጋ ወደሙ)፤ ደስታና ጨዋታው የተአምራት፤ የሙሽራውና የሙሽሪት ተዋሕዶ የትስብእትና የመለኮት አንድነት ምሳሌዎች ናቸው፡፡ በሰርግ የሙሽራውና የሙሽሪት ዘመዶች አንድ እንደሚኾኑባት ዂሉ፣ በድንግል ማርያምም ሰውና መላእክት፣ ሰውና እግዚአብሔር፣ ነፍስና ሥጋ፣ ሕዝብና አሕዛብ አንድ ኾነውባታል፡፡ ስለዚህም ቅዱስ ኤፍሬም እመቤታችንን ‹‹ሙሽራዋ ንጹሕ የሚኾን የሰርግ ቤት›› ይላታል (የረቡዕ ውዳሴ ማርያም፣ አንድምታ ትርጓሜ)፡፡
ቅዱስ ኤፍሬም ዳግመኛም “ከመ ከብካብ ዘአልቦ ጥልቀት መንፈስ ቅዱስ ኀደረ ላዕሌኪ፤ እንደ ሰርግ ቤት አደፍ፣ ጉድፍ የሌለብሽ ኾነሽ ቢያገኝሽ መንፈስ ቅዱስ አድሮብሻል” በማለት እመቤታችንን ጋብቻ በሚፈጸምበት ንጹሕ የሰርግ ቤት መስሎ አመስግኗታል፡፡ ይህም በተመሳሳይ መልኩ የጋብቻን ክቡርነት የሚያመለክት ነው (ውዳሴ ዘቀዳሚት)፡፡ ለዚህም ነው ቅዱስ ጳውሎስ “ይህ ምሥጢር ታላቅ ነው፤ እኔ ግን ይህን ስለ ክርስቶስና ስለ ቤተ ክርስቲያን እላለሁ” በማለት ጋብቻ የክርስቶስና የቤተ ክርስቲያን ተዋሕዶ ምሳሌ መኾኑን ያመሠጠረልን (ኤፌ. ፭፥፴፪)፡፡ በአጠቃላይ ጋብቻ፣ ይከብርበትና በጋራ ይኖርበት ዘንድ እንደዚሁም ራሱን ከኃጢአት ይጠብቅበት ዘንድ እግዚአብሔር አምላክ ለሰው ልጅ ያዘጋጀው መንፈሳዊ ሥርዓት ነው፡፡
፩.፪ የጋብቻ አስፈላጊነትና ዓላማዎቹ
ሰው ኾነን የመፈጠራችን ዓላማው የእግዚአብሔርን ስም ለመቀደስ (ለማመስገን)፣ ክብሩን (መንግሥቱን) ለመውረስ እንደ ኾነው ዂሉ ጋብቻንም አምላካችን በዓላማ አዘጋጅቶልናል፡፡ የጋብቻ አስፈላጊነቱ ወይም ዓላማው እጅግ የጎላ ነው፡፡ በሕገ ቤተ ክርስቲያን እንደ ተገለጸው ጋብቻን የሚያሹ (የሚያስፈልጉ) ፈቃዳት ሦስት ናቸው፤ እሊህም ጠቢብ፣ ልዑል ከኾነው ከእግዚአብሔር የተሰጡ፤ እንደዚሁም ከአብርሃም፣ ይስሐቅ፣ ያዕቆብ የተወረሱ ግብራት ናቸው፡፡ ከሦስቱ ዓላማዎች የተለየ የጋብቻ ጥቅም (አስፈላጊነት) አይኖርም፡፡ መምህራነ ቤተ ክርስቲያን “ከነቢያት ከሐዋርያት አንዱ ስንኳ ‹ጋብቻ ለዝሙት ትኹን› ብሎ ያስተማረ የለም፡፡ ልጅ ለመውለድ ብቻ ነው እንጂ” በማለት የጋብቻን ዓላማዎች ያስረዳሉ (ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ ፳፬፣ ቍ. ፷)፡፡ ቅዱሳት መጻሕፍትን መሠረት በማድረግ ጠቅለል አድርገን ስንመለከተው ጋብቻ የሚከተሉት ሦስት መሠረታውያን ዓላማዎች አሉት፤
ሀ. መረዳዳት
ከጋብቻ ዓላማዎች አንደኛው እርስበርስ መረዳዳት ነው፡፡ መረዳዳት ማለት መተጋገዝ፣ መተሳሰብ፣ መደጋገፍ፣ መጠያየቅ፣ ለራሳችን ሊደረግልን የምንፈልገውን መልካም ነገር ዂሉ ለሌሎችም ማድረግ ማለት ነው፡፡ ጋብቻ ሁለት ጥንዶች በአንድነት የሚኖሩበትና እርስበርስ የሚረዳዱበት ሕይወት ነው፡፡ በጋብቻ ውስጥ የሚደረግ መረዳዳት በማኅ በራዊ፣ በሥነ ልቡና፣ በምጣኔ ሀብትና በቤተሰብ አስተዳደር መተጋገዝን፣ መተሳሰብን፣ በአንተ ይብስ፤ በአንቺ ይብስ መባባልን እንደዚሁም በስሜት መተዋወቅን ያጠቃልላል፡፡
በጋብቻ ሊኖር ስለሚገባው የመረዳዳት ዓላማ መነሻው “ሰው ብቻውን ይኾን ዘንድ መልካም አይደለም፤ የሚመቸውን ረዳት እንፍጠርለት” የሚለው አምላካዊ ቃል ነው (ዘፍ. ፪፥፲፰)፡፡ ስለዚህም በተቻላቸው አቅም ዂሉ ባል ለሚስቱ የሚገባትን፣ ሚስትም ለባሏ የሚገባውን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ጋብቻ የአንድነት ሕይወት በመኾኑ ሚስት በራሷ፣ ባልም በራሱ ሥልጣን እንደሌላቸው ቅዱስ ጳውሎስ ይናገራል፡፡ አንዳቸው በአንዳቸው ላይ ማዘዝ እንደሚችሉም ያስረዳል፡፡ ምክንያቱም ሁለቱም አንድ አካል ናቸውና (፩ኛ ቆሮ. ፯፥፴፬)፡፡ በመኾኑም ባልና ሚስት እንደ ዓይን ብሌን ሊጠባበቁ፣ ሊከባበሩና አንዳቸው ለአንዳቸው ሊታዘዙ ይገባቸዋል፡፡ መረዳዳት ማለት አንዱ የሌላውን ስሜት መጠበቅ ነውና፡፡
ቅዱስ ጴጥሮስም በጋብቻ ሕይወት ውስጥ መኖር ስለሚገባው የመደጋገፍና የመረዳዳት ዓላማ ሲያስረዳ “እናንተ ባሎች ሆይ፥ ደካማ ፍጥረት ስለ ኾኑ ከሚስቶቻችሁ ጋር በማስተዋል አብራችሁ ኑሩ፤ ጸሎታችሁ እንዳይከለከል አብረው ደግሞ የሕይወትን ጸጋ እንደሚወርሱ አድርጋችሁ አክብሩአቸው፡፡ በመጨረሻው ሁላችሁ በአንድ ልብ ሁኑ፤ የሌላው መከራ ለእናንተ እንደሚሆን አድርጉ፤ እንደ ወንድሞች ተዋደዱ፤ ርኅሩኆችና ትሑታን ኹኑ፡፡ ክፉን በክፉ ፈንታ ወይም ስድብን በስድብ ፈንታ አትመልሱ፤ በዚህ ፈንታ ባርኩ እንጂ፡፡ በረከትን ልትወርሱ ለዚህ ተጠርታች ኋልና” ሲል በአጽንዖት አስተምሯል (፩ኛ ጴጥ. ፫፥፩-፱)፡፡
በዚህ ኃይለ ቃል ውስጥ ‹‹ደካማ ፍጥረት ስለ ኾኑ›› የሚለው ሐረግ ሴቶች በዕውቀት ወይም በዓቅም ዝቅተኛ ናቸው ለማለት አይደለም፡፡ በትዳር አጋሮቻቸው በሚደርስባቸው ጫና፣ ከውጪ በሚገጥማቸው ልዩ ልዩ ፈተና በቀላሉ የሚሰናከሉ መኾናቸዉን የመሚጠቁም ነው እንጂ፡፡ ለዚህም ማስረጃ የሚኾነን የሔዋን ጠባይዕ ነው፡፡ አዳምና ሔዋን በገነት በነበሩበት ወቅት የሰይጣን የማሰሳሳት ጥረት የተሳካው በሔዋን የመታለል ጠባይዕ ነበር፡፡ የሔዋን ውዳሴ ከንቱ (የማይጠቅም ምስጋና) የመውደድና በቀላሉ የመሸነፍ ስሜት አሁንም ድረስ በሴቶች ላይ ይስተዋላል፡፡ ሐዋርያው ድክመት ያለውም ይህንን ዓይነት የሴቶችን ጠባይዕ ነው እንጂ በተፈጥሮማ ሴቶችም በሥላሴ አርአያና አምሳል ነው የተፈጠሩት፡፡
43 viewsኢዮብ ባለሀገሩ, 04:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 09:36:04 አዳምም ከእንቅልፉ ሲነቃ ከጎኑ ሔዋንን በአገኘ ጊዜ “ይህቺ አጥንት የአጥንቴ ፍላጭ፣ ይህቺ ሥጋ የሥጋዬ ቁራጭ ናትና፤ ከኔ ከባሏ ተገኝታለችና ሚስት ትኹነኝ” በማለት ለሚስትነት እንደ ተሰጠችው አረጋግጦ ተናግሯል፡፡ ስለዚህም ወንድ አባትና እናቱን ትቶ ሚስቱን ተከትሎ ይሔዳል፡፡ ቈላ ብትወርድ፣ ደጋ ብትወጣ አብሯት ይወርዳል፤ ይወጣል፡፡ አንድ ክብር በመውረስና በመልበስ፤ እንደዚሁም በግብር (በሩካቤ ሥጋ) ሁለቱም አንድ አካል ይኾናሉ፡፡ ወንድ ቢወለድ ‹‹ያንተ ነው፤›› ሴት ብትወለድ ‹‹ያንቺ ናት›› አይባባሉምና፡፡ ዳግመኛም ሁለት ኾነው አንድ ልጅ ያስገኛሉና፤ እንደዚሁም ከእናት ደም፣ ከአባት ዘር ተከፍሎ አንድ ሰው እንዲወለድ ምክንያት ናቸውና እግዚአብሔር ‹‹አንድ አካል ይኾናሉ›› አለ (ዘፍ. ፩፥፳፰፤ ፪፥፳-፳፬)፡፡
ይቆየን
61 viewsኢዮብ ባለሀገሩ, 06:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 09:36:03 የጋብቻ ሕይወት እና የሩካቤ ሥርዓት – ክፍል ፪

በዲያቆን ኤፍሬም የኔሰው

ሚያዝያ ፲፪ ቀን ፳፻፲ ዓ.ም
ቅዱስ ጳውሎስ ጋብቻ የፈቃድ ሕግ መኾኑን ሲያስተምር ራሳቸውን መጠበቅ ለሚችሉ አለማግባት ቢቻልም ሰውነትን ለመጠበቅ ከአልተቻለ ግን ማግባት እንደሚሻል አስገንዝቧል፡፡ ሐዋርያው እንዳስተማረው ከሴት ጋር አለመገናኘት (ጋብቻ አለመምሥረት) ለሰው መልካም ነው፡፡ ነገር ግን ስለ ዝሙት ጠንቅ ለእያንዳንዱ ወንድ አንድ ሚስት ሊኖረው፤ ለእያንዳንዲቱ ሴት ደግሞ አንድ ባል ሊኖራት ይገባል፡፡ ነገር ግን ሰው ዂሉ እግዚአብሔር እንዳደለው (እንደ ፈቀደለት) ይኑር፡፡
ላላገቡና ለመበለቶች ደግሞ የሚከተለዉን ትምህርት ሰጥቷል፤ “ላላገቡና ለመበለቶች ግን እላለሁ፤ እንደ እኔ ቢኖሩ ለእነርሱ መልካም ነው፡፡ ነገር ግን ራሳቸውን መግዛት ባይችሉ ያግቡ፤ በምኞት ከመቃጠል መጋባት ይሻላልና፡፡” ይኸውም “ሚስት የሌላቸው ወንዶች፣ ባል የሌላቸው ሴቶች እንደ እኔ ከሴት (ከወንድ) ርቆ፣ ንጽሕ ጠብቆ መኖር ይሻላቸዋል፡፡ ንጽሕ ጠብቆ፣ ከሴት (ከወንድ) ርቆ መኖር ባይቻላቸው አግብተው ይኑሩ፡፡ አንዲት ሴት (ባል) አግብታችሁ፣ በሕግ ተወስናችሁ ኑሩ ማለቴ ንጽሕ ጠብቆ፣ ከሴት ርቆ መኖር ለማይቻላቸው ሰዎች ነው፡፡ ‹እንደ እኔ ንጽሕ ጠብቃችሁ፣ ከሴት ርቃችሁ ኑሩ› ብዬ አላስገድዳችሁም፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር እንዳደላችሁ ኑሩ፤” ማለቱ ነው (፩ኛ ቆሮ. ፯፥፩-፱፣ አንድምታ ትርጓሜ)፡፡
ሐዋርያው፣ ቈነጃጅት ባል አግብተው፣ ልጆች ወልደው፣ ቤት፣ ንብረት ይዘው ቢኖሩ መልካም መኾኑን ጠቁሟል፡፡ በተጨማሪም ሳይናወጥ በልቡ የጸና ግን የማግባት ግዴታ እንደደሌለበትና የወደደውን ማድረግ እንደ ተፈቀደለት ማለትም ድንግልናውን ጠብቆ መኖር ከፈለገ በምንኵስና፤ ማግባት ከፈለገም በጋብቻ ሕይወት ጸንቶ መኖር እንደሚችል አስረድቷል፡፡ ትምህርቱም ወንዶችን ብቻ ሳይኾን ሴቶችንም የሚመለከት ነው (፩ኛ ቆሮ. ፯፥፴፯-፴፰)፡፡ ይህም ጋብቻ የፈቃድ እንጂ የግዴታ ሕግ አለመኾኑን ያመለክታል፡፡
ከትምህርቱ እንደምንረዳው ጋብቻ በሰው ፍላጎት ብቻ ሳይኾን በእግዚአሔር ፈቃድና ዕቅድ የተመሠረተ መንፈሳዊ ሥርዓት ነው፡፡ ሕይወቱ ከምድራዊ አንድነት ባሻገር ለምሥጢረ ተዋሕዶም ምሳሌ ኾኖ ይጠቀሳል፡፡ “ዐቢይ ውእቱ ዝ ነገር አንሰ እብሎ ላዕለ ክርስቶስ ወላዕለ ቤተ ክርስቲያኑ፤ ይህም ምሥጢር ታላቅ ነው፤ እኔም ይህንኑ ስለ ክርስቶስና ስለ ቤተ ክርስቲያኑ እናገረዋለሁ፤” እንዳለ ቅዱስ ጳውሎስ (ኤፌ. ፭፥፴፪)፡፡
የጋብቻ ክቡርነትና ምሥጢር ይህ ኾኖ ሳለ አንዳንዶቻችን ለጋብቻ የምንሰጠው ትርጕም ግን ዝቅ ያለ ይመስላል፡፡ በስውር ከጋብቻ ውጪ ፈቃዳቸዉን የሚፈጽሙ ምእመናን መኖራቸውም ከዚህ አመለካከት የመነጨ ነው፡፡ ከዚህ የተሳሳተ ግንዛቤ በመውጣትና ንጽሕናን በመጠበቅ አንድም ጋብቻ መመሥረት፤ ካለዚያም ራስን ጠብቆ በድንግልና ጸንቶ መኖር ከክርስቲያኖች የሚጠበቅ ግዴታ ነው፡፡ ስለ ጋብቻ ሕይወት ሲነገር ከጋብቻ ዓላማዎች አንደኛው ከዝሙት ጠንቅ ለመሸሽ ነው፡፡ ይህም በሕጋዊ ሥርዓት ሩካቤ ሥጋን ለመፈጸም ያስችላል፡፡
ሩካቤ ሥጋ የተለየ ዓላማና ምሥጢር አለው፡፡ አፈጻጸሙም በሥርዓተ ተክሊል ወይም በሥርዓተ ቍርባን ይጸናል፡፡ በሕጋዊ ጋብቻ ተወስነን ካልኾነ በቀር ከጋብቻ በፊትም ኾነ በኋላ ካገኘነው ዂሉ ጋር ፆታዊ ግንኙነት መፈጸም ክቡራን ኾነን ተፈጥረን ሳለ በግብራችን ግን ከእንስሳት ጋር እንድንመሳሰል ያደርገናል፡፡ ቅዱስ ዳዊት “ሰብእሰ እንዘ ክቡር ውእቱ ኢያእመረ ወኮነ ከመ እንስሳ ዘአልቦ ልብ ወተመሰሎሙ፤ ሰውስ ክቡር ኾኖ ሳለ አላወቀም፤ ልብ እንደሌላቸው እንስሳትም መሰለ” በማለት እንደ ተናገረው (መዝ. ፵፰፥፲፪)፡፡
በዓለማችን ላይ እንደምንሰማውና እንደምናስተውለው የሰው ልጅ ራሱን ከሚጥልባቸው መንገዶች አንደኛው ዝሙት ነው፡፡ ለዚህም ነው በተለያዩ የዓለም ክፍሎች አስጸያፊ ፆታዊ ድርጊቶች ማለትም ከአንድ በላይ የትዳር አጋር መያዝ፣ ሴት አዳሪነት ብሎም የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ ምእመናንን ሳይቀር እየተፈታተነ የሚገኘው፡፡ ይህም በሰው ልጆች ዘንድ የመንፈስ ዝለትና የዝሙት ስሜትን የመቈጣጠር ስንፍናን አመላካች ነው፡፡ ከእንደዚህ ዓይነት አጸያፊ የዝሙት ሥራ ራሳችንን እንድንጠብቅ ለማስጠንቀቅ፣ ጋብቻችንንም በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ብቻ እንድንፈጽም ለመጠቆም እንደዚሁም ሩካቤ ሥጋ በሥርዓትና በሕግ እንደሚፈጸም ለማስገንዘብ ‹‹የጋብቻ ሕይወት እና የሩካቤ ሥርዓት›› በሚል ርእስ ይህን ትምህርት አዘጋጅተናል፡፡ በድጋሜ መልካም ንባብ!

//፩. የጋብቻ ምንነትና አመሠራረት//

ከቃሉ ትርጓሜ ስንጀምር ጋብቻ፡- መጣመር፣ መዋሐድ (አንድ መኾን)፣ በአንድ ጎጆ ውስጥ መኖር ማለት ነው፡፡ ቃሉ፣ የትዳር ሕይወትን ለመመሥረት የሚያስችል የሁለት ተቃራኒ ወይም ተፈላላጊ ፆታዎችን (ጥንዶችን) ዘላቂ ጥምረት (ግንኙነት) ያመለክታል፡፡ ‹ትዳር› የሚለው ቃልም ከጋብቻ ጋር በአቻነት ሊጠቀስ ይችላል፡፡ ይኸውም ባልና ሚስት በአንድ ጎጆ ጥላ ሥር የሚያከናውኑት ቤተሰብኣዊ ኑሮ ነው “በአንድ ልብ በእግዚአብሔር ቤት ተራመድን” በማለት ቅዱስ ዳዊት እንደ ተናገረው (መዝ. ፶፬፥፲፬)፡፡ ትዳር፣ ሁለቱም (ብልና ሚስት) በመስማማትና በመተሳሰብ በአንድነት መኖራቸውን ያመለክታል፡፡ ስለዚህ ጋብቻ ወይም ትዳር ማለት በሁለት የማይተዋወቁና ባዕድ ተቃራኒ ጥንዶች (ፆታ) የሚመሠርቱት የአንድነት ሕይወት ነው፡፡
አመሠራረቱን ስንመለከት ጋብቻ የተመሠረተው በእግዚአብሔር ፈቃድ፣ በአዳምና ሔዋን አማካይነት ነው፡፡ ከአዳም በፊት የተፈጠሩ አራዊት፣ እንስሳትና አዕዋፍ በዝተው፣ ተባዝተው ይኖሩ ዘንድ የተፈጠሩት ጥንድ ጥንድ (ሴትና ወንድ) ኾነው ነበር፡፡ ለአዳም ግን ገና ሔዋን አልተሰጠችውም ነበር፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ለአራዊት፣ ለእንስሳትና ለአዕዋፍ ስም ያወጣላቸው ዘንድ ወደ አዳም በላካቸው ጊዜ እንስሳቱ ተባዕትና አንስት ኾነው መፈጠራቸዉን አዳም ተመልክቶ “ከእኔ በቀር ብቻውን የተፈጠረ የለም” ብሎ ማዘኑን የቤተ ክርስቲያን መተርጕማን ይናገራሉ፡፡ በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር አምላካችን፣ “ኢኮነ ሠናየ ለእጓለ እመሕያው ይንበር ባሕቲቶ፤ አላ ንግበር ሎቱ ቢጸ ዘትረድኦ፤ ሰው ብቻውን ይኖር ዘንድ መልካም አይደለም፤ የምትረዳውን ጓደኛ እንፍጠርለት እንጂ” አለ፡፡
ከዚህ በኋላ አዳም እንዲያንቀላፋ አደረገ፡፡ ከጎኑም አንድ አጥንት ነሥቶ (ወስዶ)፣ መልክ ከደም ግባት አስተባብራ የያዘችና ውብ አድርጎ፤ ዓይን፣ አፍንጫ፣ እጅ፣ እግር አውጥቶ፤ የሴት አካል ሰጥቶ ሔዋንን ፈጠረለት፡፡ ሔዋን ከአዳም ጎድን መፈጠሯም ባልና ሚስት ተከባብረው፣ ተቻችለውና ተመካክረው በእኩልነት እንዲኖሩ የሚያመለክት ምሥጢር አለው፡፡ ከዚህ ላይ የእግዚአብሔር ዓላማ ሴትንና ወንድን ማበላለጥ አለመኾኑን ልብ ማለት ያስፈልጋል፡፡ እንደዚያ ቢኾን ኖሮ ሔዋንን አንድም ዝቅ ብሎ ከአዳም እግር፤ አንድም ከፍ ብሎ ከራሱ ሊፈጥራት ይችል እንደ ነበር መረዳት ያስፈልጋል፡፡ ሔዋን ከአዳም ጎን መፈጠሯ ባልና ሚስት እርስበርስ በመተጋገዝ፣ በመተሳሰብና በመደጋገፍ መኖር እንደሚገባቸው ያመላክታልና፡፡
58 viewsኢዮብ ባለሀገሩ, 06:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 11:21:37 የጋብቻ ሕይወት እና የሩካቤ ሥርዓት – ክፍል ፩

በዲያቆን ኤፍሬም የኔሰው
ሚያዝያ ፲፩ ቀን ፳፻፲ ዓ.ም
መግቢያ
በቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ ከዕለተ ትንሣኤ እስከ በዓለ ጰራቅሊጦስ ድረስ ያለው ጊዜ ‹በዓለ ኀምሳ› ይባላል፡፡ ይኸውም ጌታችን አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መከራ ተቀብሎ አዳምንና ልጆቹን ከሲኦል ነጻ ማውጣቱ፤ በሥልጣኑ ሞትን ድል አድርጎ መነሣቱ፤ ከትንሣኤው በኋላ በልዩ ልዩ መንገድ ለደቀ መዛሙርቱ መገለጡ፤ መጽሐፈ ኪዳንን ለሐዋርያት እያስተማረ፣ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን እያደረገ ዐርባ ቀን በምድር ቆይቶ ወደ ሰማይ ማረጉ፤ ባረገ በዐሥረኛው ቀን መንፈስ ቅዱስን ለሐዋርያት መላኩ፤ እንደዚሁም ዳግም ለፍርድ በግርማ የሚመጣ መኾኑ በስፋት የሚነገርበት ወቅት ነው፡፡ እኛ ኦርቶዶክሳውያን ምእመናን፣ እግዚአብሔር ያደረገልንን ውለታ በማሰብ ይህን ሰሙን በመንፈሳዊ ደስታ ልናከብረው እንደሚገባ የቤተ ክርስቲያን መምህራን ሥርዓት ሠርተውልናል፡፡
ከዚህ ላይ መደሰት ማለት ሥርዓት በሌለው መልኩ ከመጠን በላይ መብላት መጠጣት ማለት አለመኾኑን ማስተዋል ተገቢ ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ቸርነት እያሰቡ በመጠን እየተመገቡ፣ ነዳያንንም እያሰቡ፣ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን እየተቀበሉ መደሰት የክርስትና መገለጫ ነው፡፡ በዚህ ወቅት እያንዳንዱ ምእመን ሊጠብቀው የሚገባም ይህንኑ ሥርዓት ነው፡፡ ወቅቱ የደስታና የነጻነት ማለትም በክርስቶስ ቤዛነት የሰው ልጆች (ምእመናን) ከሰይጣን ባርነት ነጻ መውጣታችንን የምናስብበት ወቅት ነውና በዘመነ መርዓዊ እንደሚደረገው ዂሉ በዚህ ሰሙን በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ጋብቻ የሚፈጽሙ ምእመናን በርካቶች ናቸው፡፡ ዕቅዱ ላላቸውና ለተፈቀደላቸው ሰዎች ጋብቻ ከብቸኝነት ኑሮ ነጻ የሚወጡበት፣ የዝሙት ፆርን የሚከላከሉበት ሕይወት በመኾኑ በዚህ በነጻነት ወቅት (በበዓለ ኀምሳ) ይፈጸማል፡፡
ቅዱስ ጳውሎስ የጋብቻን ታላቅነትና ልዩ ምሥጢር ባስተማረበት መልእክቱ “ይህም ምሥጢር ታላቅ ነው፤ እኔም ይህንኑ ስለ ክርስቶስና ስለ ቤተ ክርስቲያኑ እናገረዋለሁ፤” በማለት የባልና የሚስት ጥምረት ወይም አንድነት የክርስቶስና የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ መኾኑን ይናገራል (ኤፌ. ፭፥፴፪)፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ጋብቻ የመለኮት እና የትስብእት (የሰውነት) ምሳሌ መኾኑን መምህራነ ቤተ ክርስቲያን ያስተምራሉ፡፡ በዓለ ኀምሳ፣ ቤተ ክርስቲያንን በደሙ የመሠረታት የመድኀኒታችን ክርስቶስ ትንሣኤ የሚታሰብበት፣ ምሥጢረ ሥጋዌና ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን በስፋት የሚሰበክበት ወቅት ከመኾኑ አኳያ በእርግጥም በዚህ የደስታ ሰሙን የተዋሕዶ ምሳሌ የኾነውን ጋብቻን በቤተ ክርስቲያን መፈጸም ለምሥጢር የተመቸ መልእክት አለው፡፡
የዛሬዉን ትምህርታዊ ጽሑፍ በጋብቻ ዙርያ ያደረግነው ወቅቱን ለመዋጀት በማሰብ ነው፡፡ በእርግጥ ስለ ጋብቻ በልዩ ልዩ መንገድ ብዙ ጊዜ ተምረናል፡፡ ኾኖም ጉዳዩ የሕይወት ጉዳይ ነውና ደጋግመን መማማሩ ይጠቅመናል፡፡ አንዳዶቹ በማወቅም፣ ባለማወቅም ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ውጪ ጋብቻቸውን ሲፈጽሙ ይስተዋላል፡፡ ስለ ጋብቻ በተደጋጋሚ መማማራችንም በማወቅ ወይም በግድየለሽነት ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ውጪ ትዳር የሚመሠርቱ ምእመናንን ለመመለስና ሌሎችም እንዳይስቱ ለመጠቆም ይረዳናል፡፡ ስለዚህም በዚህ ዝግጅት ስለ ጋብቻ አመሠራረት፣ ክቡርነት፣ ምሥጢር እና ዓላማ የሚያትት ተከታታይ ትምህርት ይዘን ቀርበናል፡፡ ትምህርቱን ትከታተሉ ዘንድ መንፈሳዊ ግብዣችንን እናስቀድማለን፡፡

//መቅድም//

የሰው ልጅ ወደዚህ ዓለም ከመጣ በኋላ ራሱን እስከሚችል ድረስ ሕይወቱ በእናት በአባቱ እጅ የተወሰነ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ የወደፊት የኑሮ ዕጣውም በወላጆቹ አኗኗር ላይ የተመሠረተ ሊኾን ይችላል፡፡ በየትኛውም ዓይነት የአስተዳደግ ሥርዓት ብናልፍም ግን ዕድሜያችን እየገፋ ሲሔድ ራሳችንን መፈለግ እንጀምራለን፡፡ አንዳዶቻችን ጳጳስ፣ ቄስ፣ ዲያቆን፣ ሰባኪ፣ ዘማሪ፣ ወዘተ፤ ሌሎቻችን የአገር መሪ፣ አውሮላን አብራሪ፣ ተመራማሪ፣ ደራሲ፣ አርሶ አደር ወይም የተለየ ሰው የመሆን ርዕይ ሊኖረን ይችላል፡፡ ምንም ዓይነት ርዕይ የሌለን ሰዎችም ልንኖር እንችላለን፡፡ እግዚአብሔር አምላክም ልንሸከመውና ልንወጣው በምንችልበት የኑሮ መስክ ያሰማራናል፡፡
በርዕይ ወይም ያለ ርዕይ ከአገኘነው ሥራ ወይም መዓርግ ባለፈ ሁለት ፈቃዳት ያስፈልጉናል፡፡ አንድም በድንግልና መኖር፤ አንድም በትዳር መወሰን፡፡ ሦስተኛው ግብር ግን ሰይጣናዊ ሲኾን፣ ይኸውም ዘማዊነት ነው፡፡ “ኦ ዘትቤ ንግበር ሎቱ፡፡ ለዕጓለ እመሕያው ቢጸ ከመ ኢይንበር ባሕቲቱ፡፡ እግዚአብሔር መጋቢ ወሠራዔ ዓለም በበሥርዓቱ፡፡ ሥርዐኒ ኀበ ፈቃድከ እምፆታ ፈቃዳት ክልኤቱ፡፡ ሣልሳዊሰ ግብር እምሰይጣን ውእቱ፤ ‹የሰው ልጅ (አዳም) ብቻውን ይኖር ዘንድ መልካም አይደለም› በማለት የተናገርህ፤ ዓለምን በየሥርዓቱ ፈጥረህ የምትመግበው (የምታኖረው) እግዚአብሔር ሆይ፣ ከሁለቱ ፈቃዶች ውስጥ አንተ ወደ ወደድኸው ፈቃድ ምራኝ፡፡ ሦስተኛው ግብር (ሥራ) ግን ከሰይጣን የመጣ ነው፤” እንዳለ ደራሲ (ጠቢበ ጠቢባን)፡፡
ከሦስተኛው ፈቃድ ነጻ በመውጣት በምንኵስና ወይም በጋብቻ ለመኖርም ዋነኛውና መሠረታዊው ጉዳይ የእግዚአብሔር ፈቃድ ቢኾንም ከእርሱ ቀጥሎ የእያንዳንዳችን ፈቃድም ወሳኝነት አለው፡፡ ለመመንኰስም ትዳር ለመመሥረትም የሰውነታችንን ፈቃድ በትክክል መረዳት ይኖርብናልና፡፡ እንኳን ከገቡ ለማይወጡበት ለምንኵስና ሕይወት በልዩ ልዩ ምክንያት ሊቋረጥ ለሚችለው ለጋብቻ እንኳን ፈቃደኝነት ያስፈልጋል፡፡ የሁለቱ ጥንዶች የጋራ ስምምነት ደግሞ ሌላው ሊታሰብበት የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡ ሁለቱ ተጋቢዎች ሳይስማሙ ማጋባት ተገቢ አይደለም፡፡
ምክንያቱም ሳይዋደዱ ከተጋቡ ኑሯቸው ጭቅጭቅና ጥርጣሬ የተሞላበት ሊኾን ይችላልና ነው፡፡ ስለዚህ ወደ ጋብቻ ሕይወት ከመግባታችን በፊት ከአጋራችን ጋር በሙሉ ልብ መተማመንና መስማማት ይገባል፡፡ “ወኢይኩን ተዋስቦ ዘእንበለ በሥምረተ ክልኤሆሙ እለ ይትዋሰቡ ወበሥምረተ እሉ እሙንቱ ታሕተ ምግብናሆሙ ወዝንቱኒ ይከልእ እምአውስቦ …፤ በባልና ሚስት ፈቃድ ነው እንጂ ያለ ሁለቱ ፈቃድ ጋብቻ አይጸናም፤ አይፈጸምም፡፡ ወላጅ፣ ወይም አሳዳጊ ሳይፈቅድ ማጋባት አይገባም፤” እንዲል ፍትሐ ነገሥት (አን. ፳፬፣ ክፍል ፲፭)፡፡
በጋብቻ የመወሰን ፈቃድ እንደ ተሰጠን ዂሉ ፈቃደ ሥጋችንን ማሸነፍ እንደምንችል እርግጠኞች ከኾንን አለማግባትም ማለትም በድንግልና (በምንኵስና) መኖር እንችላለን፡፡ ለዚህም እግዚአብሔር አምላክ የዝሙትን ፆር አርቆላቸው ከሴት ርቀው፣ ንጽሕ ጠብቀው በድንግልና (በምንኵስና) የሚኖሩ አባቶች እና እናቶች አብነቶቻችን ናቸው፡፡ ጌታችን አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የባልና ሚስት ያለ ምክንያት መፋታት አመንዝራነት እንደ ኾነ ሲያስተምር ቅዱሳን ሐዋርያት “የባልና የሚስት ሥርዓት እንዲህ ከኾነስ ማግባት መልካም አይደለም” አሉ። ጌታችንም “ይህ ነገር ለተሰጣቸው ነው እንጂ ለዂሉ የሚቻል አይደለም፡፡ ከእናታቸው ማኅፀን እንዲሁ የተወለዱ፤ ሰዎች የሰለቧቸው፤ ስለ መንግሥተ ሰማያትም ራሳቸውን የሰለቡ ዣንደረቦች አሉ፡፡ መታገሥ የሚችልስ ይታገሥ” በማለት ስለ ጋብቻ እና ድንግልና ሕይወት አስረድቷቸዋል (ማቴ. ፲፱፥፲፩)፡፡ ይህ ኃይለ ቃል፣ ጋብቻም ኾነ ድንግልና በእግዚአብሔር ፈቃድ የሚመሠረት ሕይወት መኾኑን ያመላክታል፡፡
ይቆየን


@yeEregnaw_beg
@orthodox_betie
66 viewsኢዮብ ባለሀገሩ, 08:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 10:02:38 ዮሐንስም ባያቸው ጊዜ ደነገጠ፤ ከዚያ በፊት ሰው አይቶ ስለማያውቅ የእናቱን አስክሬን ብቻውን ትቶ ወደ ጫካ ሸሸ፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም የዮሐንስን ፍርሃት አራቀለትና እንዲህ አለው፤ ‹‹እኛን ከማየትህ የተነሣ አትፍራ፤ አትደንግጥም፤ አይዞህ እነሆ የእናትህ ዘመዶች ማርያምና ሰሎሜ በእናትህ አስክሬን ላይ መልካም ነገር ሊያደርጉ መጥተዋልና ና ወደ እኛ ቅረብ›› አለው፡፡ ዮሐንስም ይህን ቃል ከጌታችን አንደበት በሰማ ጊዜ ወደኋላው ተመለሰ፡፡ ከመሬትም ላይ ወድቆ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ሰገደለት፡፡ ጌታችንም እመቤታችን ማርያምንና ሰሎሜን ‹‹በጠማው ጊዜ ለእርሷ ይጠጣ ዘንድ ለዮሐንስ በፈለቀችለት ውኃ የኤልሣቤጥን ሥጋ አጥባችሁ ገንዙ›› አላቸው፡፡ እንዳዘዛቸውም የኤልሣቤጥን አስክሬን አጥበው ገነዙ፡፡ ጌታችንም ቅዱስ ሚካኤልንና ቅዱስ ገብርኤልን ይመጡ ዘንድ አዘዛቸው፡፡ እነርሱም ፈጥነው እንደ ዐይን ጥቅሻ ከሰማይ ወርደው መጡና ከጌታችን ፊት ቆሙ፡፡ ጌታችንም ‹‹የኤልሣቤጥን ሥጋ የሚቀበርበትን መሬት ቆፍሩ›› አላቸው፡፡ ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤልም መቃብሩን ይቆፍሩ ዘንድ ጀመሩ፡፡ ጌታችን ዘካርያስንና ስምዖንን በአካለ ነፍስ ከሰማይ መጥተው በኤልሣቤጥ አስክሬን ላይ ጸሎተ ፍትሃቱን ያደርሱ ዘንድ አዘዛቸው፡፡ እነርሱም የኤልሣቤጥ አስክሬን ካለበት ቦታ ላይ ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል፣ እመቤታችን ማርያምና ሰሎሜ ከጌታችን ፊት ቆመው ሳለ ስምዖንና ዘካርያስ በአስክሬኑ አጠገብ ቆመው ጸሎተ ፍትሃቱን ያደርሱ ጀመር፡፡ ጸሎተ ፍትሃቱንም በጨረሱ ጊዜ መላእክት በቆፈሩት መቃብር ውስጥ ቀበሩዋትና የስምዖንና የዘካርያስ ነፍስ ወደነበረችበት ቦታዋ ተመለሰች፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም የኤልሣቤጥን መቃብር በትእምርተ መስቀል አምሳል ደፈነው፡፡ እርሷም ያረፈችበት ዕለት የካቲት ፲፮ ቀን ነው፡፡
ከዚህ በኋላ ዮሐንስን ብቻውን ከበረሃ ውስጥ ትተውት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን ጋር ወደ ናዝሬት ለመመለስ በደመናዋ ላይ ሄደ፡፡ ያንጊዜም ክብርት እመቤታችን ልጇን እንዲህ አለችው፤ ‹‹ጌታዬና አምላኬ ፈጣሪዬ ሆይ! ስለምን ዮሐንስን ብቻውን ከበረሃ ውስጥ ትተወዋለህ? እንዴትስ ትተነው እንሄዳለን? ወደዚህ ቦታ ይዛው የሸሸችው እናቱ ጥላው ሞታ በመቃብር ውስጥ ተቀብራለች፤ ከእኛ ጋር ይዘነው እንሂድ እንጂ›› አለችው፡፡ ዳግመኛም እመቤታችን እንዲህ አለችው፤ ‹‹ነፍስ ያለወቀ ሕፃን ስላሆነ አራዊት ይበሉታልና ይዘነው መሄድ አለብን›› አለችው፡፡ ጌታችንም ለቅድስት እናቱ እንዲህ በማለት መለሰላት፤ ‹‹በመምህርነት ወጥቶ ለእስራኤል ታይቶ እስከሚያስተምር ድረስ የሰማያዊው አባቴ ፈቃድ በበረሃ ውስጥ ብቻውን እንዲኖር ነው፡፡ አንቺ ብቻውን እንዴት ከበረሃ ይኖራል ትያለሽ፤ አራዊቶች እንዳይጣሉት ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ከእርሱ አይለይም፡፡ በፈለገው ነገር ሁሉ እንዲራዱትና እንዲታዘዙለት መላእክተ ብርሃንን አዝለታለሁ፡፡ ብርሃናዊው መልአክ ገብርኤልም ሰማያዊ ኅብስትን ለምግቡ ያመጣለታል፤ በጠማውም ጊዜ እንደ ወተት የነጣችውን እንደ ወለላ ማርም የጣፈጠችውን ውኃ ከኤዶም ገነት ያመጣለታል፡፡ ይህችንም እርሱ ካለበት ድንጋይ ሥር የምትፈልቀውን ውኃ እንደ እናቱ ጡት ለአፉ የጣፈጠች አደርግለታለሁ፡፡ አንቺ ብቻውን እንዴት በበረሃ ውስጥ ይኖራል ትያለሽ? እስከ ዛሬ ድረስም የጠበቅሁት እኔ ነኝ፤ ሌላ ማን ጠበቀው ብለሽ ነው? እኔ አይደለሁምን? ወዳጄ ዮሐንስን ሰማያዊው አባቴ ከዚህ ዓለም ፍጥረት ሁሉ በጣም አብልጦ ይወደዋል፡፡ አባቱ ዘካርያስም በሥጋው ቢሞት በነፍሱ ሕያው ስለሆነ ዮሐንስን ለማጽናናት በአካለ ነፍስ ከእርሱ እንዳይለየው አደርጋለሁ፡፡ እናቱ አልሣቤጥም በሥጋዋ ብትሞት በነፍሷ ሕያዊት ስለሆነች ታጽናናው ዘንድ በነፍሷ በፍጹም ከእርሱ እንዳትለየው አደርጋለሁ፡፡ ዮሐንስን የተሸከመች ማኅፀን ንዕድ፣ ክብርት ስለሆነች በሥጋዋ ውስጥ መጥፎ ሽታ ክፉ መዓዛ አይገኝባት፤ በመቃብሯም ውስጥ ትሎች አይገኙበት፡፡ ድንግል እናቴ ሆይ! አንቺ እኔን ፀንሰሽ ሳለሽ ወደ ኤልሣቤጥ በሄድሽ ጊዜ በእጇ ይዛ ጨብጣ፣ በአፏ በሳመችሽ ጊዜ እንዲህ ብላ ትንቢት ተናግራለች፡፡ ‹አንቺ ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ፤ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው፤ የጌታዬ እናቱ ወደ እኔ ትመጪ ዘንድ እኔ ምንድነኝ? ከእግዚአብሔር አግኝተው የነገሩሽን ቃል ይደረጋል ብለሽ የተቀበልሽ አንቺ ብፅዕት ነሽ፤ ክብርት ነሽ› ብላ ስላመሰገነችሽ እንኳን ሥጋዋ ሊፈርስ ይቅርና መግነዟም አይለወጥም፤ መቃብሯም አይጠፋም፤ ነፍሷንም ከሥጋዋ ጋር እንድትኖር አደርጋታለሁ፡፡› ስለ ወዳጁ ዮሐንስ ለድንግል እናቱ ነግሯት ከጨረሰ በኋላ ዮሐንስን ከበረሃ ውስጥ ትተውት በደመና ላይ ተጭነው ወደ ናዝሬት ተመለሱ፡፡ ዮሐንስም አድጎ በሀገረ እስራኤል እስከተገለጠበት ጊዜ በበረሀ ኖረ፡፡
(ምንጭ፡- ገድለ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ-ደብረ መንክራት ሚጣቅ ቅዱስ አማኑኤል አንድነት ገዳም ያሳተመው፣ የመስከረምና የየካቲት ወር ስንክሳር)
107 viewsኢዮብ ባለሀገሩ, 07:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 10:02:38 ልደቱ ለቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ
ሰኔ ፳፰ ቀን ፳፻፲፬ ዓ.ም
ከካህን አባቱ ዘካርያስና ከቅድስት እናቱ ኤልሣቤጥ የተወለደው መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ የስሙ ትርጓሜ ‹‹ፍሥሐ፣ ሐሴት፣ ርኅራኄ›› ነው። የመወለዱም ነገር እንዲህ ነው፤ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል በአምላኩ ትእዛዝ ወደ ዘካርያስ በመምጣት በመጀመሪያ በመሠዊያው በስተቀኝ በኩል ተገልጦ ታየው፡፡ ከዚያም ‹‹ዘካርያስ ሆይ፥ ጸሎትህ ተሰምቶልሃልና አትፍራ ሚስትህ ኤልሳቤጥም ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፥ ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ፤ ደስታና ተድላም ይሆንልሃል፡፡ በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል፡፡ እርሱ በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ ይሆናልና የወይን ጠጅና የሚያሰክርም መጠጥ ሁሉ አይጠጣም፤ ከእናቱ ማሕፀን ጅምሮም መንፈስ ቅዱስ ይመላበታል፡፡ ከእስራኤልም ልጆች ብዙዎቹን ወደ አምላካቸው ወደ እግዚአብሔር ይመልሳቸዋል፡፡ እርሱም የአባቶቻችን ልብ ወደ ልጆች፥ የከሓዲያንንም ዐሳብንም ለእግዚአብሔር የተዘጋጀ ያደርግ ዘንድ በኤልያስ መንፈስ ቅዱስና ኃይል በፊቱ ይሄዳል፡፡›› ዘካርያስም መልአኩን እንዲህ አለው፤ ‹‹ይህ እንደሚሆን በምን አውቃለሁ? እነሆ፥ እኔ አርጅቻአለሁ፤ የሚስቴም ዘመንዋ አልፏል፡፡›› መልአኩም እንዲህ ብሎ መለሰለት፤ ‹‹እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ፤ ይህንም እነግርህና አበሥርህ ዘንድ ወደ አንተ ተልኬአለሁ፡፡ አሁንም በጊዜው የሚሆነውንና የሚፈጸመውን ነገሬን አላመንኽኝምና ይህ እስኪሆን ድረስ ዲዳ ትሆናለህ፤ መናገርም ይሳንሃል›› በማለት አበሠረው፡፡ (ሉቃ.፩፥፲፫-፳)
ሚስቱ ኤልሣቤጥም ፀነሰች፤ በዚያንም ወቅት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ፀንሳ እናቱ ኤልሣቤጥን ለመጠየቅ ሄደች፤ በማሕፀኗ ውስጥ ሳለም ሕፃኑ ለጌታችን ሰገደ፡፡ (ሉቃ.፩፥፴፱-፵፩) ኤልሣቤጥ የመውለጃዋ ጊዜ በደረሰ ጊዜ ወንድ ልጅን ወለደች፡፡ ዘመድ አዝማዱና ጎረቤቷም ደስ ተሰኙ ተሰብስቦ ወደ እርሷ መጥተው ጠየቋት፤ ሕፃኑም ስምንት ቀን በሞላው ጊዜ ይገረዝ ዘንድ ገራዦች መጥተው ስሙንም በአባቱ ስም ዘካርያስ ብለው ሊሰይሙት ፈለጉ፤ እናቱ ኤልሣቤጥ ግን ‹‹ዮሐንስ›› ተብሎ መጠራት እንዳለበት አሳወቀች፡፡ ይህንንም ነገር በሰሙ ጊዜ ካህኑ ዘካርያስን ማን በመባል እንዳለበት ጠየቁት፤ እርሱም መናገር የተሣነው ዲዳ ስለነበር ብራና ለምኖ ስሙ ‹‹ዮሐንስ ይባል›› ብሎ ጻፈ፤ ሁሉም ተደነቁ፤ የዘካርያስ አንደበትም ይህን ጊዜ ተፈታ፤ እርሱም አምላኩ እግዚአብሔርን አመሰገነ፡፡ (ሉቃ.፩፥፶፪-፷፬)
ንጉሥ ሄሮድስም መሢሕ ሕፃን ክርስቶስ መወለዱን ሲሰማ መንግሥቱን እንዳይቀማው በመፍራት በቤቴልሔም ያሉ ሁለት ዓመትና ከዚያ በታች ያሉ መቶ ዐርባ አራት ሽህ የቤቴልሔም ሕፃናትን በሰይፍ ሲያስገድል ድንግል ማርያም ከልጇ ጋር ወደ ግብፅ ስትሰደድ፣ ቅድስት ኤልሳቤጥ ደግሞ ወደ ሲና በረሃ ሄዳ ልጇን ዮሐንስን ከዚያ ደብቃዋለች፡፡ ከመሄዷ በፊት ግን ከባሏ ከዘካርያስ ጋር ሲሰነባበቱ የሚሆነውንም ሁሉ እርሱ ቀድሞ ያውቅ ነበርና ‹‹ሕፃኑን ልጄን ሲያጡ እኔን ይገድሉኛል፤ አንቺ ግን ወደ በረሃው ይዘሽው ሂጂና በዚያ ሸሽጊው›› ብሎ መክሯታል፡፡ እርሷም ከሄደች በኋላ የርጉም ሄሮድስ ጭፍሮች ዮሐንስን ባጡት ጊዜ ወደ ዘካርያስ መጥተው ‹‹ልጅህን ወዴት አድርሰኸው ነው? ወዴትስ ደበቅኸው? አሁን ከደበቅህበት አምጥተህ ፈጥነህ አስረክበን›› በማለት የፍጥኝ አስረው ካሠቃዩት በኋላ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ከሚሠዋበት በቤተ መቅደስና በዕቃ ቤት መካከል አንገቱን ቆርጠው ገደሉት፡፡ የዘካርያስም ደም እስከ ሰባት ዓመት ድረስ እየፈላ ደሙ ሲካሰሳቸው ኖረ፡፡ ‹‹ቅድስት ኤልሣቤጥም ልጇን ዮሐንስን ይዛ ወደ በረሃ ከገቡ አምስት ዓመት በሆናቸው ጊዜ ዮሐንስ ዕድሜው ሰባት ዓመት ከመንፈቅ ከሆነው በኋላ እናቱ ኤልሣቤጥ ሞተችበትና ብቻውን ከበረሃ ውስጥ ተወችው፡፡ ዮሐንስም በሰፊዋ በረሃ ውስጥ በአራዊቶች መካክል ብቻውን ቀረ፡፡ ለዮሐንስ ግን በእርሱ ላይ ምንም መጥፎ ነገር ሳያደርጉ የቶራና የአንበሳ የነብርም ልጆች እንደ ወንድምና እንደ እኅት ሆኑት፡፡ አራዊቶችም ሁሉ ወዳጅ ሆኑት፡፡ ምግቡም የበረሃ ቅጠል ነው፤ መጠጡም ከተቀመጠባት ድንጋይ ሥር የፈለቀችለት ውኃ ነበረች፡፡ ዮሐንስ ሰውነትን አለምልመው፣ ሥጋን አለስልሰው፣ ገጽንና ፊትን የሚያሳምሩትን ምግቦች አልተመገበም፡፡ የበረሃ ቅጠሎችንም አልተመገበም፡፡ አንቦጣ ከተባለችው ከአንዲት የበረሃ ቅጠልና ከጣዝማ ማር በስተቀር ከሚበሉት ምግቦች ሁሉ ዮሐንስ ኅርምተኛ ሆኖ የተለየ ነበር›› ይላል ቅዱስ ገድሉ፡፡ ነገር ግን ‹‹አንቦጣ›› ተብላ የምትጠራ አንዲት የበረሃ ቅጠልንና የጣዝማ ማርን እየተመገበ ማደጉን ለመግለጽ ብዙ ጊዜ በተለምዶ ‹‹የዮሐንስ ምግቡ የበረሃ አንበጣ ነበር›› ተብሎ የተሳሳተ ነገር ሲነገር ይሰማል፡፡
ንጉሥ ሄሮድስ በሞተ ጊዜ እነሆ የእግዚአብሔር መልአክ በግብፅ ኀገር ለዮሴፍ በሕልም ተገልጦ በመታየት ‹‹እነሆ የዚህን ሕፃን ነፍስ የሚሹ ሙተዋልና ተነሥተህ ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ምድረ እስራኤል ተመለስ›› ካለው በኋላ ዮሴፍ ተነሥቶ ሕፃኑንና እናቱን ይዞ ወደ ምድረ እስራኤል ገባ፡፡ ጌታችን ‹‹ልጄ ናዝራዊ ይባላል›› ተብሎ በነቢይ የተነገረው ቃል ይደርስ ይፈጸም ዘንድ መጥቶ ናዝሬት በምትባል ሀገር ተቀመጠ፡፡ ለሞት ይፈልገው የነበረው የተረገመ ከሃዲ ሄሮድስ ከሞተ በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከድንግል ማርያም ጋር ከምድረ ግብፅ ተመልሶ በናዝሬት ተቀምጦ ሳለ የዕድሜ ባለፀጋ የሆነችው የዮሐንስ እናት ክብርት ኤልሳቤጥ ልጇን ዮሐንስን ይዛው ወደ ደብረሲና በረሃ ከገቡ ከአምስት ዓመት በኋላ ዐረፈች፡፡ ዮሐንስም በእናቱ አስክሬን አጠገብ ተቀምጦ በእጅጉ እያዘነ መሪር ልቅሶንም ሲያለቅስ የተሸሸገውን ሁሉ የሚያውቅ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በናዝሬት ተቀምጦ ሳለ የኤልሳቤጥን መሞትና ዮሐንስ ብቻውን ከበረሃ ውስጥ ተቀምጦ እያለቀሰ መሆኑን ዐወቀ፡፡ ጌታችን በናዝሬት ሆኖ ያለቅስ ጀመር፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ልጇ ወዳጇ ሲያለቅስ ባየችው ጊዜ ‹‹ልጄ ወዳጄ ሆይ! ምን ሆንክ? ስለምንስ ታለቅሳለህ?›› ብላ ጠየቀችው፡፡ ጌታችንም ለቅድስት እናቱ እንዲህ በማለት መለሰላት፤ ‹‹እነሆ ወገንሽ የሆነችው ኤልሣቤጥ ዐረፈች፤ ዮሐንስንም ብቻውን ከበረሃ ውስጥ ተወችው፡፡ ዮሐንስም ሕፃን ስለሆነ የሚያደርገውን አጥቶ በእናቱ አስክሬን አጠገብ ከፊት ለፊቷ ተቀምጦ በመረረ ኃዘን ያለቅሳል፡፡ እናቴ ሆይ እኔም ዘመድሽ የሆነ የዮሐንስን ልቆሶ ስላወቅሁኝና የእርሱም ኃዘን ስለተሰማኝ የማለቅሰው ስለዚህ ነው›› አላት፡፡ በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የፀናች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም የኤልሣቤጥን መሞት በሰማች ጊዜ በጣም ምርር ብላ አለቀሰች፡፡ ያንጊዜም ብርሕት ደመና መጥታ ከፊታቸው ቆመች፤ ፈጥናም ተሸከመቻቸውና ኤልሣቤጥ ከሞተችበት ዮሐንስም ካለበት ቦታ ከደብረሲና በረሃ ውስጥ ወስዳ አደረሰቻቸው፡፡
82 viewsኢዮብ ባለሀገሩ, 07:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ